የወቅቱ የአገራችን የፖለቲካ ሁኔታና የወደፊት የትግል አቅጣጫ

ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ Dr. Negasso Gidadaዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ (የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር)

መግቢያ

የሁላችንም የረጅም ጊዜ ህልም፣ አንድነትዋ የተጠበቀ የበለፀገች ኢትዮጵያን ማየት ነው። ወደዚያ ለመድረስ ሁሉም ኢትዮጵያውያን አስተዋጽኦአቸውን የሚያበረክቱበት ለአገሬ እሠራለሁ ብለው በነፃ አየር የሚተነፍሱበት ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ምህዳር እንዲፈጠር ካሁኑ ጀምረው እንዲታገሉ ሁኔታን መመቻቸት ይፈልጋሉ። ስለዚህም የፖለቲካ ምህዳሩን ማየትና ወዳለምነው ግብ ለመድረስ የሚረዱንን አቅጣጫዎች መዳሰሱ ጠቃሚ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሐውልት የሚያለማውስ?

ከድሜጥሮስ ብርቁ - ቶሮንቶ

የዳግማዊ ምንሊክ አና የአቡነ ጴጥሮስ መታሰቢያ ሃውልቶችን ከስፍራቸው ለማንሳት ዝግጂቱ አንደተጠናቀቀ ስሰማ አሁን በስልጣን ላይ ያለው የህወሃት ቡድን በትክክልም የ”መለስን ራዕይ”ለማስፈጸም ደፋ ቀና አያለ አንደሆነ ተረዳሁኝ። ከዚህ በፊት በሌላ ፅሁፍ አንደገለጽኩት የ”መለስ  ራዕይ” የሚባል ነገር አንደሌለ እና የመለስ አየተባለ ለመሸጥ የሚሞክረው “ራዕይ” በትክክል የህወሃት ለመሆኑ አመላክቻለሁ። ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲወር የነበረው የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ “ሃገሪቱን አሰለጥናለሁ” የሚል ነበር። አስቡት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ጉዳይ ወዝውዞት ከጣልያን ሃገር ድረስ ጦር ሰብቆ ሲመጣ። አቡነ ጴጥሮስ በግፍ ሃውልታቸው የቆመበት ቦታ ላይ የተገደሉትም ዛሬ ህወሃት በሚጠቀመው ቋንቋ ሲመነዘር “ጸረ-ልማት” ናቸው በሚል ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሁለት ሐውልቶች ዕጣ

የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልትየዐፄ ምኒሊክ ሐውልትዳንኤል ክብረት

ሰሞኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ የመነጋገርያ አጀንዳ የሆነ አንድ ጉዳይ አለ። የአቡነ ጴጥሮስና የምኒሊክ ሐውልትና የባቡሩ መሥመር ያላቸው ዝምድና። ስለ ባቡር በመዝፈን ከመቶ ዓመት በላይ ያሳለፍን ሕዝቦች የከተማ ባቡር ማግኘታችንን በዕልልታ የምንቀበለው ነገር ነው። ዘግይተን ይሆናል እንጂ አልቸኮልንም። ሥራው በቁርጠኝነት መጀመሩና ከወሬ አልፎ ሲተገበር ማየታችንም እሰዬው የሚያሰኝ ሆኗል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ‘ትግላችን’ አሣር

ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም Mengistu Hailemariamዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ከደቂቃዎች በፊት የኤልያስ ወንድሙን የኢሣት ቃለ ምልልስ እየተከታተልኩ ነበር። ያን ቃለ መጠይቅ እንዳገባደድኩ ኤልያስ የሚመራው የፀሐይ አሣታሚ ድርጅት እስካሁን ካሣተማቸው 60 ያህል መጻሕፍት ለየትኞቹ ይበልጥ ክብደት እንደሚሰጥ ሲጠየቅ ከጠቆማቸው ሥራዎች መካከል በሁለተኛነት የጠቀሰው የቀድሞውን መሪ የኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማርያምን (ባሉበት ሰላምታዬ ይድረሳቸው) “ትግላችን” የሚል መጽሐፍ ነበርና ጀማምሬው ሳበቃ ሁሉንም ሳላነብ ዴስክቶፕ ላይ ያኖርኩት ይሄው መጽሐፍ ትዝ አለኝ። ከጅምሩ እንደገና ላነበው ፈቀድኩናም ወደንባብ ክፍል አመራሁ። ግን እውነት ልናገርና ሸከከኝ፤ ዱሮውንም ሸክኮኝ ነበር ሳልጨርስ የተውኩት። እናገራለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አስታውሳለሁ! እንዴት እረሳለሁ!!

በፍፁም አይደገምም! Never Again!ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)

በሰኔ 6-8 እና በህዳር 1-4 2005 (እ.ኤ.አ.) በግንቦት 2005 የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ ኢህአዴግ ያወጣውን ሕገ መንግሥት በማመን ባዶ እጃቸውን ወደ አደባባይ የወጡ ንጹሃን ወንዶች፤ ሴቶች፤ ሕጻናት ኢትዮጵያዊያን በቅርቡ ሕይወታቸው ባለፈው በመለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትእዛዝና ቁጥጥር ሕይወታቸው በአሰቃቂ ሁኔታ በጥይት ተደብድበው ተገድለዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የህወሓት ምስለ-ወራሪነት ሚና በኢትዮጵያ

The TPLF Empire, የህወሓት ምስለ-ወራሪነት ሚና በኢትዮጵያዳዊት ፋንታ

አዜብ መስፍን በቅርቡ ለዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከል የሰጠችውን መግለጫ ተከትሎ በመገናኛ ብዙኃን ልክ እንደ አዲስ ከየአቅጣጫው ውግዘት ደርሶባታል። ምናልባትም ውግዘቱ ለ21 አመታት በህወሓት በኩል ሲሰራበት የኖረውንና ሊሰራ የታቀደውን እሷ በቃላት በመግለጿ ይሆን እንደሆነ እንጂ በተግባር የሚታየው የህወሓት ምስለ-ወራሪነት ሚና ያው በነበረው አካሄድ መጠኑን እያሰፋ ከመሄድ በዘለለ የተለየ እንግዳ የሆነ ነገር አልታየበትም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሕዝብ ራዕይ ለምን በአምባገነን ስም ይጠራል?

የኢትዮጵያ ሲቪክ ንቅናቄ

አቶ ኃይለማርያም ”የታላቁን መሪ ራዕይ“ እንደሚተገብሩ ቃል ገብተዋል፤ ለውጥ እንደሚያደርጉ ግን አልገለፁም። ኢህአዴግ በአቶ መለስ ፍላጎት ብቻ ይመራ፣ የኢትዮጵያ ህዝብም በሰውየው ፍላጎት ይገዛ ነበር። ከዛ ፍላጎት ማፈንገጥ ለግምገማ ያጋልጥና በጠላትነት ያስፈርጅ ነበር። ያገዛዙ ጠባይ በድርጅቱ አባላትም አለመተማመንን አስርፆና አስፍኖ፣ አባላቱ በግልፅ ሃሳባቸውን እንዳይገልፁ አፍኖ ስለቆየ ኢህአዴግ ከአቶ መለስ ሞት በሁዋላም እስካሁን የሚመራው በሟቹ መንፈስ ነው። አባላቱ ከአፋኙ ባህል ገና አልተላቀቁም። ስለዚህ የአቶ ኃይለማርያም ንግግር የተጀመረውን መቀጠል ከሚለው ሃሳብ አለመውጣቱ ለጊዜው አያስገርምም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እኛም ሁላችንም “አበበ በቀለ” ነን!

አበበ በቀለ

ባለፉት ጥቂት ወራት ውስጥ ሦስት ነገሮችን በጥልቀት ብዙ ሳሰላስል ነበር። በመጀመሪያ የከነከነኝ ነገር አንዲት አቢጌል የምትባል የአራት ዓመት ሕፃን ስለ “ብሮንኮ ባማ እና ሚት ራምኒ” በሬዲዮ መስማት እንደሰለቻት ለእናቷ ስቅስቅ ብላ እያለቀሰች ስትናገር ማየቴ ነው። የዚህች ሕፃን ቪድዮ በዩቱብ ከ16 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ አይቶታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፕሬዝዳንት ኦባማ በሁለተኛውን ዙር ምርጫ ምን ይጠበቅባቸዋል

Presidant Barack Obama ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ፕሬዝዳንት ኦባማ ሁለተኛውን ዙር የፕሬዝዳንትነት ምርጫ በማሸነፋቸው እንኳን ደስ ያለዎት ማለቱ አግባብ ነው። የአሜሪካንን መራጮች አብላጫ ድምጽ አግኝቶ ለማሸነፍ ብቃት ባለው አካሄድ ለድል በቅተዋል። ሚት ሮምኒም ለማይናቀው የምርጫ ግብግባቸው ሊመሰገኑ ተገቢ ነው። በማጠቃለያው የመለያያ ንግግራቸው ላይ ሚት ሩምኒ ግሩም የሆነ መልእክት አስተላልፈዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእብዶቹ መንግስትና ሕገ-መንግስታቸው

ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)

ያለፈው የወያኔ መሪ ባለቤት ወይዘሮ አዜብ መስፍን ትግራይን የኢንዱስትሪ ማእከል ለማድረግ መለስ ዜናዊ አቅዶት የነበረውን፤ ጽፎ ጽፎ ያስቀመጠውን ህልሙን ተግባር ላይ ለማዋል መንቀሳቀስ እንደምትጀምር በቅርቡ በይፋ አውጃለች። ይህ ሰው የኢትዮጵያ መሪ ይባል የነበረ ነው። ለምንድነው ከኢትዮጵያ ህዝብ ደብቆ ለትግራይ ብቻ ያን ሁሉ ራዕይ አልሞ፤ አቅዶ፤ ነድፎ እንዲፈጸም አደራ ብሎ የነበረው? ለሚለው ጥያቄ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የራሱን መልስ ይስጥ።ወይዘሮዋ ይህንን ተልኮ የምትፈጽመው ኢፈርት የሚባለውን የንግድ ድርጅት በመምራት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ