“ጠ/ሚኒስትሩ ስለ ማኅበረ ቅዱሳን በተናገሩት አልስማማም”

Diakon Ephrem Eshete + Mahibere kidusan + PM Meles Zenawi(ኤፍሬም እሸቴ - በግል)

ማክሰኞ ሚያዚያ 9/2004 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለምክር ቤቱ ሪፖርት ካቀረቡ በኋላ እንደተለመደው የምክር ቤቱ ክቡራን አባላት በንባብ ላቀረቡላቸው ጥያቄዎቻቸው መልስ ሲሰጡ ተከታትያለኹ። ከጥያቄዎቹ አንዱ ወቅታዊው የሙስሊሞች ጉዳይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምላሻቸው “መንግሥት በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ አልገባም” የሚለውን በሰፊው ሲያብራሩ ቆዩ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጎሹም ሄደላችሁ!

ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ Colonel Goshu Woldeተስፋዬ ገብረአብ

የኮሎኔል መንግሥቱን መጽሐፍ ሳነብ ከገረሙኝ ነገሮች አንዱ የኮሎኔል ጎሹ ወልዴን ስም አለመጥቀሱ ነበር። ቢያንስ፣ “የታጠቅ ጦር ሰፈር አመሰራረት” በሚለው ምእራፍ ስር እንኳ ስሙን ሊያነሳው በተገባ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ2004 ፋሲካ በጨረፍታ

ተሻለ መንግሥቱ

የክርስትና እምነት ተከታይ የሆናችሁ የድረ ገጽ ታዳሚዎች እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሳችሁ። ለጊዜው መድረሳችሁ ብቻ ይበቃል - አደረሳችሁ ላይ ለወትሮው ይገባ የነበረው ‹በሰላም› የሚለው ቅጥያ ለአሁኑ ይቅር። እየተዋወቅን ለደንብ ሙሌት ብቻ በቃላት አንጫወትም፤ እነሱም ይታዘባሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ፤ ወደ ዴሞክራሲ የመጓዣው ጎዳና ካርታ ላይ

ፕ/ር ዓለማየሁ ገብረማርያም (ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ)

ባለፈው ሳምንት በሲያትል ከተማ የኢትዮጵያን ራዕይ በተመለከተ ሰፊ ሕዝባዊ ውይይት፤ ክርክር፤ ለማካሄድ በተመሰረተ የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ፎረም ላይ (EPFS) ላይ ተጋብዤ ተገኝቼ ነበር። በዚህምስብሰባ ላይ በቅርቡ ሳቀርባቸው በነበሩት የኢትዮጵያን ከፈላጭ ቆራጭ ግዛት ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሽግግርን በተመለከተ ማብራሪያ እንድሰጥ ተጠይቄ ነበር። እኔ በኢትዮጵያ ከፈላጭ ቆራጭ አገዛዝ ወደ ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ሊካሄድ ስለሚገባው የሽግግር ሁኔታ የማቀርባቸው ሃሳቦች፤ በሃገራችን በመካሄድ ላይ ያለውን ጭካኔ የተመላበት አገዛዝ፤ የሰብአዊ መብት ረገጣ፤ የፍትሕ እጦት፤ እስራትና ወከባን በተመለከተ ካለኝ ወገናዊነት የተነሳ የተፈጠረብኝ የግል አመለካከቴ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የፍትህ መንገድ-ከአሲምባ እስከ ቀራኒዮ

ተመስገን ደሳለኝ

ፍትህ ጋዜጣ (አዲስ አበባ)

አቤት! እንደምን ያለ ጉዞ ነው? አድካሚ፣ ፈታኝ፣ አስፈሪ፣ አደናቃፊ… ብቻ ዙሪያው በአደጋ የተሞላ ነው። ልክ እንደ ጦር ሜዳ። በእርግጥ ጦር ሜዳን በፊልም እና በቴሌቪዥን ካልሆነ ገፅ-ለገፅ አይቼ አላውቅም። ሆኖም በጣም አስፈሪ እና ከሞት ጋር ‹‹አኩኩሉ›› የመጫወት ያህል እንደሆነ ለማወቅ አይቸግረኝም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሰውዬውን ከሀሳቡና ከአስተሳሰቡ እንለየው

ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም

አቶ ስብሐት ስለ ውይይትና ስለክርክር ጠቃሚነት ደጋግሞ ይጽፋል፤ በሰንደቅ ጋዜጣም በጻፈው ውስጥ (መጋቢት 12/2004) ‹‹ውይይት እየተደረገበት፣ ሕዝብ እየተሳተፈበት፣ ሓቁ እየተነጠረ፣ እውቀት እየተመረተ፣ ሕዝባዊ ጉልበት እየተጠናከረ እንዲሄድ የሚያደርግ ዓይነተኛ የዴሞክራሲ ሂደት ይመስለኛል፤ ሂደቱ መበረታታት አለበት።›› ይላል፤ በመሠረቱ ይህ ግሩም ሀሳብ ነው፣ ግን ማንም የማይደግፈው የለም ለማለት አይቻልም፤ ይህንን ሀሳብ የማይደግፉት ለስብሐት ቅርብ ናቸው፤ መልእክቱ እንደሚደርሳቸው ተስፋ አለኝ። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእኛስ ጠቅላይ ሚንስትር ማን ነው?

ተመስገን ደሳለኝ

የጦር ሃይሎች አዛዥ የኢህአዴግ ሊቀመንበር፣ የህወሓት ዋና ፀሀፊ፤ የአፍሪካ የአየር ንብረት ተደራዳሪ፣ አባይን የደፈሩ፣ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሚሉ በርካታ የሹመት ተቀጥላዎች በኋላ የምናገኛቸው መለስ ዜናዊ ሰሞኑን የአባይ ግድብ የታቀደበትን (የተሰራበትን አይደለም) አንደኛ አመት አስመልክቶ ከሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ካሉ ኢትዮጵያውያኖች ‹‹የተሰበሰበ›› ተብሎ የተለያዩ ጥያቄዎችን (በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን አቅራቢነት) ሲመልሱ ተመልክተናል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ