የቦይ ስካውት ትዝታዬ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

Boy Scout ቦይ ስካውትአበራ ለማ
"አስካውት! ..."
"ምን ጊዜም ዝግጁ!!!"
ዱሮ ዱሮና በኛም ዘመን የቦይ ስካውት ክለብ (Boy Scout) እንቅስቃሴ ሞቅና ደመቅ ያለ ነበር። ሰላሌ ፍቼ፣ የአበራና አስፋው ወሰን የ1ኛ ደረጃና ወሊሶ የደጃዘማች ገረሱ ዱኪ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ እያለሁ (ከ1953-1960 ዓ.ም.) የቦይ ስካውት ክለብ አባል ነበርኩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አመፀኛው ነፋስ (በልጅግ ዓሊ)

Star InactiveStar InactiveStar InactiveStar InactiveStar Inactive

በልጅግ ዓሊ

"ባሰላው ባሰላው እንቢ አለኝ እንዝርቱ፣
ከታችም አይደለ ከላይ ነው ጥመቱ።"
የጎንደር ሕዝብ እንጉርጉሮ

ኦክቶበር 28 እንደ ሀገሩ አቆጣጠር ጠዋት ጉልበተኛ ነፋስ ከባሕር ተነስቶ በደቡብ እንግሊዝ በኩል አድርጎ እያቆራረጠ ወደ ሰሜን ተፈተለከ። የባሕሩ ሠይጣን የላከውን ጉልበተኛውን ነፋስ የፈራው አዳሜ ፈረንጅ ሁሉ ተርበትብቶ እኛንም በሬዲዮንና በቴሌቪዚዮን ሲያርበተብተን ሰነበተ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቴዲ የኳስ ሜዳ ልጅ ነው

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ሄኖክ የሽጥላ (ገጣሚ)

ከምን ልጀምር? እንደው ይጨንቃል፤ ደሞ ዝም ቢሉት ያንቃል። አሁን ይሄን የምጥፈው ለማስተማር ነው ለማካረር? በልጅነቴ አንድ አብሮ አደጌ በጣም የሚወዳቸው እናቱና አባቱ እየተጋጩ ቢያስቸግሩት፣ ሄኒ አሁን አንተ በኔ ቦታ ብትሆን ማንን ትጠላለህ? ብሎ የጠየቀኝ ትዝ አለኝ። ማንን ልጥላ? ለማን አግዤስ ማንን ላውግዝ? ማንንስ ልውቀስ? ማንንስ ልጥቀስ? ሲደብር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በ19 ዓመቴ ወልጄው፣ ጠፍቶ፣ ሞቷል ያልኩትን ልጄን አገኘሁት

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

ዶ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ Dr. Fikre Tolossa ፍቅሬ ቶሎሳ ጅግሳ (ዶ/ር)

ውድ አንባብያን ሆይ! የምሥራች! የምሥራች ስላችሁም በሀገራችን ባህል አጸፋውን "ምስር ብላ!" በሉኝ። ልቤን ወደ ሰማይ እያዘለለ፣ እግሮቼን ጮቤ የሚያስመታ ነገር ሰሞኑን ገጥሞኛልና። እሱውም ከአያሌ ከዘመናት በፊት ዕድሜዬ 19 ሳለ የወለድኩት ልጄ፣ ያውም የበኹር ልጄ፣ ጠፍቶብኝ "በቃ! ሞቷል፣ ተከቷል!" ብዬ እርሜን አውጥቼ እያዘንኩ እኖር ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጎዳና ተዳዳሪው የወታደራዊ ደህንነትና መረጃ መኮንን ኮሎኔል ካሣሁን ትርፌ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

የጎዳና ተዳዳሪው የወታደራዊ ደህንነትና መረጃ መኮንን ኮሎኔል ካሣሁን ትርፌ

ፍቅር ለይኩን

እንደ አለመታደል ሆኖ ከቅርብ የታሪካችን ዘመን እንኳን ብንነሳ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ የሆነ፣ ብሔራዊ ስሜት ያለው፣ ጠንካራ የሆነ ሕዝባዊ መሠረት ያለው የመከላከያ ኃይል ለመፍጠር እየተደረገ የነበረውና አሁንም እያየነው ያለው ሙከራ መንግሥት በተለዋወጠ ቁጥር ሂደቱ እየተገታ ከዚህ ደርሰናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ደሳለኝ ደበረኝ ደሳለኝ

የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5

Star ActiveStar ActiveStar ActiveStar ActiveStar Active

አባጅፋር

ፊት ላይ ያሉት ቀዳዶች የተበጁት ለመተንፍሰ፣ ለመብላት፣ ለመናገርና ለመናፈጥ ነው። እንዳስፈላጊነታቸው እንጠቀመባቸዋለን። በዚህም ምክንያት ሰውየው ተናገሩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ