አምሃ ዳኘው (የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናት እና ምርምር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.  

ይህ ጽሑፍ በታህሳስ ወር 2001 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ለአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ቀርቦ የነበረ ጥናታዊ ጽሑፍ ነው። አቶ አምሃ ዳኘው የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የጥናት እና ምርምር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ናቸው።

 

ጽሑፉ ለአንድነት ጥናት እና ምርምር ቋሚ ኮሚቴ ቀርቦ የዳበረ እና በቋሚ ኮሚቴው የፀደቀ ጽሑፍ ነው። ጽሑፉ ውይይት ሳይደረግበት ቆይቶ በጥር ወር አጋማሽ ላይ ለብሔራዊ ምክር ቤት አባላት እንዲዳረስ ተደረገ። ያም ሆኖ በፓርቲው አካላት ውስጥ እስካሁን ድረስ ውይይት ስላልተካሄደበት፣ የመድረክ ስብስብ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች በታህሳስ ወር ሁለተኛ አጋማሽ ላይ ለሴሚናር ያቀረቡትአቸው ጥናታዊ ጽሑፎች ሲገኙ ይህን ጽሑፍ እንደገና በሴሚናሩ ላይ ከቀረቡ ጽሑፎች ጋር አገናዝቦ በድጋሚ የተዘጋጀ ጽሑፍ ነው።

 

አቶ አምሃ በዚህ ጽሑፋቸው ጠለቅ ብለው የቃኙዋቸው ርዕሰ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፤ በኢትዮጵያ የወቅቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አሰላለፍ፤ ከ1997 ምርጫ በኋላ በኢትዮጵያ የፖሊቲካ ፓርቲዎች አሰላለፍ፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ውህደት፣ የግንባር እና የጥምረት ግንኙነት ከአንድነት የፖለቲካ ዓላማ አንፃር፤ አሁን ካለው የፖለቲካ አሰላለፍ አንፃር ለአንድነት ከውህደት፣ ከግንባር እና ከጥምረት ግንኙነት የትኛው ተመራጭ ይሆናል? ምንስ ሊደረግ ይገባል? ... የሚሉት ናቸው። ሙሉውን ጥናታዊ ጽሑፍ በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ! (መልካም ንባብ!)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ