መርስኤ ኪዳን

ግንቦት 15 ቀን 2002 ዓ.ም. የተካሄደው ምርጫ ማንም ባልገመተው መልኩ በኢህአዲግ ሙሉ በሙሉ አሸናፊነት ተጠናቅቋል። ይህ ውጤት ለተለያዩ አካሎች የተለያየ ትርጉም ይኖረዋል። በውጭ ሀገር ሆነው ”ሠላማዊ ትግል ዋጋ የለውም፤ ኢህአዲግን በተገኘው መንገድ ሁሉ በማጥቃት መደምሰስ ያስፈልጋል” ለሚሉ ለዚህ አቋማቸው ማረጋገጫ እንደሆነ አድርገው ይወስዱታል። በሀገር ውስጥ በሠላማዊ መንገድ ዓላማቸውን ለማሳካት ሲጥሩ ለቆዩት ደግሞ በሠላማዊ ትግልና በአመፅ መካከል አንዱን እንዲመርጡ የሚያስገድድ ሁኔታ ፈጥሯል። የዚህ ጽሑፌ ትኩረት የሚሆነው እነዚህ በሠላማዊ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ፓርቲዎች የገጠማቸውን ፈተና ለመዳሰስና በበኩሌ ያዋጣል የሚለውን ለመጠቆም ነው። ወደዋናው ጉዳይ ከማምራቴ በፊት ግን፤ ይህ ያልተጠበቀ ውጤት እንዴት ተከሰተ የሚለውን ለማየት እሞክራለሁ።

 

ግንቦት 15 በተካሄደው ምርጫ ከ547 ወንበሮች ውስጥ ከሁለት መቀመጫዎች በስተቀር የተቀሩት በሙሉ በኢህአዲግና በአጋሮቹ መያዛቸውን ምርጫ ቦርድ በጊዜያዊ ውጤት መግለጫው አርድቶናል። አርድቶናል ያልኩበት ምክንያት ይህ ዜና ለማንም የምስራች ሊሆን ይችላል ብዬ ስለማላስብ ነው። ገዥው ፓርቲ ራሱ ሊደነግጥና ሊያስብበት የሚገባ ዜና ነው። ምናልባት የምስራች ከሆነ ሊሆን የሚችለው በውጭ ሆነው የትጥቅ ትግል እናካሂዳለን እያለ ለሚፎክሩ አካላት ነው። ከፋም ለማም ይህ ውጤት እንዴት መጣ የሚለውን ለማየት ስሞክር በሦስት አንኳር ነጥቦች ሊከፈሉ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው የመጡልኝ። ... (ሙሉውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ