ይህ ሁሉ ለአንድ ሰው

ኤፍሬም እሸቴ

ባለፈው ዓመት በአንዱ እሑድ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኔ አንድ የክርስትና ዝግጅት ነበር። በአካባቢያችን ከሚኖሩት ክርስቲያኖች አንዷ ልጃቸውን ለማስጠመቅ መጥተው ነበር። እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ካህናቱ ከቅዳሴው አስቀድመው ለሕጻኑ መደረግ ያለበትን ሥርዓተ ጸሎት ያደርሱ ገቡ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከፖለቲካ ፍጥጫው በስተጀርባ

ኢየሩሳሌም አርኣያ

በገዢው ሰፈር ጎራ ለይቶ ከተለኮሰው የቡድን ፖለቲካዊ ፍጥጫ እና ሴራ ጀርባ አገር እና ህዝብን የሚጎዳ አደገኛ ተግባር በግልጽ እና በስውር እየተካሄደ እንዳለ ከተለያዩ የፓርቲው ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ድምጽ ራዲዮ ሲፈተን

ክንፉ አሰፋ

አንድ የሜዲያ ተቋም ስኬታማ ስለመሆኑ የሚመሰክረው የስራው ውጤት ብቻ ነው። በመገናኛ ብዙሃን ስራ ላይ የተሰማሩ ጋዜጠኞች ስራቸውን የሚገመግሙት ከሚደርሳቸው በጎም ይሁን መጥፎ ምላሽ አንጻር ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ራዕይ አልባው ወራሽ!

(ታላቅሰው ምንአለ ከአ.አበባ)

በኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ዘመን ትምህርታቸውን ተከታትለው በማዕርግ መመረቅ ከቻሉ የዐመድ አፋሿ እናት ሃገር ልጆች መካከል አንደኛው ነበር። ጥሎበት  የመረጠውንና የዕለት እንጀራዬን ያሳምርልኛል ያለውን ሙያ ብቻ መከታተልን እንጂ ፖለቲካ ይሉትን ነገር እነደኮረንቲ ሲሸሽ ነው የኖረው። ጨዋነት ተፈጥሮው ነው። “እሺ” ባይነት መለያ ባሕርይው። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ቪቫ ስዬ አብርሃ!

አቶ ስዬ አብርሃንና ፕ/ር መረራ ጉዲና በሚኒሶታ ከተማ Siye Abreha and Prof. Merera Gudina public meeting in Minnesotaያሬድ አይቼህ

በሚኒሶታ ከተማ የአቶ ስዬ አብርሃንና የፕ/ር መረራ ጉዲናን ንግግሮች ፓልቷክ ዱቅ ብዬ ሰማሁ። ሁለቱም የዴሞክራሲ ታጋዮች ያቀረቡዋቸው ነጥቦች ግሩም ናቸው። በተለይ አቶ ስዬ ከስብሰባው ታዳሚዎች አንዱ ከነበሩት ከአቶ ጌዲዮን የቀረበላቸውን ጥያቄ አስከትለው ያነሱዋቸው ጉዳዮች እጅግ በጣም ማረኩኝ። ለካስ የበሰሉ የፓለቲካ ታጋዮች ኢትዮጵያ አፍርታለች! አቶ ስዬ አብርሃ በአንድ ጎኑ ብቻ የበሰለ ሰው አይደሉም። አቶ ስዬ በሁለቱም ጎኑ ተገላብጦ እንደበሰለ አንባሻ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፖለቲካ የዲሞክራሲ ጮራ ስትወጣ

ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም፦ ነጻነት ለሃገሬ)

በድጋሚ እውነት፤ ኃይልን ለተነፈጉ

ላለፉት በርካታ ዓመታት ስለሥልጣን ተጠቃሚዎች ዕውነትን ስናገር ነበር። የጦማሬ ገጼ መግቢያ መስመሩ ”ለሰብአዊ መብት ተሟገት። ስለሥልጣን ተጠቃሚዎች እውነትን መስክር” ነው የሚለው። ይህ ደሞ ልዩ ትርጉም ያለው፤ ጠንካራ ሞራልና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ አላግባብ የሚጠቀሙበትን፤ ከመጠን በላይ ለሚተማመኑበት ኢሰብአዊ ድርጊት ማስገንዘቢያ የሆነ ስንኝ ነው። ለባለስልጣናት ነን ባዮች እውነትን መናገር፤ ተናጋሪው በነዚህ ባለስልጣናት ላይ ስልጣናቸው የተዘረጋው በሃሰት ላይ መሆኑን ምስክርነቱን ያረጋግጣል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢንተርኔት አጠቃቀማችን “ነጻነት” ጉዳይ

ኤፍሬም እሸቴ

የኢንተርኔት መብት አያያዝ ጉዳይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን ሁናቴ በተመለከተ በየዓመቱ ጥናት የሚያደርገው “ፍሪደም ሐውስ” የሚባለው ታዋቂው የአሜሪካ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት የ2012 ዘገባውን ሰሞኑን ይፋ አድርጓል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂነት እንዳላቸው እና ዓመታዊ ሪፖርታቸው በጉጉት እንደሚጠበቀው “ሒዩማን ራይትስ ዎች”ን እንደመሳሰሉት ድርጅቶች ሁሉ “Freedom House”ም ሚዛን የሚደፋ ሪፖርት በማቅረብ የሚታወቅ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማግስት የተቋቋመ የአሜሪካ ድርጅት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የነፃነት ዘይቤ

ሰሎሞን ተሠማ ጂ.

“ነፃ-አውጪ” ነን ባዮችና “የነፃነት ታጋዮች/ተጋዳላዬች” ናቸው የሚባሉት ወገኖች ቁጥር ቀላል አይደለም። ለአብነት ያህል እንኳን “ሕወሐት- ሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ” (ወያኔ)፣ “ሕሐኤ- ሕዝባዊ ሐርነት ኤርትራ” (ሻዕቢያ)፣ “ኦነግ- የኦሮሞ ነፃነት ግንባር”፣ “ኦብነግ- የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር”፣ “ግ7ፍነን- የግንቦት 7፣ ለፍትሕና ለነፃነት ንቅናቄ”፣ “እኦነግ- የእስላማዊ ኦሮሚያ ነፃነት ግንባር (ጃራ)”፣ “አሕነግ- የአማራ ሕዝብ ነፃነት ግንባር” እና ከቅርብ ጊዜ ወዲህም “ነኢጦ- ነፃ የኢትዮጵያዊያን ጦር” የሚባል እንቅስቃሴም ስለመኖሩም ተሰምቷል። ከወያኔ በስተቀር፣ ብዙዎቹ “በሽብርተኝነት” የተፈረጁ ድርጅቶች ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፀረ-ማርያም ፖለቲካ

ማርያም Mariamተስፋዬ ገብረአብ

ስብሃት ነጋ፣ በፓልቶክ ክፍል ተጋብዞ ባደረገው ንግግር፣ “ለኦርቶዶክስ ወይም ለአማራ ብቻ ተወስኖ የቆውን የኢትዮጵያ መንገስታዊ ስልጣን ለተጨቆነው ህዝብ አስረከብነው” ማለቱን አንድ ጓደኛዬ ነገረኝ። ይህን የነገረኝ ጓደኛዬ በስብሃት ንግግር በጣም ተገርሞ ስለነበር፣ “አታስብ! ስብሃት አብሻቂ የንግግር ጠባይ አለው።” ስል ጠቆምኩት። ለነገሩ በሚናገረው ባልስማማም፣ ስብሃት ያመነበትን እንደወረደ ስለሚያፈርጠው ከሌሎቹ እሱ ይሻለኛል። “በዚህች አለም ላይ መጥፎም ይሁን ጥሩ ያመንክበትን ፈፅመህና የልብህን ተናግረህ ማረፍን የመሰለ እርካታ የለም” ይል ነበር መለስ ዜናዊ - ነፍሱን ይማረውና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ