እጃችን ለወገኖቻችን የተዘረጋ ይሁን! (ግርማ ካሣ)
ግርማ ካሣ ከቺካጎ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.) ሰኔ 13 ቀን 2000 ዓ.ም.
![]() | ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት፣ ስለ ኤድስ ለመነጋገር በተጠራ ስብሰባ ላይ፣ አንዲት የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑ የሕክምና ባለሞያ የተናገሩት አንድ አባባል ነበር። ያኔ ቀሳፊው የኤድስ በሽታ በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ገድሎ፣ የሰው ልጆች ቀንደኛ ጠላት ከተባሉት ውስጥ ከመጀመሪያዎቹ መከከል የተመደበበት ጊዜ ነበር። ይህ በሽታ ከየት እንደመጣና እንዴት ሊስፋፋ እንደቻለ ሃሳብ የሚሰጡ በርካቶች ነበሩ። ታዲያ እኝህ ሴት የትኩረት አቅጣጫው ወዴት ሊሆን እንደሚገባ ለማስረዳት የአንድ ነብርን ምሳሌ አቀረቡ። | |
በሻሸመኔ አካባቢ፣ “ድንበር የለሽ ሐኪሞች” የተሰኘው ድርጅት በሚያንቀሳቅሰው የእርዳት መስጪያ ማእከል፣አንዲት እናት ልጇን ስታጥብ | ||






