ዋሊያ፣ ቀይ ቀበሮና ሊሲዎች በርቱ ተበራቱ!

Ethiopian soccer team for the 3rd African cupበአውሮፓ የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን

እግር ኳስ በሀገራችን ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ1924 ዓ.ም. አዲስ አበባ ውስጥ ይኖሩ በነበሩ የውጭ ሀገር ተወላጆች (ፈረንጆች) የተጀመረ ሲሆን፣ ምንም እንኳን በአለም አቀፍ ደረጃ በመዝገብ ሠፍሮ ባይገኝም በ1935 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ ከጅቡቲ ጋር ግጥሚያ ተደርጎ እንደነበረ ‘History of Ethiopian Soccer’ በሚል የተጻፈ ታሪክ ያስረዳል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የቤት ልማቱ እና ሦስቱ ኢንቁፍቱ

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

በመጀመሪያ

በዘመነ ትምክህተኞችና ጠባቦች አንድ ቁስለኛ ሰው ነበረ። ይህ፣ በአድኃሪነት የተወጠረ የመሬትና የቤት ከበርቴ ድንገት ጋሬጣ ወግቶት ቅልጥሙ ቆሰለ። ያንንም ቁስል ንቆት ኖሮ፣ እያደር እያመረቀዘ ሄደና ደህና የዝንብ መሰብሰቢያ ቤት ወጣው። መጀመሪያ ላይ ንፍፊቱ፣ ቀጥሎ ግን መገረኑ ሰውዬውን አላስኬድ አላራምድ አለው። በየት በኩል ይላወስ። እግር ተወርች አሳሰረው። እቤቱ ዋለ። ዝንቡን እሽሽ ሲል ለመዋልም ተገደደ። የኋላ ኋላ ግን፣ ዝንቦቹን እሽሽ ማለቱንም ተወው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አምባሳደር ተወልደ ከፓርቲው ለቀቁ

Ambassador Tewelde Gebru አምባሳደር ተወልደ ገብሩ ኢየሩሳሌም አርኣያ

የህወሓት ማ/ኰሚቴ አምባሳደር ተወልደ ገብሩ (በቅጽል ስማቸው ተወልደ አጋሜ) በገዛ ፈቃዳቸው ከፓርቲው እንደለቀቁ ምንጮች አረጋገጡ። ባለፈው በተካሔደው የፓርቲው ጉባኤ ላይ የመልቀቂያ ጥያቄ አቅርበው ከማ/ኰሚቴ አባልነት እራሳቸውን እንዳገለሉ አስታውቀዋል። በአምባሳደርነት ሲያገለግሉ የቆዩት ተወልደ «አጋሜ» ከ1993 ዓ.ም. በኋላ ተዛውረው በአትሌቲክስ ፌዴረሽን ያለሙያቸው ተመድበው ቆይተዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትንሽ ወግ ስለደምሴ ዳምጤ

አያልቅበት አደም

የደምሴን መታመም ከሰማሁ ወዲህ ያደረበት የስኳር ሕመም (ዲያቤቲክስ) የዓይኑን ብርሐን ከማሣጣት በዘለለ ይህን ያህል ለሕይወቱ ያሰጋል ብዬ አልገመትሁም። ለመጀመሪያ ሕክምና ወደ ባንኮክ ተጉዞ ሲመለስ የአንደኛው ዓይኑ ብርሐን ማጣት አስከፊ ዜና ቢኖርም የቀኝ ዓይኑ ብርሐን ወደ 20 ከመቶ የተመለሰ መሆኑንና ሊሻሻል እንደሚችል በመስማቴ ተመስገን ብያለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊው ዑሴይን ቦልት የራሱን ሪከርድ አሻሻለ

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ለለውጥ ያህል ለምን አንባቢን ፈገግ ልታደርግ በምትችል የአዲስ አበባ ዘመነኛ ቀልድ አልጀምርም? ... አንድ የወያኔ ከፍተኛ ባለሥልጣን በዋቢ ሸበሌ ሆቴል ሲዝናና ያመሻል። ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት አካባቢ ሲሆን ወደቤቱ ሊሄድ ቄንጠኛ ፕራዶ መኪናውን ሊያስነሳ ቢሞክር ያልታሰበ ብልሽት ያጋጥመውና ሞተሩ ለመነሣት እምቢዬው ይለዋል። ቢለው፣ ቢለው አልሆነለትም። ከዚያም ሌላ ምርጫ ሲያጣ ላዳ ታክሲ ያስጠራና ወደቤቱ እንዲያደርሰው ሹፌሩን ይጠይቀዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግ ስንት ቦታ ሊሰነጠቅ ይችላል?

ከተመስገን ደሳለኝ

ብርዱ የጥቅምት ነው፤ አጥንት ድረስ ዘልቆ የሚያንቀጠቅጥ ኃይለኛ ቅዝቃዜ። አዲስ አበባ ገና ከእንቅልፏ በመንቃት ላይ ነች። ለስራ የቸኮሉ መንገደኞች ትራንስፖርት ፍለጋ ወዲያ ወዲህ ይካለባሉ። ማክሰኞ ጥቅምት 7 ቀን 2005 ዓ.ም. ከጠዋቱ 12 ሰዓት ከ50 ደቂቃ ላይ ብስራተ ገብርኤል አደባባይ ‹‹መገናኛ ራዲዮ›› በያዙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋለ። የትራፊክ ፖሊሶቹ ስራ የበዛባቸው ይመስላሉ። 12 ሰዓት ከ55 ደቂቃ ሲል በሁለት የሞተር ብስክሌት በተፈናጠጡ የትራፊክ ፖሊሶች ፊት አውራሪነት አንዲት ሳይረን የተገጠመላት የፖሊስ ታርጋ የለጠፈች መኪና የ‹‹መንገድ ልቀቁልኝ›› ጩኸቷን እያንባረቀች አቋርጣ በማለፍ ወደ ሳር ቤት አቅጣጫ ከነፈች። ሶስት ‹‹ቪኤት›› መኪና ሰለሱ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእንክርዳድ ውርስ

(ክፍል ፩) ዳዊት ፋንታ

በረከት ስምኦን “የሁለት ምርጫዎች ወግ`` የተሰኘ መፅሐፉን በሸራተን አዲስ ሲያስመርቅ ´´አሮጌዋ ኢትዮጵያ እየፈራረሰች በአዲሷ ኢትዮጵያ እየተተካች …" እያለ ተናግሮ ነበር።በእርግጥ በሌላ በኩል ´´ሀገር ማለት ብሄር ብሄረሰቦች እንጂ ወንዝና ተራራው አይደለም፥የግዛት አንድነት ጉዳይ የነፍጠኝነት ጉዳይ ነው´´ እያሉ የወያኔ ርዕሳን ሲናገሩ መስማቱንም ለምደነዋል። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አንድ ማስታወሻ ለጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ

ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ, Journalist Demissie Damteመስፍን ነጋሽ

በእኔ እድሜ የደምሴን ያህል አገራዊ የስፖርት ስሜትን፣ በተለይ እግር ኳስን ወደ ልባችን ያቀረበ ጋዜጠኛ አልነበረም። እንደዛሬው ኢንተርኔት መገልበጥ ማእረግ በማያሰጥበት ዘመን። በሳምንት ሁለትና ሦስት ቀን ስታዲየም በምገባበት፣ ሁለቱን ሙሉጌታዎች፣ እነሚሊዮን በጋሻውን፣ እነቸርኬን (ጊዮርጊስ)፣ እነሙሉዓለም እጅጉን (ጦሩ)፣ እነአብዲን (መድን)፣ እነአፈወርቅን (እርሻ)፣ ያ ደሞ የአየር ኀይሉ አጥቂ ማን ነበር? ... ረሳሁት ማለት ነው? (ይልቅ ተከላካያቸው መሰለ፣ ጆን ቴሪን ቁጭ ነበር)፣ ከዛ ደሞ ... ይህ ሁሉ ሲሆን ብቸኛው የስፖርት መረጃ ምንጫችን ደምሴ ነበር፤ እርግጥ ሌሎችም ጋዜጠኞች ነበሩ በተለይ እነ ... ማነው ... ይንበርበሩ መሰለኝ። ቢሆንም ደምሴ የተለየ መስህብ ነበረው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የብሔራዊ ስሜት - አብነት!

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው DC-6 B አይሮፕላን፣ Ethiopian Airlines DC-6 Bሰሎሞን ተሰማ ጂ.

ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነውን DC-6 B አይሮፕላን፣ መስከረም 3 ቀን 1962 ዓ.ም. በሶሪያ የወንበዴዎች ቡድን (ጀብሃን ለማለት ነው) ተገድዶ ኤደን ባረፈ ጊዜ፣ የመንገደኞቹን ሕይወትና አይሮፕላኑንም ከቃጠሎ ያዳነው ም/አለቃ ካሳዬ ታደሰን የያዘው አይሮፕላን ከድሬዳዋ አዲስ አበባ፣ ትናንት ጥቅምት 3 ቀን 1962 ዓ.ም በዘጠኝ ሰዓት ተኩል ገብቷል። ቀድሞ በምድር ጦር ውስጥ ምክትል የአስር አለቃ የነበረውና አሁን በሲቪል አቪዬሽን ውስጥ የበረራ ደኅንነት ኢንስፔክተር የሆነው ካሳዬ ታደሰ ከቦሌ አይሮፕላን ማረፊያ በቀጥታ ወደ ኢዮቤልዩ ቤተ መንግሥት ኼዶ፣ ግርማዊ ንጉሠ ነገሥት ዘንድ ቀርቧል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ