ዓባይ (ገ/ኢ. ጐርፉ)
ዓባይ
ገ/ኢ. ጐርፉ
ፀሐይ ዳመናው ቁልጭ-ልጭ
በጋው አልፎ ክረምት ገባ፣
ዳመናው ብልጭ-ልጭ
ነጐድጓዱ ነጐደ፣
መስከረም እስኪጠባ
ወንዙ ሄዶ ገደብ አልባ ...
አባይ ተዥጐደጐደ!
ዝናቡ ዘንቦ-ዘንቦ
መሬቱን ተረተረው፣
ግድብ የለ ገንዳ፣ ገንቦ
አፈሬን አጥቦ-አጥቦ
ቁልቁሊት አምዘግዝጎ
መሬቱን ሸረሸረው
ግብፅ ወስዶ ሊከምረው
ወሰደው ጠራርጎ ...
ማነው ፈረሰኛው
ዘምቶ ከወድያ ማዶ
ከባዕድ ምቀኛው
የሚመልስ ያንን
ያገሬ አፈሩን፣
ባሕር-ዛፉ ማገዶ
አለቀ ነድዶ-ነድዶ!
አንድ በሉልኝ እንጅ
ወንድም ጋሼስ የለም ወይ?
ስሞትስ አያይም ወይ?
ይህ መቸውም አይበጅ
በግብፁ በጠላቴ
ማቀቀ አካላቴ፣
ተቀጨ ልጅነቴ …
ገ/ኢ. ጐርፉ
9852 Stanford Av., Garden Grove, CA. 92841



