ሃይማኖትና አክራሪነት
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
አንድ የአሜሪካ ፈላስፋ የሚተርከው ገጠመኝ አለው፤ አንድ ቀን በእግሩ ሲንሸራሸር ሰዎች አንድ ዛፍ ከብበው ሲጨቃጨቁ ያያል፤ ይጠጋና ሲያዳምጥ ክርክሩ በአንዲት ዛፉ ላይ ባለች የዛፍ አይጥ (የዛፍ አይጥ እኔ ያወጣሁላት ስም ነው፤ በእንግሊዝኛ ስኮረል ትባላለች ረጅም ጭራ ያላት ጸጉራማ ፍራፍሬ ለቃሚ ነች፤) የተነሣ ነው፤ አንዱ ሰው ይቺን የዛፍ አይጥ እዞራታለሁ ይላል፤ ሌላው ደግሞ የለም ዛፉን ትዞራለህ እንጂ አይጥዋን ልትዞራት አትችልም ይላል፤ እዞራታለሁ የሚለው ሰው ለማስረዳት ዛፉን ይዞራል፤ አይጥዋም በዛፉ ላይ ትሽከረከራለች፤ የተሰበሰቡት ሰዎች በዚህ ጉዳይ ለሁለት ተከፍለው ይጨቃጨቃሉ። ሙሉውን አስነብበኝ ...


