“ሠላማዊ ወይስ ትጥቅ?” - እንካ ስላንቲያዎቹ!

የአንባብያን ድምፅ: 1 / 5

Star ActiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ኩችዬ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

ሰሞኑን በድረ-ገጾች ላይ የማነባቸው አስተያየቶችና ትችቶች ሁለት ቤሳ የምታወጣ ሃሳቤን እንዳካፍል ገፋፉኝ። “ኢህአዴግን ማስወገድ ወይስ መለወጥ?” በሚል ርዕስ ግርማ ካሣ፣ ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ ደግሞ “ሕብረትን በማስቀደም …”፣ ሮቤል አባብያ “አንድነት ፓርቲ ለሚከተለው የሠላም ጎዳና ይሁን ብለናል” በሚሉ ርዕሶች ያስነበቡን ሰነዶች “ሠላማዊ ወይስ ትጥቅ ትግል” በሚለው ትኩስ መነጋገሪያ ነጥብ ዙሪያ የሚያንዣብቡ ናቸው። እነዚህንና ሌሎችንም ጽሑፎች በአቡጊዳ እና በሌሎች ድረ-ገጾች ማንበብ ይቻላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ቴዲ አሁንስ የቀረለት አይመስለኝም" ዳኛ ወልደሚካኤል

የአንባብያን ድምፅ: 2 / 5

Star ActiveStar ActiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ

ወያኔ/ኢህአዴግ ለራሱ በአደገኛነቱ አንድ ጊዜ በጥርሱ ከነከሰው፣ በዚህም በዚያም አድረጎ መቦጫጨቁን አይለቅም። ምንን ፈርቶ! ለጊዜው ሁሉም በጁ፣ ሁሉም በደጁ አይደል? መቼም አበው "ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል" ይሉ የለም። እውነታቸውን ነው። ዛሬ ሁሉም አልጋባልጋ የሆነላቸው፣ ያ ቀን እስከሚመጣ ድረስ ነገም ዛሬ ይመስላቸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመድረኩ መመስረት መልካም ዜና ነው (ግርማ ካሣ)

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

የመድረኩ መመስረት መልካም ዜና ነው

ግርማ ካሣ ከቺካጎ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

(በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)

 

የግንቦት 7 ንቅናቄ ምንድነው? ምንስ አመጣው? ምንስ ሊያመጣ ይፈልጋል? (አንዳርጋቸው ጽጌ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

"የግንቦት 7 ንቅናቄ ምንድነው? ምንስ አመጣው? ምንስ ሊያመጣ ይፈልጋል?" በሚል ርዕስ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ሎንዶን ላይ እሁድ ሰኔ 15 ቀን 2000 ዓ.ም. (ጁን 22 ቀን 2008 እ.ኤ.አ.) ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ያደረው ንግግር ነው። ሙሉ ንግግሩን በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

 

«እየሮጡ የሚታጠቁት ፖለቲከኞች» (ፕ/ር መስፍን)

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

መስፍን ወልደማርያም (ፕ/ር) ሰኔ 2000 ዓ.ም.

በቅርቡ በአንድ ጋዜጣ ላይ ስለ ችጋር በተናገርኹት ላይ አንድ ስሙን የማላስታውሰው ሰው፣ ዛሬ ያለውን የገጠሩን ህዝብ የጥጋብ ኹኔታ ባለማወቄ አዝኖልኝ መልስ ሰጥቶ ነበር። ሰሞኑን በውጭ ቴሌቪዥኖች ከትግራይ እስከ ቦረና የተከሠተውን ችጋር በሚያሣቅቅ ኹኔታ ሲያሳዩን ነበር። ይህን በምጽፍበት ጊዜ ትግራይ ውስጥ ህዝቡ በቤተ ክርስቲያን ተሰብስቦ እግዚኦ እያለ ነው። አለማወቅ የሚባለው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚባለውን ከሆነ ጸሐፊው ትክክል ነበር። ነገር ግን ችጋርን እና ሞትን መደበቅ በጣም አስቸጋሪ ነውና እያየነው ነው፤ ላስተዋለ ችጋር ያባረራቸውን በአዲስ አበባ መንገዶችም ላይ ያያቸዋል። ይህንን ለማንሣት የተገደድሁት «እየሮጡ የሚታጠቁት ፖለቲከኞችና የትም የማያደርሰው መንገዳቸው» በሚል በአቶ ጌታቸው ረዳ የተጻፈውን ሳነብ በጣም የሚቀራረብ ሀሳብና አስተሳሰብ ስላገኘሁበት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...