“ከሀገር በስተጀርባ” (ገሠሠ እንግዳ)

ከሀገር በስተጀርባገሠሠ እንግዳ

በኢትዮጵያ በህይወቴ ዘመን ሦስቱን ሥርዓቶች ማለት የዓፄ ኃይለሥላሴ፣ የኰለኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም እና የመለስ ዜናዊ መንግሥታት መልካቸው ብቻ ሳይሆን ተግባራቸውንም ጭምር ለማስተዋል ከበቁት ሰዎች ውስጥ አንዱ ነኝ። በተለይም በሀገራችን ለውጥ ለማምጣት “ዳቦ ለተራበ”፣ ”መሬት ላራሹ” የሚል ህያው መፈክር ይዞው “አትነሳም ወይ የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ?!” እያሉ በአደባባይ ወጥተው ይጮኹ ከነበሩት ተማሪዎች አንዱ ሁኘ ብዙ ውጣ ውረድ አልፈው እዚህ ከደረሱት ትውልድ አንዱ ነኝ። የወጣቱ አስራት አብርሃምን መጽሐፍ ሳነብ የቀሰቀሰብኝ ትዝታም ያ ያሳለፍኩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች እንቅስቃሴ የእሳትነት ዘመኔ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ነፃነትና ዳኝነት በኢትዮጵያ” - በስየ አብርሃ

“Freedom & Justice in Ethiopia” - By Siye Abrahaእንደ ግምገማ - ኩችዬ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.

“መጽሐፍ!” ሲሉት ሰፍ የሚል ከራማ ቢጤ አለብኝ መሰል ስየ አብርሃ ደረሱ የተባለው መድብል እጄ እስኪገባ ቸኩዬ ነበር። ባገራችን የቅርብ ዘመን ታሪክ ላይ አሻራቸውን ካተሙት ጥቂት ስዎች መሀል ናቸውና እኒህ ሰው የሚሉትን ለማወቅ ብተጋ አይፈረድኝም። ጀመርሁ የሚሉት የሁለተኛው ምዕራፍ ጉዟቸው የምንፈልገው ዓይነት መሆኑን የሚያመላክቱ ፍንጮች ያዘለ ሊሆን ስለሚችልም መጽሐፉን ለማንበብ በቂ ምክንያት ያለ መሰለኝ። ላወቀበት በመስመሮቹ መሀል የተሰነጉትን ሁሉ መመርመር ነው።  ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተስፋዬ ገብረአብ እና ሁለቱ ዝሆኖች

Yederasiw Mastawesha, የደራሲው ማስታወሻእጅጋየሁ አወቀ

”... ደራሲ ተስፋዬ ራሴን ነፃ አውጥቻለሁ የሚሉትን የቀድሞ የፖለቲካ ድርጅታቸውን በመደገፍ ተቃዋሚውን፤ በተለይም በአሰብ ጉዳይ ላይ ከመለስ የተለየ አቋም የወሰዱትን ቢታገሉ፤ እየሠሩ ያሉት ”ሀገሬ” ለሚሏት ለኢትዮጵያ ወይስ ለእናታ ሀገራቸው ለኤርትራ? ልብ በሉ፣ በአሰብ ላይና የአልጀርሱን ስምምነትና የሔጉን ውሳኔ ውድቅ እናደርጋለን በሚሉት የአንድነት/መድረክ አመራር አባላት ላይ ሰፊ ዘመቻ እያካሄዱ ሲሆን፣ የአሰብን ጉዳይ አታንሱብኝ እያለ የአልጀርሱን ስምምነት ፈርሞ ያፀደቀውንና የሔጉንም ፍ/ቤት ውሳኔ ለተቀበለው ለጠ/ሚ መለስ ቡድን የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ በመስጠት ላይ ናቸው። ታዲያ አቶ ተስፋዬ ማን ናቸው? የኢትዮጵያ ወይስ የኤርትራ ጥቅም አስከባሪ ፕሮፓጋንዲስት? ...” ሙሉውን አስነብበኝ ...

የደራሲው ማስታወሻ - የመጽሐፍ አቃቂር

Yederasiw Mastawesha የደራሲው ማስታወሻተስፋዬ ዮሐንስ

... ተስፋዬ ‘የባርነት’ ዘመኑን በመቃኘት ያሳለፈውን ህይወት፣ ገጠመኙን፣ የታዘባቸውን፣ ወዘተ፣ በጭልፋ እየቆነጠረ ያቋድስ ጀመር። ‘የጋዜጠኛው ማስታወሻ’ የተባለውን መጽሐፍ ደርሶ ለንባብ አበቃ። ብዙዎች አበጀህ፣ ደግ አደረግ አሉት። ቀጣፊ ያሉትም ነበሩ። ኤርትራዊ የዘር ሃረጉን በመቁጠር የሻዕቢያ ደጋፊ ያሉትም አልጠፉም። በተለይ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና አባላት፣ ገበና አጋለጠ በማለት ብዙ ጽፈውበታል። ሙሉ በሙሉ ከባርነት በወጣበት ‘የጋዜጠኛው ማስታወሻ’ መጽሐፉ ላይ የብዙ ሰዎች ስሞች ተነስቶ ተስፋዬ ከበድ ከበድ ያሉ ክሶችና ውንጀላዎች ደረድሮአል። አንዳቸውም አላስተባበሉም። ለምን? ... ከአንድ ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ፣ ተስፋዬ ሌላ መጽሐፍ ደርሶ ለንባብ አብቅቷል፤ ‘የደራሲው ማስታወሻ’። መጽሐፉ 25 ራሳቸውን የቻሉ ክፍሎች አሉት። ይህ አቃቂር በሦስት ዐብይት ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። 1/ መጽሐፉን መድረስ ለምን አስፈለገ? 2/ መጽሐፉ ያቀፋቸው ዋና ዋና ጭብጦች ምንድናቸው? 3/ የመጽሐፉ ደካማ ጎኖችስ? ... ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምላሽ ለየደራሲው ማስታወሻ

Yederasiw Mastawesha የደራሲው ማስታወሻመድረኩ ካልተደገፈ፤ ማን ነው የሚደገፈው?

ግርማ ካሣ ( This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. ) ሚያዝያ 16 ቀን 2002 ዓ.ም.

“… “ከቁጥጥራችን ውጭ የማይሄድ ፌደራሊዝምና የምርጫ ሂደት ከተከተልን ለረጅም ጊዜ ትግራይን ሥልጣን ላይ ማቆየት ይቻላል” ይላሉ እነ መለስ። ስየ ከመነሻውም ይህን ይቃወማል። በዚህ ዘዴ ለረጅም ጊዜ መዝለቅ አንችልም ባይ ነው። አማራው እስከዛሬ እንደተጠቀመበት ኢትዮጵያዊነት የሚለውን በሽፋን ተጠቅመን ውስጥ ውስጡን ግን የትግራይ ተወላጆችን በሀብትና በእውቀት በማጠናከር ለረጅም ጊዜ ልንገዛ እንችላለን። አፄ ዮሐንስ ያደጉትን አንደግምም፤ ሥልጣን ከእጃችን ከወጣች ተመልሶ ማግኘት ከባድ ነው“ ይላል ስየ …»

ተስፋዬ ገብረአብ - ከየደራሲው ማስታወሻ ላይ የተወሰደ ሙሉውን አስነብበኝ ...

አቶ ተስፋዬ ገብረአብ ኢትዮጵያዊነትን ለምን ፈለጉት?

Yederasiw Mastawesha የደራሲው ማስታወሻከንስረ ኢትዮጵያ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.)

አቶ ተስፋዬ ገብረአብ በደራሲነት ሙያ መተዳደር ከጀመሩ ሰንብተዋል። ከሙያ በላቀ መልኩ መተዳደሪያነቱን አጥብቀው በመያዛቸው ቢመችም ባይመችም የተለያዩ ጽሑፎች ወይም መጻሕፍት አበርክተዋል። ብልጥ የግዜውን ሁኔታ የሚያዩ ጎበዝም ናቸው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከመጻሕፍት አምባ (አበራ ለማ)

የመጽሐፉ ርዕስ - የወገን ጦር ትዝታዬ

ደራሲ - ማሞ ለማ (ሻለቃ)

አሣታሚ - ሻማ ቡክስ

አታሚ - የተባበሩት አታሚዎች አ.አ. ኢትዮጵያ

የገፅ ብዛት - 497

የታተመበት ዓመት - 2001 ዓ.ም.

ዋጋው - ያልተመለከተ

ሂሳዊ ንባብ - አበራ ለማ

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አባቴ ያቺን ሰዓት (አዲስ መጽሐፍ)

Abaté Yachin Seat አባቴ ያቺን ሰዓትፀሐፊ - ደረጀ ደምሴ

ቋንቋ - አማርኛ

አሣታሚና አከፋፋይ - Aesop Publishers & Distributors

ዋጋ - 25 የአሜሪካ ዶላር

“አባቴ ያቺን ሰዓት” በደረጀ ደምሴ የተጻፈና በቅርቡ በገበያ ላይ የዋለ አዲስ መጽሐፍ ነው። የመጽሐፉ ፀሐፊ ደረጀ ደምሴ ስለ አባቱ ሜ/ጄ ደምሴ ቡልቶ፣ በኢትዮጵያ ሠራዊት ውስጥ በአመራር ላይ ስለነበሩት ከፍተኛ መኮንኖች፤ እንዲሁም ስለ ግንቦት 81 መፈንቅለ መንግስት የጻፈው አዲስ መጽሐፍ ነው። ደረጀ ከአባቱ ጋር በተለያዩ ቦታዎች እየተዘዋወረ ያየውን እና በቦታው ከነበሩ የተለያዩ ከፍተኛ መኮንኖች ያጠናቀረውን፤ በጣፋጭ ትረካ አቅርቦታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወገን ጦር ትዝታዬ

Yewegene Tore Tizetaye, የወገን ጦር ትዝታዬ በኢትዮጵያ ዛሬ ዘጋቢ

”... ”የወገን ጦር ትዝታዬ” የተሰኘው ይሄ መጽሐፍ የደርግን የ17 ዓመት ታሪክ ለማወቅ የሚሹ በሙሉ ሊያነቡት፣ ሊመረምሩት፣ ለትውልድ ሊያሳልፉት የሚገባ መጽሐፍ ነው ብዬ አምናለሁ። ስለደርግ ብዙም መጻሕፍት አልተፃፉም፤ በተለይም በደርግ አባላትና በወቅቱ በከፍተኛ ሥልጣን ላይ የነበሩ ግለሰቦች የሚያውቁትን ታሪክ ለትውልድ አላካፈሉም። ...”

ሙሉውን አስነብበኝ ...