የሳምንቴ ትዝብትና ትንግርት!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አስፋ ጫቦ (Corpus Chirsti, Texas, USA)

Donald Trump.
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ “አርብ ማታ ስዊድን የደረሰው አደጋ!” አለ። ስዊድኖቹ “እንዴት እኛ ሳናይ፣ ሳንስማ ትርምፕ ሰማ!” አሉና አሽሟጠጡት። ይህንን ዜና ያገኘው ከFox ነበር።

አሜሪካ ዛሬም በሁለንተናው ግምባር ቀደም ነኝ ስለምትል (“ያማ ያለፈ ወሬ ነው!) የሚሉ ሞልተዋል) በፕሬዚዳንቱ፤ በዶናልድ ትራምፕ፤ ልጀመር። ”የኔ ጠላት የአሜሪካን ሕዝብ ጠላት ነው”፣ “They are not my enmeies but the enemy of the American people) ብሎ አረፈው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያና አሜሪካ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሙሉነህ እዩኤል

ኢትዮጵያና አሜሪካ ምን አገናኛቸው ትሉኝ ይሆናል። ነገሩ እንዲህ ነው፦ ባለፈው ሳምንት ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራም የሰባት አገሮች ዜጎች ወደ አሜሪካን አገር እንዳይገቡ እግድ ጥለው ነበር። ፕሬዝደንቱን ለዚህ ያነሳሳቸው እግዱ ከተጣለባቸው አገሮች የሚመጡ ዜጎች ለአሜሪካን ደህንነት የሚያሰጉ ሆነው ስላገኟቸው እንደሆነ ይናገራሉ፤ ብዙዎች ይህን ስጋት ባለመጋራት እገዳውን ቢቃወሙም። እገዳው ውሎ ሳያድር የዋሽንግተን ክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የተከበሩ ጀምስ ሮበርት በሰባቱ አገሮች ዜጎች ላይ የተጣለው የጉዞ እግድ በዋሽንግተን ክልል ብቻ ሳይሆን በአሜሪካን በሙሉ እንዳይተገበር የሚል ብይን ይሰጣሉ። የእግድ እግድ መሆኑ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጻዕረ ሞትና መስፍን ወልደማርያም

የአንባብያን ድምፅ: 4 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Inactive

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

Mesfin Woldemariam

አንደኛ፣ ገና በልጅነቴ አሥር ዓመት ግድም ሲሆነኝ አንድ በድቀድቂት ከእንጦጦ ወደታች የሚወርድ ኢጣልያዊና እኔ ተጋጠምን፤ እሱ በዚያ በጥቁር ድንጋይ ኮረት በረበረበበት መንገድ ላይ ሲጓዝ ወደእንጦጦ የሚወጣ ወታደሮችን የጫነ ከባድ መኪና ቆሞ ነበር። በዚያ መኪና ላይ አንድ ዝንጀሮ ነበር፤ የኔ አትኩሮት በዚህ ዝንጀሮ ላይ ነበር። እንደሚመስለኝ ዝንጀሮውን እያየሁ ስሮጥ ከድቅድቂቱ ጋር ተገናኘን፤ እኔ ከስር በተረበረበው የጥቁር ድንጋይ ኮረት ላይ፣ ድቅድቂቱ ደግሞ የእኔን ራስ ጨፍልቆ! ምኒልክ ሐኪም ቤት ከስንት ቀኖች በኋላ የካቶሊክ መነኮሳት አስታማሚዎች ከነመለዮአቸው አልጋዬ አጠገብ ቆመው በትልቅ የበሽተኞች ድንኳን ውስጥ በአንዱ መደዳ ውስጥ ተኝቼ ነቃሁ፤ መድኃኔዓለም ማንን ልኮ የእኔን ጭንቅላት ከድንጋዩና ከድቅድቂቱ መክቶ እንዳዳነኝ አላውቅም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቦይ ስብሃት ነጋ የሙስና ወጎች

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ክንፉ አሰፋ

Sebhat Nega

በአሜሪካ አገር፤ አንድ ባለሥልጣን በሙስና ሲባልግ እስር ቤት ይገባል። በፊሊፒንስ አገር አንድ ባልሥልጣን የሙስና ወንጀል ቢፈጽም አሜሪካ ይገባል። የኛ አገር ባለግዜ ግን ሙስና ሲሰራ አሜሪካ እየተመላለሰ ይነግዳል። ለግዜው ልዩነቱ የዚህን ያህል ነው። ገለልተኛ የፍትህ አካል ባለበት አገር፤ ሙስና አፍ አውጥቶ አይናገርም፣ እግር አውጥቶም አይራመድም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እንኳን ለገና አደረሰን!

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Assefa Chaboአሰፋ ጫቦ (Dallas Texas USA)

የፈረንጅ ገና ዋዜማ ዕለት በሆንኩት ልጀምር። ሁለት ወዳጆቼ፤ አንደኛው ከዚሁ ከቨርጂኒያ፤ ሌላው ከሳሳከችዋን፤ ካናዳ ደውሎ ስለበዓሉ ትንሽ ተነጋገርን። እነሱም የሚሰማቸውን እኔም የሚሰማን ያዝ ለቀቅ አደርገነው። “ዞሮ ዞሮ ከቤት!” እንዲሉ ያው ሁሌም ሚዛኑ የኢትዮጵያ ዓመት በዓላት ናቸው። “ባሻ አሸብር ባሜሪካ” መሆንናችን መሰለኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት አቤቱታ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Temesgen Desalegne and his mother

ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የልጄ የተመስገን ደሳለኝን ጤንነትና የጉብኝት ሁኔታን ስለማወቅ

የልጄ ተመስገን ደሳለኝን ጉዳይ ይዤ እናንተው ጋር መመላለስ የግድ ሆኖብኝ ዛሬም ከደጃችሁ መጥቻለሁ። ባሕሌና አስተዳደጌ ያስተማረኝ፤ አንድ ቦታ ለአንድ ጉዳይ መመላለስ ለችግሩ ባለቤትም ሆነ ለመፍትሔ ሰጭው አሰልቺ መሆኑን ነው። እውነት ለመናገር ዛሬም ወደ በራፋችሁ ስመጣ እንደው እነዚህን ሰዎች ሥራ እያስፈታኋቸው ይሆን ከሚል ሃፍረት ጋር ነው። ግን ምን ላድርግ? ጉዳዩ ልጅን የሚያኽል የስጋ ክፋይ ነገር ሆነብኝ። እንድትረዱልኝ የምፈልገው እኔም ተቸግሬ እያስቸገርኳችሁ መሆኑን ነው። በተጨማሪም ጭንቀት እረፍት ስላሳጣኝና ጤናዬንም እየፈተነኝ በመሆኑ የመፍትሔ ያለህ እያልኩ አለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!