አቶ ኃይለማርያም እና ኤርትራ
ግርማ ካሣ
“Hailemariam Desalegn a perfect mimic of Meles” በሚል ርእስ ሥር በኢትዮሜዲያ የቀረበች አጭር ትንተና አነበብኩ። የአቶ ኃይለማርያም ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬን እንዲሁም ልጃቸው ዮሃናን በተመለከተ በተጻፈው ላይ ትንሽ የግሌን አስተያየት እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ግርማ ካሣ
“Hailemariam Desalegn a perfect mimic of Meles” በሚል ርእስ ሥር በኢትዮሜዲያ የቀረበች አጭር ትንተና አነበብኩ። የአቶ ኃይለማርያም ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬን እንዲሁም ልጃቸው ዮሃናን በተመለከተ በተጻፈው ላይ ትንሽ የግሌን አስተያየት እንዳቀርብ ይፈቀድልኝ።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ነጻነት ለሃገሬ)
ኢትዮጵያ በመልካም ስሟም፤ በአስከፊ ገጽታዋም ትታወቃለች። ኢትዮጵያ በመልካም እንግዳ ተቀባይነቷና አስተናጋጅነቷ፤ በሕዝቦቿ መልካም ባሕሪ፤ በመልክአ ምድሯ ውበት፤ እና በግሩሙ ቡናዋና በማይደፈሩት ጅጋኖች ረጂም ርቀት ሯጮቿ ትታወቃለች፡፡ ተወዳዳሪ በሌለው የሰብአዊ መብት ጥሰት፤ የፕሬስ ማፈኛ ተቋሟም፤ በአፍሪካ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፖለቲካ እስረኞች የሚገኙባት ሃገርም ሆና ኢትዮጵያ ትታወቃለች፡፡
ሙሉውን አስነብበኝ ...
በኣረብ ኣገራት ለግርድና የሚሄዱትን እህቶቻችንን የሚደርስባቸውን ስቃይ መናገር መነሻዬ ኣይደለም። ያልፍልኛል፣ እናት ኣባቴን እጦራለሁ እያሉ ወደ ሊባኖስና ሌሎች የኣረብ ገልፍ ኣገራት የሚጎርፉት እህቶቻችን ከሰባዊነት ደረጃ ዝቅ ብለው ሲሰቃዩ ሌላው በተለያየ የኣለም ክፍል ያለው ኢትዮጵያዊ ከንፈሩን ከመምጠጥ ያለፈ ብዙ ነገር ሲያደርግ ኣይታይም። እግዚኣብሄር ይባርካቸውና የተለያዩ ሰባዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች የቻሉትን ሁሉ እየታገሉ ነው። ግን ኢትዮጵያዊው የበኩሉን ለመወጣት ከማንም በላይ የሞራልም የዜግነትም የውዴታ ግዴታ ኣለበት።
የዛሬው ጽሁፌ በሌላው ኣለም ያለው ኢትዮጵያዊ ምን ሊያደርግ ይችላል? በሚል ተግባራዊ ዘዴዎችን ለመጠቆም ነው።
በመሆኑም ለእህቶቻችን በሚከተሉት መስመሮች ልንደርስላቸው እንችላላን።
1) ለወገን ለሃገር ተቆርቋሪ በሆኑ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመው ኢሳት ቴሌዚዥን ድርጅት በኣፋጣኝ መቀመጫውን ሊባኖስ ያደረገ የሪፖርተር ቡድን ሊልክ ያስፈልጋል። ይህ ቡድን በየጊዜው የሚደርሰውን በደልና እንግልት እየዘገበ በማጋላጥ ችግራቸውን ሊቀንስ ይችላል። ኣንዱ ትልቁ ችግራቸውም በየሜዳው እየሞቱ ወደ ሚዲያ ስለማይወጣ ነው። ይህ ቡድን በየጊዜው በሚያደርገው ኢንቬስትጌቲቭ ሪፖርት ለኣለም ኣቀፉም ሆነ ለ ኢትዮጵያዊያን ያሳውቃል። ኣንዱ ችግር የኢንፎርሜሽንም ነው። ባለፈው እህታችን ኣለም ደቻሳ የሞተች ጊዜ ነው ትንሽ የተደናገጥነው። ያ ወደ ሚዲያ ስለወጣ እንጂ ሚዲያ ሳያውቃቸው የሚገደሉ የሚሰቃዩ ብዙ ናቸው።
ባለፈው የ ሂውማን ራይት ዎች ባውጣው ዘገባ ላይ እንደሚያሳየው በየ ሳምንቱ ኣንድ የቤት ውስጥ ሰራተኛ ተፈጥሮኣዊ ባልሆነ መንገድ ይሞታል። እንግዲህ ልብ በሉ በሊባኖስ ውስጥ ወደ 200 ሺህ የሚጠጋ የቤት ውስጥ ሰራተኛ ያለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ከ 60 እስከ 70 ሺህ የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ይህ ማለት በየ ወሩ ሁለት የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወይ ተገለው፣ ወይ ታመው ፣ወይ የሚያሳክማቸው ኣጥተው፣ ወይ ራሳቸውን እንዲያጠፉ ተገደው ይሞታሉ ማለት ነው። ከዚህ የከፋ ነገር የለምና ኢሳት ባስቸኩዋይ ደርሶ ወገንተኛነቱን፣ ኢትዮጵያዊነቱን ማሳየት ኣለበት።
2) በ ኣሜሪካን ኣገር ኣዲስ የተቋቋመው የሴቶች መብት ድርጅት ኣስቸኳይ የቤት ስራው ሊሆን የሚገባው የህግ ባለሙያ የያዘ ኣንድ ቡድን መላክ ነው። በርግጠኝነት ለመብታቸው ለሚሟገት በደላቸውን ወደ ብርሃን ለሚያወጣ ድርጅት ወጪውን እንደሚሸፍኑ እምነቴ ጽኑ ነው። ከሚያገኙዋት ጥቂት ገንዘብ ላይ እያዋጡ ወጪውን ሊሸፍኑ ስለሚችሉ ድርጅቱ በባጀት በኩል ስጋት የሚገጥመው ኣይሆንም። የተጨነቁ እህቶች ኣለን የሚላቸው ካገኙ የሚከፈለውን መስዋእትነት ይከፍላሉ። እነዚህ እህቶች ከ ኤምባሲ ያጡትን የምክር ኣገልግሎትና ፍቅር ይህ ለመብታቸው የቆመ ድርጅት ይክስላቸዋል።
3) ለሲቪክ ማህበራትና ለ ፓለቲካ ድርጅቶች።
ለግርድና የሄደችው እህታችን ስትሰቃይ ዛሬ ስትገደል ከንፈራችንን እየመጠጥን ችግሩ የሚፈታው የችግሩ ምንጭ የሆነው ኣምባገነን መንግስት ሲወገድ ነው ማለት ኣግባባ ኣይደለም። እሱን ማን ኣጣው? ኣሁን በመሃል ግን ድምጻቸው ታፍኖ ተዘልለው የሚያነቡትን እህቶች ኣይዙዋችሁ ማለት ግፋቸውን ማጋለጥ በርግጥ የህዝብ ፍቅር ያለው ድርጅርት ተግባር ነው ። የነሱን መከራና ግፍ ለፓለቲካ ፍጆታ መጠቀም ፈጽሞ ሊሆን ኣይገባም። በመሆኑም ሁለቱም ኣይነት ድርጅቶች በመገናኛ ብዙሃኖቻቸው ይህን በደል ማውጣት ማሳየት ሰላማዊ ሰልፍ ማቀድ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ሌላው ደሞ ለዚህ የዳረጋቸውን ኣስከፊ ስርኣት ለመለወጥ እንዲችሉ ሊያደራጁዋቸውም ይገባል።
4) ሌላው ከፖለቲካው ተገልሎ ያለው ኢትዮጵያዊ በሙሉ በያለበት ድምጹን በተለያየ መንገድ ማሰማት ኣለበት። በፌስ ቡክ በሰልፍ ወዘተ. ተቃውሞውን ማሰማት ኣለብት። ኣንዲት ኣረብ ኣገር የምትኖር እህታችን በስሜት ስትናገር እህቶቻቸውንና ሴቶቻቸውን ኣውጥተው ለግርድና የሰጡ ወንድሞች እንደ ኢትዮጵያዊያን ኣላየሁም ብላለች። ድሃ ኣገር እኛ ብቻ ኣይደለንም ግን እንደኛ ሴቶች ለግርድና ሄዶ የሚሰቃይ የለም ብላለች። በመሆኑም ኣለማቀፋዊ ተቃውሞ በማድረግ እህታችንን ልንደገፍ ይገባናል።
እነዚህ ከፍ ሲል ያነሳሁዋቸው ነጥቦች በውነት በጣም ቀላል ልንሰራቸው የምንችላቸው ናቸው።
እግዚኣብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!
አቤ ቶኪቻው
አዲሳባ ብሆን በፍፁም ከማልቀርባቸው ቦታዎች ውስጥ ሶስቱን ጥቀስ ብባል አንድ ታላቁ ሩጫ ሁለት ኢህአዴግ የሚጠራቸው ሰልፎች (በቅንፍም ተቃዋሚዎች ሰልፍ ስለማይጠሩ አምሮት መወጫ ነው!) ሶስት አዲሳባ ስታድየም ናቸው። ሙሉውን አስነብበኝ ...
ተስፋዬ ገብረአብ
በኛ ዘመን የብእር ሰው ሆኖ መፈጠር መረገም ሆኖ ይሰማኛል። ከቡቃያው የሚነጋገር፣ በሁዳዱ ላይ ሽምጥ ፈረስ የሚጋልብ፣ ውሎው ከዋልካው፣ ማምሻው ከመልካው የሆነ ገበሬ እንዴት እድለኛ ነው? የኛ ዘመን ብእረኛ ህይወቱ በሰላዮች የተከበበ ነው። ተፈጥሮው ነውና አለመፃፍ አይችልም። መፃፍ ደግሞ አደጋ ነው። በአሉ ግርማ እንዲህ ባለ ችግር ውስጥ አልፎ፣ በከንቱ ያለፈ ደራሲ ነበር። ደርግ ብዙ ሰላዮች መድቦበት ነበር።
ሙሉውን አስነብበኝ ...ይድረስ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ
ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)
ከሀያ አንድ ዓመታት የሸፍጥ፤የውሸት፤የተንኮል እና የጭካኔ አገዛዙ በሗላ በኢትዮጵያ ህዝብ እንቢ ባይነትና በሟቹ አንባገነን “እኛ እንጂ የሚገዛችሁ የለም” የተግባርና የስነልቡና ጦርነት፤በአሜሪካኖች፤ በእንግሊዞች ወይም ደሞ በኔቶ ያየር ድጋፍ ሳይሆን በእግዚአብሄር ጣልቃ ገብነት፤መለስ ዜናዊ የፈጀውን ፈጅቶ ገና ሳይበቃው፤ ያን ሁሉ በህዝብ ላይ የተሸከመውን ንቀት፤ ያን ሁሉ በአማራ ላይ ያረገዘውን ጥላቻ፤ ያን ሁሉ ለዛ የሌለው ንግግር እንደተጫነ፤ የልቡን እስከመጨረሻው ሳያደርስ ኢትዮጵያን ሳይበትንና የትግራይን መንግስት በይፋ ሳያውጅ እንደወጣ በዚያው ቀረ። የእግዚአብሄር ፍርድ ይግባኝ የለውም። እሱ የፈረደባቸው የእስር ግዜያቸውን ሳይጨርሱ፤ ሞት የፈረደባቸውም ተራቸውን በመጠበቅ ላይ እንዳሉ፤ ለምን እንደቀደማቸው የሚታወቅ ነገር የለም።ቀደማቸው።ይገርማል። ሙሉውን አስነብበኝ ...ጠቅላይ ሚንስትር የነበሩት ታመዋልም ሞተዋልም በሚማልበት ሰአት ሎጋው ሽቦ ተዘፈነ …
የርዕሰ ብሄር መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ በሆነበት ሰአት ደግሞ ብር አንባ ሰበርልዎ ተብሎ ሲዘፈን በሰፊው ተሰማ…
ኃይለማርያም ደስ አለኝ ቦታው ተፈቅዶላቸው ሀገር ወከሉ ተብሎ ሲታወጅ አስገራሚው ዘፈን አላቆመም የቤተ ዘመዱ ይታያል ጉዱ ይባል ተገባ…
////////////////////////////////////////////////
አጋጣሚ የፈጠረውን ፖለቲካዊ ግርግር በጥበብ ተጠቅሞ በፖለቲካው እንቅስቃሴ ውስጥ የመደራደሪያ አቅም በማበጀት ወይም አቅም በመገንባት አማራጭ ሀይል መሆንን ከማሳየት ፋንታ በቀረርቶና በሽለላ የጨዋታውን ህግ ለመቀየር መመኘት የምኞት ሁሉ መናኛ ቢባል ያስነውር ይሆን?
በትግል አጋሮቻቸው ከአንድ ነፍስ በላይ እንዳላቸው የተስትናገዱት ጠቅላይ ሚንስትሩ ለመጨረሻ ግዜ የስጋቸውን ነፍስ ተሰናብተው በአጥንታቸው ላይ በቀረው ነፍስ ተንገዳግደው ደቡብ አሜሪካ ሜክሲኮ ብቅ ብለው ነበረ።
ታዲያ ከወዳጃቸው ከቻይናው መሪ ጋር ተጨባብጠው እስከ ወዲያኛው በተሰነባበቱበት ወቅት አጥንታቸው ከስጋቸው መለያየቱን ያላስተዋለ የኮንፒውተር ቆዛሜ አለ ብየ አላምንም።
በዚያን ወቅት በውጭ የሚገኙት የፖለቲካ ጥበብ ያልዞረባቸው ተቃዋሚዎች መንግስት የተገለበጠ መስሏቸው ተዋግቶ ነፃ መሬት እንደያዘ የደፈጣ ተዋጊ ዘራፍ በማለት የተለመደው ምስቅልቅል የፖለቲካ አመራር ከየአቅጣጫው ይጎርፍ ጀመረ።
ሰውየውም ያላቸውን ነፍስ በሙሉ አሟጠው ካመለጡም በኋላ ይህንን ማመን የከበዳቸው ጓዶቻቸው የጠቅላይ ሚንስትሩን ሪሳ አልሞትክም ብለው ሲክዱ፥ ህዝቡን ደግሞ መሪያችን አልሞቱም በማለት ገገሙ።
ይህም ሆኖ መሪያችው የሚሞት ስጋ ለባሽ መሆናቸውን መቀበል ያቃታቸው እስከሚመስል ድረስ ተደናግጠው በነበረበት ወቅት የመሪያቸውን ሞት በመካድ የመረጋጊያ ግዜ ገዝተው የተቃዋሚዎቻቸውን እንቅስቃሴ በትጋት መከታተል ጀመሩ።
ፖለቲካ የፉክክር ጨዋታ መሆኑን እንጂ የመጫወቱ ተሰጥኦ እንብዛም ያልተካኑት ከሀገር ውጭ የሚገኙ ተቃዋሚዎች ታዲያ የተሸበረው መንግስት ግዜን ለመግዛት በመረጠው ሜዳ ሲያሰልፋቸው በተርታ ተኰልኩለው የመለስ ዜናዊን ዜና እርፍት ለነበረከት ስምኦን ለማሳመን ያላሉትና ያልሰማነው ትንታኔ የለም እንግዲህ ይህንን ስንል ፉከራውንና ሽለላውን ትተነው ነው።
በመጨርሻም በረከት፤ ሳሞራና፤ ብርሀኔ ገብረክርስቶስ፤ የሞት ትርጉሙ ገብⶆአቸው የመሪያቸውን ሞት ይፋ አደረጉ።
በዚህን ግዜ ደግሞ ከሜዳ ውጭ ሆኖ የሚጫወተው ተቃዋሚ ቡድን በጎዶሎ ተጫዋች ከሚጫወተው የገዢው ፓርቲ ላይ ግብ ለማግባት የጫዋታ ስልት ቀይሮ ዋና ሚዳ ውስጥ ለመግባት መሞከሩን ዘንግቶ ድል ብድል እያሉ በመዘመር ለመለስ ከሚያለቅሰው ወይም ከሚያስለቅሰው ቲፎዞ ጋር ግብግብ ገጥመው ጨዋታውን በፎርፌ አስረከቡ።
በፖለቲካ ጨዋታ እንደሚታወቀው ዳኛ የሚሆነው ምንግዜም አሸናፊው ነው።
በመሆኑም በተቆጣጠሩት ሜዳና ባላቸው የዳኝነት ስልጣን ተጋጣሚውን ቡድን ከለቀስተኛው ጋር አተካራ ተያይዞ ከሜዳው መራቁን ካረጋገጡ በኋላ የጉደለባቸውን ተጫዋች(ጠቅላይ ሚንስትሩን) ለመተካት እርስ በርስ ተሳልጠው፥ ተዋቅጠው፥ ተዳጉሰው፥ ተሰልቀው፥ በመጨርሻም ለኃይለማርያም ደሳልኝ የሟቹን የማእረግ ስምና መቀመጫ ሸልመው አሁንም ጨዋታውን በበላይነት መምራት ይዘዋል።
ታዲያ እንዳያችሁት በፎርፌ የተዘረረው የጨዋታው ህግም ይሁን ጥበብ ያልገባው የውጪው ተቃዋሚ ቡድን በሚያስገርም አይነት የምኞት ፈረስ ላይ ቂጥ ብሎ በጎደለው ተጫዋች የተተካውን ኃይለማርያም ደሳለኝን በራሱ ቡድን ላይ ጎል እንዲያገባ የቤተዘመዱ ይታያል ጉዱ እያሉ በመዝፈን የምኞት ሁሉ መናኛ የሆነውን ምኞት ተመኙ።
ባልተመጣጠነ ጉልበት፥ ውል በሌለው አመራር፥ ጥበብ ባልዞረበት ስሌት፥በተለይ ደግሞ፥ በተመሰቀቃቀሉ ድርጅቶች፥ የሚመራው ከሀገር ውጭ የሚደረገው ትግል፤ ጉልበቱን ያፈረጠመን መንግስትና፥ ሁኒታዎችን የመጠቀም የረቀቀ ዘዴ የተለማመደን ግዙፍ ድርጅት፥ እንዲሁም ስልጣን ማለት አስፈላጊ የሆነ የሴጣን ስራ (power is the necessary evil) መሆኑን ተረደቶ በጭካኔ ለሚወሰድ እርምጃ ቀላል መክንያት ሰጥቶ ከሚያስፈፅም ቡድን ጋር ሲጋጠም የራስ አቅምንናና የባላንጣን ጉልበት ማወቅ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ወሳኝም ነው።
መሪውና ተመሪው ተደባልቆ፥ ሽለላና ፉከራ በመሰቃቀሉት፥ በእውቀት ሳይሆን በስሜት በሚንቀሳቀስ በብዙ መሪዎች የሚመራው እንቅስቃሴ የመሸነፍን ልምድ ለሀያ አመት ደግሞ ደጋግሞ ተጎናፅፏል ይህንን ለመቀየር ይህችኑ እውነት ክልብ ማመን የመጀመሪያው እርምጃ ይሆነል።
በተለይ ካገር ውጭ ሆኖ አብሮ ካማይኖረው ህዝብ ላይ የመሪነትን መንፈስ ማዳበር በተግባር ሊተረጎም የማይችል ግብ አልባ ጨዋታ ነው።
የሰማኒያ ሚሊዮን ህዝብ ጉዳይ የኔ ነው ብሎ እራሱን ወክሎ የሚንቀሳቀስ ቡድን መደገፍ እንዳለበት ሁሉ ሀላፊነትን በሚገባ ካልተወጣና መወጣት ካቃተው እንዲስተካከል መጠረብ ይገባዋል።
ስለዚህም በውጭ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተመሰቃቀለውን የተቃዋሚ ድምፅ መግራትም ሆነ ማጎለበት ካልቻሉ መገሰፅና መወረፍ አግባብ ነው።
ብዕሪ በተቃዋሚዎች ላይ እንዲህ መሳለቁ ገዢዎቹን ደግፌ ውይንም ፈርቼ አይደለም።
ይህንን ብሶቴን በማስተዋል ያነበበና እንደኔ በውጭ በሚገኘው ተቃዋሚው ተስፋ የቆረጠ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይገነዘባል ብየ አምናለው።
የመብት ረጋጮቹና የጉልብት አምላኪዎቹ ገዥዎቻችንን ፅናትንና ያላሰለሰን ዘዴ ባደንቅም ለሰማኒያ ሚልዮን ህዝብ ተጠሪ ለመሆን የሚያበቃ የሞራልም ሆነ የሀገር ፍቅር ስሜት የሌላቸው መሆናቸውን መናገር አስፈላጊ ይመስለኛል።
በፖለቲከኞች መሳለቅ መቀለድ ከዛም ሲያልፍ መፀየፍ ግፍና አድሎ ያንገበገብው በዕር መሄጃ ሲያጣ የሚያነባው እንባ በመሆኑ እንደተለመደው በአንድ አይነት አስተሳሰብ ዙሪያ ብቻ ያልተፃፈን አስተያየት ከተቆጣጠራችሁት መድረክ የምታገሉት ከሆነ ከገዢዎቻችን መንፈስ ያልተለያችሁ ስለሆነ አንድ አርጌያችሁ እድታገላችሁ እገደዳለሁ ማለት ነው።
በመጨረሻም የፖለቲካ መሪዎችና ፓርቲዎች የመምራት ሀላፊነት ስላለባችሁ በድረ ገፅ አርበኞች፤ በሪድዮ ፕሮግራም ፊት አውራሪዎች፤ በአጠቃላይ በብዙሃን መገናኛ ባለሙያዎች መመራታችሁን አቁሙና እንደ ፖለቲካ መሪ አላማችሁን ፕሮግራማቹን ፍልስፍናችሁን አጥምቁንና ምሩን።
የብዙሀን መገናኛ ባለሙያዎች ወይም የድረ ገፅ፥ ሪድዮንና፥ ፓል ቶክ፥ ጋሻ ጃግሪዎች በምታደርጉት ተሳትፎ መብታችሁን እየተለማመዳችሁ መሆኑን ጥያቄ ውስጥ ባላስገባውም ቢይንስ ብያንስ ከሙያ አንፃር በመመልከት ለዲሞክራሲያዊና ሠብዐዊ መብት የሚደርገገው ትግል እንዳይጓተት ለፖለቲካ ፕርቲዎች እንቅስቃሴ እንቅፋት አትሁኑ።
ማለትም በሙያችሁ እንደጋዜጠኛ አግልግሉን አልበለዛም ለአንዱ ፓርቲ አድራችሁ እንደ መሪ ምሩን ተመሰቃቅላችሁ አትመሰቃቅሉን።
እስካሁን ግን ሳታውቁት ጠላታችሁን እያገለገላችሁ ነው።
እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይታደጋታል!!
ጸሐፊዉን ለማግኘት ከፈለጉ at: This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
ግርማ ካሳ
በምርጫ ዘጠና «ይህ ሕዝብ የሚፈልገው የመጣህበትን መሰረት አይደለም። የመጣህበትን ብሄር አይደለም። የምትሰራለትን ስራ ነው» የሚለው፣ አቶ በረከት ስምኦን ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ካደረጉት ቃለ ምልልስ የተቀነጨበ ግሩም አባባል ነው። ከአንድ ከኢሕአዴግ አመራር አባል ብዙ ጊዜ የማንሰማው አባባል!!!
ሙሉውን አስነብበኝ ...
ተስፋዬ ገብረአብ
ሰሞኑን ግርማ ብሩ አሜሪካ ለሚገኝ ሬድዮ ሰጠውን ቃለመጠይቅ በጥንቃቄ አዳምጬው ነበር። በርግጥ ሰውየው ስነአመንክዮአዊ ክርክር ይችልበታል። የሚጠቀምባቸው ቃላት ምርጥ ናቸው። ቢሆንም መረጃ ይደብቃል። ከእውነታው ይሸሻል።
ሙሉውን አስነብበኝ ...
(ልዩ ጥንቅር- በደረጀ ሀብተወልድ - ኢሳት)
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶና አራት ባለስልጣናት፤ ከኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚነት ሰሞኑን ተነስተዋል። ሚኒስትር ጁነዲንና አራቱ አመራሮች ከሥራ አስፈፃሚነታቸው እንዲነሱ የተወሰነው፤ የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ካለፈው መስከረም 21 ቀን እስከ መስከረም 24 ቀን ባካሄደው ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ነው።
ሙሉውን አስነብበኝ ...