ከዘፀዐት በፊት (በትረ ሙሴ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

በትረ ሙሴ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የተወደዳችሁ ወገኖቼ!

ተደጋጋሚ ውድቀት፣ ውርደት፣ ስደት፣ መከራ፣ ችግር እና የመሳሰለት ነገሮች ለገጠመው አንድ ህዝብ በነገሮች ላይ እምነት ቢያጣ አይፈረድበትም። እኛ ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ሰዓት የገጠመን ድክመት ይኼ ነው። እምነት የለንም። ስለዚህ ሁለ ነገር ጭልምልም ብሎ ይታየናል፤ ከዚያ ሁሉ ነገር ይበላሻል። ለማንኛውም ነገር ትዕግስት አስፈላጊ መሣሪያ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ሰውዬው ጉዴን አፈላው አይደል?” - በፈቃዱ ሞረዳ

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ጋዜጠኛና ደራሲ ተስፋዬ ገብረአብ Tesfaye Gebreabከበፈቃዱ ሞረዳ

“የጋዜጠኛው ማስታወሻ” በሚል ስያሜ አንድ መጽሐፍ አዘጋጅቶ (ጽፎ) በተለይም የ“ዲያስፖራው” ቡና ማጣጫና ወግ መሰልቀጫ ሆኖ የሰነበተው ተስፋዬ ገብረአብ በአንድ ድረ ገጽ ላይ ቃል ተውሶ፣ ስሜን ጠቅሶ ውንጀላ ቃጥቶ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ መለስ በንጹሃን ደም በቦካ እጃቸው ምን ሊጽፉበት ነው? (ልዑልሰገድ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ልዑልሰገድ (ከአቢሲኒያ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የዛሬ 18 ዓመት ግንቦት 13 ረቡዕ አዲስ አበባ ውስጥ ዕኩለ ቀን ላይ በውይይት ታክሲ እጓዛለሁ። ከቀበና አቅጣጫ የአራት ኪሎ አደባባይን አቋርጦ ታክሲው ወደ ፒያሣ አቅጣጫ ይገሰግሳል። በታክሲው ስፒከር የዕለቱ የዜና ዕወጃ ይሰማል። ዜናው ከወትሮው የተለየ ነበር። ኮ/ል መንግሥቱ ሀገር ጥለው ኮበለሉ የሚል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወርቅ ኢዮቤልዩ እንዲህ አይከበርም ያለው ማነው? (ምጥው ለቤ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን መንበረ ፕትርክና 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤልዩ በዓል አከባበር በቤተክህነቱ ግቢ

ምጥው ለቤ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

ሰኞ ሰኔ 29 ቀን 2001 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስቸኳይ ምልዐተ ጉባዔ በመጥራቷ፤ ኃላፊነት ያለባቸው ሊቃነ ጳጳሳት በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ከየሀገረ ስብከታቸው ወደ መንበረ ፓትርያርኩ የእየተሰቡ መገኘታቸው ተደምጧል። ጉባዔው በቤተክህነቷ አካባቢ አለ ለሚባለው አስተዳደራዊ ችግር መፍትሔ ይሰጣል ተብሎ ይገመታል። ይህ ጉባዔ የሚካሄደው ቤተክህነቷ የራሷን ፓትርያርክ በሾመችበት በ50ኛ ዓመት ላይ ነው። ታሪክን አጣቅሶና ጉባዔውን አስመልክቶና “ምጥው ለቤ” የሚከተለውን ጽሑፍ አድርሶናል። መልካም ንባብ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መልዕክተ ኦባንግ (ስለሺ ዘእንግልጣር)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ስለሺ ዘእንግልጣር This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

“የምንታገለው ለመንደር ወይስ ለሀገር? መታገል ያለብን ለሀገር አነድነት ነው፣ ሀገር ከሌለች መንደር አይኖርምና።”

አቶ ኦባንግ ሜቶ ‘የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የትብብር ንቅናቄ’ መስራች ከተናገሩት ተተርጉሞ የተወሰደ

አተኩሮ ላየው ቅንነቱን ለመረዳት ጊዜም አይፈጅም። በተኮላተፈና ጥርት ባለ አማርኛውም ሆነ አቀላጥፎ በሚናገረው እንግሊዝኛው በጨዋ ኢትዮጵያዊነት ከአፉ የሚወጡት ቃላት ልብ ውስጥ ጠልቀው ይገባሉ። ዘወትር በሄደበት ሁሉ የሚናገረው ኢትዮጵያዊነትን ነው። ሊነግረን የሚፈልገው ልዩነታችንን ወደጎን በመተው እርስ በርሳችን በመነጋገር ችግሮቻችንን እየፈታን አንድነታችንን ማጠንከር እንዳለብን ነው። በዘርና በመሳሰሉት ዛሬ ገዥው ፓርቲ የሚያራምደው የጎሣ ፖለቲካ ውስጥ ገብተን በመዳከር እርስ በርሳችን እንዳንጠላላና እንዳንቀያየም ይማጸነናል። “የነገዪቱ ኢትዮጵያ እጣ ያሰጋኛል፤ ዛሬ ካልተባበርን፣ ኢትዮጵያዊ ነን የምንል ሁሉ እጅ ለእጅ ተያይዘን መሔድ ካልቻልን፣ ነፃና ፍትሕ የሰፈነባት ዲሞክራሲያዊ ኢትዮጵያን ለማየት የምንጓጓበትን ጊዜ ያርቅብናል እንጂ አያቀርብልንም” ይለናል ኦባንግ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሁሉ ነገር በእጃችን ነው (ግርማ ካሣ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ግርማ ካሣ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ) ሰኔ 17 ቀን 2001 ዓ.ም.

ኢትዮጵያን በጽጌረዳ አበባ እመስላታለሁ። ጽጌረዳ አበባ በጣም ተወዳጅ የሆነች አበባ ናት። ብዙ ጊዜ በማስቀመጫ ውስጥ ተደርጋ የሚመጡ እንግዶች በሚያዩዋት ቦታ ትቀመጣለች። የክብር፣ የፍቅርና የውበት ምልክት ናት። ኢትዮጵያ ሀገራችንም በነፃነቷና በአንድነቷ ታፍራና ተክብራ የኖረች፣ ከተለያዩ ብሔረሰቦች የተውጣጡ ልጆቿ ውበቷ የሆኑላት፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ለጥቁር ህዝብ ሁሉ ኩራት የሆነች ሀገር ናት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...