ከአኝዋክ የሀዘን ድንኳን ወደ ኢትዮጵያ ልቅሶ ዳስ፤ የኦባንግ ጉዞ (ልጅ ተክሌ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Obang, Photo: Abbay Mediaልጅ ተክሌ - ከካናዳ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የታክሲ ነጂው መገረም፤ ኢትዮጵያዊ የማይመስል ኢትዮጵያዊ

አበዛኸው እንዳትሉኝ። ይሄ መነገር ያለበት ታሪክ፤ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ልናውቀው የሚገባ ክስተት ስለሆነና አላደርስ ስላለኝ ነው ተመልሼ የመጣሁት። የዛሬ አራት አመት አካባቢ አንድ ጥቁር ያለ (“ቁ” ይጠብቃል) “ኢትዮጵያዊ የማይመስል” ኢትዮጵያዊ፤ ሌላ ኢትዮጵያዊ የሚመስል ኢትዮጵያዊ በሚያሽከረክረው ታክሲ ከአንዱ የዋሽንግተን ዲ.ሲ. አውሮፕላን ማረፊያ ወደ መሀል ከተማ ይጓዛል። መሰለኝ። በእንግሊዘኛ ንግግር ጀመሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቴዲ ዜማዎች ጥላቻን የሚያከስሙ የፍቅር ቅመሞች ናቸው (ዳኛቸው ቢያድግልኝ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ቴዲ በታሰረ በ415ኛው ቀን ከ1900፡45፡15 ሰዓት በዕለተ ቅዳሜ ተተየበ

ዳኛቸው ቢያድግልኝ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

የዘመናት የህዝብ ብሶትን ያጨናገፈውና ሀሳዊ ድመሲዕ ሆኖ መጣሁላችሁ ብሎ በወርሃ ግንቦት የመጣብን የትግራይ ነፃ አውጪ እንደ ጠፉ ጎልያዶች ይጠፋል። እንደ ጥንብ ክርፋት በስብሶ ሲያልቅ ይረሳል። የፍቅር መንፈሥ፣ የአንድነት ዝማሬ፣ የሕብረት ፍካሬ ግን የትውልድ ዘመናትን እየተሸጋገረ በብርታት ላይ ጉልበት፣ በእውቀት ላይ ብልህነት እያከለበት ይኖራል። ፍቅርን የዘከሩ ሰዎች ሊያልፉ ይችላሉ። ፍቅር ሲያልፍ ግን ዓለምም ይጠፋል። ሰማይና ምድር በፍቅር ተዘርግተዋልና!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጉባዔ ቫንኩቨርና ውሳኔ ቫንኩቨር፤ ይህቺ ናት ጉባዔ!! (ልጅ ተክሌ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ልጅ ተክሌ

“ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰቆቃ ለማዋጣታችን ማስረጃ አለ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ መፍትሄ ለማዋጣታችን ግን ማስረጃ የለም!! እርስ በርሳችን በመናከስና መወያየት ባለመቻላችን የጠላታችንን እድሜ እያራዘምን ነው” ከተሰብሳቢዎች አንዱ

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያና ኤርትራ ከየት ወዴት? (ፕ/ር ተስፋጽዮን መድኅኔ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Prof. Tesfatsion  Medhanie ፕ/ር ተስፋጽዮን መድኅኔ"የኢትዮጵያንና የኤርትራን ወንድማማች ህዝቦች ሊቀራርብ የሚችለው የኮንፌዴሬሽን ሥርዓት ነው" ፕ/ር ተስፋጽዮን መድኅኔ

ባለፈው ግንቦት 7 ቀን 2001 ዓ.ም. በካሊፎርኒያ ሳን ዮሴ በተካሄደው የኢትዮጵያውያንና የኤርትራውያን የወዳጅነት ኮንፈረንስ ላይ ፕ/ር ተስፋጽዮን መድኅኔ እና ፕ/ር ዳንኤል ክንዴ ተናጋሪዎች ነበሩ። ፕ/ር ተስፋጽዮን ”ኢትዮጵያና ኤርትራ ከየት ወዴት?” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሑፍ የኢትዮጵያንና የኤርትራን ወንድማማች ህዝቦች ሊቀራርብ የሚችለው የኮንፌዴሬሽን ሥርዓት ነው ይላሉ። ፕ/ር ዳንኤል ክንዴ ደግሞ በፌዴሬሽን ነው ሲሉ በኮንፈረንሱ ላይ ጥናታዊ ጽሑፎቻቸውን አቅርበዋል። ለዛሬ የፕ/ር ተስፋጽዮንን ሙሉ ንግግርና ጽሑፍ እንደሚከተለው ቀርቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኤርትራ ስጦታ፤ የታሪክ እስር ቤት፣ የህወሀት ጥፋት (አባኪያ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

“የራስን እድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል የሚለው አንቀጽ በሕገ መንግስቱ ውስጥ መጨመር ስህተት ነው።” ፕሬዚደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ-2009 

“የራስን እድል በራስ መወሰን እስከመገንጠል መብት እንቀበላለን።” መለስ ዜናዊ፣ ገብሩ አስራት፣ ስዬ አብርሀ፣ አረና ትግራይ - 2009

ከአባኪያ

አጀንዳን ስለመቅረጽ፤ የኛን አጀንዳ በኛው

ልቤ እንደተንጠለጠለ የላፕቶፔ ሰሌዳ ላይ እንዳፈጠጥኩ ነው ልብ የሚሰቅል ቦታ ላይ ቃለ ምልልሱ የተቆረጠው። የሚቀጥለው ክፍል ምንም ይሁን ምን እስካሁን ያየሁት ክፍል አንድና ሁለት ብቻ አርክቶኛል። ከዚህ በኋላ አጀንዳችን የኛ ነው። እስካሁን አጀንዳችንን የሚደረድርልን ሕወሀት ነበር። አሁን እኛው ነን። “ማንም የታሪክ እስረኛ ሆኖ መኖር የለበትም። እኔም ራሴ የታሪክ እስረኛ መሆን አልፈልግም።” አልጨመርኩም፤ አልቀነስኩም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአስመራ ትዝታዬ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ግርማ ካሣ

W/t Birtukan, Paster Haile, Dr. Kiflu, Paster Tesfatsion & Teddy Afro (L to R)

በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እና በፕሬዝዳንት ኢሣያስ አፈወርቂ በግፍ የታሰሩ ሠላማዊ ወገኖቻችን መካከል በጥቂቱ። (ከግራ ወደ ቀኝ) ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ፣ ፓስተር ኃይሌ ነዕዝጊ፣ ፓስተር ዶ/ር ክፍሉ ገብረመስቀል፣ ፓስተር ተስፋጽዮን ሃጎስ እና አርስቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን።  

በቅርቡ የኢትዮጵያን ሪቪው ዋና አዘጋጅ አቶ ኤሊያስ ክፍሌ በድረ ገጻቸው ላይ አስመራ ሆነው የተነሱትን ፎቶግራፎች ተመለከትኩ። የአስመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የነበሩኩ ጊዜ በዚያ ያሳለፍኩትን ዓመታት ፎቶግራፎቹ አስታወሱኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...