ኢትዮጵያ፤ በአዲስ ዓመት አዲስ ጠ/ሚኒስቴር

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ

ኢትዮጵያዊያኖች አዲሱን ዓመታቸውን የዘመን መለወጫ በሴፕቴምበር 11 አክብረዋል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ 2005 ዓም ነው፡፡ በሴፕተምበር 21 ደግሞ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሰጥቷቸዋል፡፡ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአዲስ ዓመት መግባት ጋር ተዳምሮ ሲቀርብ እንዴት ደስ ያሰኛል!! ከልብ የመነጨ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክትና መልካም ምኞት ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ተገቢ ነው፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለጠ/ሚ/ር ኃይለማርያም ደሳለኝ ያልተባሉና ያልተነገሩ ነገሮች በቀድሞ ተማሪያቸው ዕይታ

ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ PM Hailemariam Desalegn

ታደሰ በላቸው (ከአቶ ኃይለማርያም የቀድሞ የዩነቨርሲቲ ተማሪ)

I. መግቢያ፡-

የጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊ ድንገተኛ ሞት ተከትሎ የአቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ያልተጠበቀና ያልታሰበ ወደስልጣን መምጣት ብዙዎችን ያስገረመ ጉዳይ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የዚች ሃገር ጉዳይ ያገባኛል ያሉ ብዙ ግለሰቦች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማሀበራት እና ሌሎችም የሳቸው ሹመት ለሃገሪቱ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችልና ምናልባትም ፈጣሪ ለዚች ሃገር ለውጥ ያስቀመጣቸው ሊሆኑ ሁሉ እንደሚችሉ ተስፋ አድርገውባቸዋል። እኔም ከነዚህ ወገኖች አንዱ ነኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢህአዴግና የተዳፈነው ፍም

ደረጀ ሀብተወልድ ከሆላንድ

የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ እና ሊፈነዳ የደረሰ ቂም እንዳለ በስፋት ይወራል። እርግጥ ነው፤ ባለፉት ዓመታት በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች በተለይም በህወሓት እና በብአዴን መካከል ተዳፍነው የቆዩት የቂም እሳቶች በገሀድ የሚነድዱበት ጊዜ ላይ የደረስን ይመስላል። ስፍር ቁጥር ከሌላቸው የነ አቶ በረከት እና የህወሓቶች ቁርሾዎች መካከል ለዛሬ አንዱን እንመልከት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጉዱ ካሳ እና “ሰበነክ-ሊቃውንት”

ኤፍሬም እሸቴ

እንግሊዛዊ ሆኖ “ሼኪስፒርን የማያውቅ፣ ሥራዎቹንም ያላነበበ፣ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ሀዲስ ዓለማየሁን የማያውቅ ‘ፍቅር እስከ መቃብርን’ም ያላነበበ” ቢኖር እጅግ የሚደንቅ ይሆናል። እንዲያውም ጥያቄው ‘ስንት ጊዜ አነበብከው?’ እንጂ ‘አንብበኸዋል እንዴ?’ አይሆንም የሚል ግምት ነበረኝ። ከዕለታት በአንዱ ቀን በድሮ የትምህርት ቤት መጽሐፎቻችን ውስጥ ስላሉ ታሪካዊ ጽሑፎች ስናወጋ በመካከሉ አብዲሳ አጋን አስታወስን። “ስንተኛ ክፍል መጽሐፍ ውስጥ ነበር ጃል?” እያልን ስንጠያየቅ አጠገባችን የነበረ አዕምሮው ብሩህ የሆነ ልጅ እግር የዩኒቨርሲቲ መምህር “ማነው አብዲሳ አጋ?” የሚል ጥያቄ አቀረበ። በመጀመሪያ እንደ ቀልድም ወሰድነው። ቀጥሎ እንደ መገረምም አደረገን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የበረከት አዜብና የስብሃት ፍጥጫ

 ከኢየሩሳሌም አርአያ                                                       

በሽማግሌው ስብሀት ነጋና በረከት ስምኦን መካከል ስር ሰዶ የቆየው የውስጥ ሽኩቻ እየከረረ ሔዶአል ።አዜብ መስፍን ከበረከት ጎን ተሰልፈዋል።አዜብ ለፓርቲው ሊቀምንበርነት «ይመጥናሉ» ያሉዋቸውንና «መለስን ይተካሉ» ሲሉ በድፍረት የተሟገቱላቸው ሁለት አመራር አባላት ተቀባይነት አለማግኘታቸው አበስጭቶአቸዋል። አዜብ የጠ/ሚ/ር እንዲሆኑ የተሟገቱላቸው ቴዎድሮስ አድሀኖም ከእጩነት ራሳቸውን በማግለል ኩም አድርገዋቸዋል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሞቱት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ቢሆኑስ ኖሮ?

ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም Mengistu HaileMariamአቶ መለስ ዜናዊ Meles Zenawiበሕግ አምላክ (ከስዊድን)

ሰው ሆኖ መኖር፣ ኖሮ - ኖሮ መሞት አይቀርም። ቢሆንም ገና በህይወት ያለ ሰውን ቢሞት ኖሮስ ብሎ የቀብር ስነሥርዓቱን መግለጽ በባህላችን አልተለመደም። ስለዚህም በርዕስ ምርጫዬ ኮሎኔል መንግሥቱ ቤተሰቦቻውም ሆኑ ደጋፊዎቻቸው እንደማይቀየሙኝ ተስፋ አደርጋለሁ። በርካታ ሰዎች በምስል አቅርቦትና በድምፅ ቀርፃ ያዩትንና የሰሙትን አስመልክቶ የአቶ መለስ ዜናዊ የቀብር ስነሥርዓት እፁብ ድንቅና ወደርየለሽ ነው ይላሉ። እኔ ግን ወደርየለሽ የሚለውን አባባል አልጋራቸውም። ምክንያቱም ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትንሽ ድጋፍ ለአቶ ኃይለማርያም

ደረጀ ሀብተወልድ (ከሆላንድ)

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከአቶ መለስ የተረከቧት ኢትዮጵያ፤ እርሳቸው ቃለ-ምሕላ ከፈጸሙ በሁዋላ እንዳሉት ወደ ተስፋ ምድርነት ለመቀየር ሩብ ጉዳይ የቀራት ኢትዮጵያ ሳትሆን፤ በውድቀት አፋፍ እያጣጣረች የምትገኝ ኢትዮጵያ ናት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጨለማው ሰው

ቴዎድሮስ ኃይሌ

በርካታ የኢትዮጵያውያን ድረ ገጾች (ኢንተርኔቶች) አሉ፣ በርካታ የኢትዮጵያውያን የፓልቶክ መነጋገሪያ ክፍሎች (ፓልቶክ ሩምስ) አሉ፣ በርካታ የኢትዮጵያውያን ሬዲዮ ጣቢያዎችና ጋዜጦች አሉ። የድረገጾቹን አዘጋጆች እናውቃቸዋለን - እዚያ ላይ አስተያየትና መጣጥፍ የሚያቀርቡትን ብዙዎቹን ግን አናውቃቸውም። ብዙዎቹን የፓልቶክ ውይይት ክፍል አስተዳዳሪዎች (አድሚንስ) እናውቃቸዋለን - እዚያ ላይ መጥተው የሚያወሩትንና አስተያየት የሚሰጡትን ብዙዎቹን ግን አናውቃቅቸውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ