ክፉው ስደት የማያሳይ የማያሰማኝ የለም! (የማለዳ ወግ)
ነቢዩ ሲራክ
★ ውሃ የበላው ጎልማሳና እኔ ... ያኔ :(

የማወጋችሁ ዛሬ ስለሌለ፣ ትናንት ስለነበረ አንድ ጎልማሳ ወንድም ነው ... ተንከራታች እግሬ የማያደርሰኝ ቦታ የለም፣ ክፉው ስደት የማያሳይ የማያሰማኝ የለም። እኔና ከዚህ በታች የማወጋችሁ ጎልማሳ ወንድም ከሁለት ወር በፊት የሳውዲን የውጡ ምህረት አዋጅ ተከትሎ መልዕክት ልኮልኝ ግንኙነነት ተጀመረ ... ብዙ ሳይቆይ ለዓመታት ይሰራበት ወደ ነበረው የአሲር ግዛት ለኩባንያ ስራ ሳመራ በፊስቡክ የጻፍኩትን መረጃ ተመልክቶ በአካል ሊያገኘኝ እንደሚፈልግ ጠየቀኝ ... ፍቃደኝነቴን ገለጽኩለት ... ደስታው ገልጾልኝ በክልሉ ለስራ ጉዳይ ስተላለፍ ተገናኘን። ለሰዓታት ባንደ ተቀምጠን የሆድ የሆዱን ዘርግፎ እንደ ትልቅ ወንድም አምኖ አጫወተኝ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...