አብርሃም ቀጀላ

Geez
በተለምዶ ግዕዝ ፊደል ተብሎ የሚጠራው የሁሉም ኢትጵያያውያን ፊደል

ከጥንት ጀምሮ አስቀድሞ በሀገረ ኢትጵያያ ላሉት የሕዝብ ቋንቋዎች ሁሉ በምልአት፣ በጥራትና በብቃት ሲያገለግል የነበረው፤ በተለምዶ ግዕዝ ፊደል ተብሎ የሚጠራው የሁሉም ኢትጵያያውያን ፊደል እ.ኤ.አ በ1983 ዓ.ም. በመንግሥት መለዋወጥ ተፈጥሮ በነበረው ክፍተት ጥቂት ግለሰቦች በፖለቲካ ስሜታዊነትና ግልፍተኝነት ወደፊት በቀጣዩ ሕዝቦች ላይ የሚያመጣውን ጣጣ፣ መዘዝ፣ ጉዳት እና ቀውስ ሳያጤኑ የቀድሞ ያለፈው ፖለቲካዊ ችግር በፈጠረው ቁጣና ትኩሳት ብቻ በመነዳት አፋን ኦሮሞ ግእዙን እንዲተው አድርገዋል።

በዚህ በነባሩ የግዕዝ ፊደላችን አፋን ኦሮሞን በተመለከቱ

1ኛ. ከ16ተኛው ክፍለ ዘመን በፊት ቅዱስ ቁርአን የተከተበበት ሰነድ በሀረር ይገኛል።
2ኛ. በ1845 ከአፄ ቴዎድሮስ ዘመን በፊት የመጽሐፍ ቅዱስ ወንጌላት በከፊል የተፃፋበት
3ኛ. ከ140 ዓመታት በፊት በኦሮሞው ሊቅ በቅዱስ አናሲሞስ ነሲብ (አባገመችስ) ሙሉው መፅሃፍ ቅዱስ በአፋን ኦሮሞ የተተረጎመበት
4ኛ. በ1967 ዓ.ም. ከ20 በላይ በሆኑ በተለያዩ ብሔርና ብሔረሰቦች ቋንቋ የመሬት አዋጅን ፈትፍቶና ቁልጭ አድርጎ የተገለፀበት
5ኛ. የኢትዮጵያ የመስረተ ትምህርት ከ30 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች ቋንቋዎች በብቃትና በጥራት ይሰጥበት የነበረ
6ኛ. የበሪሳ ታላቅ የአፋን ኦሮሞ ጋዜጣ ለዘመናት በበርካት ቁጥሮች ሲሰራጭበት የነበረ
7ኛ. የቀድሞው የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በበርካታ ባብዛኛው ከ 45 ብሔር ብሔረሰቦች በላይ ቋንቋዎች የተገለጡበት
8ኛ. በበርካታ የእስልምና ዝክሮች፣ መንዙማዎች የተፃፋበት የተዘከሩበት
9ኛ. በርካታ የክርስትያን መዝሙራት በኦሮምኛና በሌሎች ቋንቋዎች የተገለጡበት
10ኛ. በአፋን ኦሮሞና በሌሎችም ከረጅም ዘመናት በፊት የመዝገበ ቃላት የተደራጀበት ናቸው።

ከእነዚህ ነገሮችም በላይ ብዙ በመሳሰሉት ሁሉ አድጎ ዳብሮ ተፈትኖ ተፈትሾ ተመስክሮለት የደረጀ መሆኑን ሰንዳፋ ከተማ የተወለዱት እውቁ ኢትዮጵያዊ የቴክኖሎጂ ሳይንቲስትና አርበኛ ዶ/ር አበራ ሞላ (Dr. Aberra Molla) ከዛሬ 30 ዓመታት በፊት ማለትም ኢሕዴግ አገሪቱን ከመቆጣጠሩ በፊት በተለምዶ የግዕዝ ፊደል (Ethiopic) ተብሎ የሚጠራውን የኢትዮጵያውያን ሁሉ ፊደል በኮምፒተር እንዲጻፍ በመፍጠርና በዩኒኮድ በማስገባት በአለም አቀፍ ደረጃ እንዲመዘገብ አድርገዋል። (ቀሪውን ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ