ኢትዮጵያና ኤርትራ ወደ ሠላም ወይስ ወደ ጦርነት?

(ትንታኔ)

በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ሠላም ለማስከበርና ለማስፈን በሚል በሁለቱ ሀገራት ድንበር መሃከል ሰፍሮ የነበረው የተባበሩት መንግሥታት ሠላም አስከባሪ ቡድን (አንሚ) ባለፈው ሐምሌ 23 ቀን 2000 ዓ.ም. ተልዕኮው መገባደዱን ገልጾ ከሰፈረበት ጥሎ መውጣቱ አይዘነጋም። የአንሚ ውሳኔ በርካቶችን ያሳሰበ ጉዳይ ከመሆኑም በላይ ሁለቱ ሀገራት ወደ ሠላም ወይንስ ወደ ጦርነት ነው የሚያመሩት? የሚል ጥያቄ አስከትሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለአቶ አብርሃም ያየህ ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ (ከተስፋዬ ማሩ)

ሃሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት ሳይከበር የጥላቻ ፖለቲካን እና የመሳሰሉትን ለመዋጋት መሞከር ከንቱ ልፋት ነው

በተስፋዬ ማሩ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.) - ለአቶ አብርሃም ያየህ ጽሑፍ የተሰጠ ምላሽ

በሀገራችን ፖለቲካ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የሚነሱትን የጥላቻ ክስተቶች በተመለከተ ጥቂት ተብሏል። ቀና አመለካከት ያላቸው ሰዎች ጥላቻ ሊያመጣ የሚችለውን ክፉ ውጤት እየጠቀሱ ማስጠንቀቂያ በሞላበት ሁኔታ ለማስተማር ሞክረዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከወርቅ የበለጠ ሜዳሊያ (ግርማ ካሣ)

ግርማ ካሣ - ቺካጎ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.) እሁድ ነኀሴ 18 ቀን 2000 ዓ.ም.

Tirunesh Dibaba, Beijing Olympic, 20080822Kenenisa Bekele, Beijing Olympic, 20080823

“ድሮ መች ነበረ ዘር መርጦ ጎሮቤት

በጠዋቱ በጥንቱ በነአባብዬ ቤት

እድር መቃብሩ ሲያሰባስባቸው

መች ይጠየቅ ነበር የዘር ሃረጋቸው” 1

በቤጂንግ አትሌቶቻችን በወርቅ፣ በብር እና በነኀስ የተሰሩ ሜዳሊያዎች ብቻ አልነበረም ያስገኙት። የኦሎምፒክ ኮሚቴ ከሚሰጠው ሜዳሊያዎች ያለፈ፣ የኦሎምፒክ ባለሥልጣናት የማያወቁት፣ እጅግ በጣም የከበረ የሜዳሊያዎች ሁሉ ሜዳሊያ ይዘውልን መጥተዋል። … አሲዮ ቤሌማ!!!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"ኦባማ እና ኢትዮጵያ - ከተስፋ ማጣት ወደ መሪነት" ፕ/ር ዶናልድ ሌቪን

Prof. Donald N. Levineበቅርቡ አሜሪካዊው ፕሮፌሠር ዶናልድ ሌቪን ”ኦባማ እና ኢትዮጵያ - ከተስፋ ማጣት ወደ መሪነት” በሚል በእንግሊዝኛ ያቀረቡትን ጽሑፍ በሀገር ውስጥ የሚታተመው ”እንቢልታ” የተሰኘው ጋዜጣ ወደ አማርኛ ተርጉሞ ለንባብ አብቅቶታል። ይህንኑ ትርጉም የኢትዮጵያ ዛሬ ታዳሚዎች በሀገራቸው ቋንቋ ቢያነቡት ለግንዛቤ ይረዳቸዋል በሚል እንደወረደ አቅርበነዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የብሔር (ጎሣ) ግጭት መንስዔዎችና መፍትሔዎቹ

( ትንታኔ)

ከ81 በላይ የሆኑ ብሔሮች በኢትዮጵያ እንዳሉ ይታወቃል። እነዚህ ብሔር ብሔረሰቦች ለረዥም ዘመናት የቆየና የዳበረ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ባህላዊ ትስስር እንደነበራቸውና እንዳላቸው እሙን ነው። በተቃራኒው ደግሞ በተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች መካከል ግጭቶች ሲከሰቱ ኖረዋል። በተለይ ከ1983 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥ ወዲህ ግጭቶቹ እየበረከቱ ስለመምጣታቸው ብዙዎች ይስማሙበታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

HR2003'ን በተመለከተ ያሉ ግራ መጋባቶች (ከአማኑኤል ዘሰላም)

የዲፕሎማሲውን እንቅስቃሴ በተመለከተ አስተያየት

ከአማኑኤል ዘሰላም (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.) ነኀሴ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. (August 13, 2008)

በቅድሚያ HR2003'ን በተመለከተ ሃሳብ ከመወርወሬ በፊት በአጭሩ የአሜሪካንን የመንግሥት መዋቅር በአጭሩ ለማሳየት እሞክራለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጥላቻ-ፖለቲካ ለኢትዮጵያ ህልውና ጠንቅ ነው (ከአብርሃም ያየህ)

ከአብርሃም ያየህ (ሐምሌ 30 ቀን 2000 ዓ.ም. / August 6, 2008)

ባሁኑ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ የቃሚዊው ጎራ፣ የአብዛኛዎቹ ተቃዋሚ ነን ባይ ኃይሎችና ደጋፊዎቻቸው ዋነኛ የማታገያ ስልት ሆኖ በማገልገል ላይ ያለው በጥላቻ የተመሰረተ ፖለቲካ ነው። ይህ መርዘኛና አደገኛ የጥላቻ-ፖለቲካ፣ በትግራይ ስም በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ወይም በገዢው ፓርቲ ብቻ ያተኮረ አይደለም። አትኩሮቱ፣ በጅምላ አጠቃላዩን የትግራይ ህዝብ ዒላማ ያደረገ ነው። የህዝባቸውና ያገራቸው ህልውና የሚከነክናቸው ዜጎች፣ የዚህ አደገኛ በሽታ መዘዙ በትክክል ተረድተው አጥብቀው ካልታገሉት በቀር፣ ሄዶ-ሄዶ በመጨረሻ ኢትዮጵያን በመበተን ያለው ሚና እጅግ ወሳኝ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ነገ ኢህአዴግን ልንደግፍ እንችላለን (ግርማ ካሣ)

ግርማ ካሣ (ቺካጎ) This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. - ሐምሌ 30 ቀን 2000 ዓ.ም.

የቅንጅት ወራሽ ነው ብዬ የማምነው፣ መሰረቱን ኢትዮጵያ ያደረገውንና ሠላማዊ በሆነ መንገድ በኢትዮጵያ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት እየታገለ ያለውን አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ አንደአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እደግፋለሁኝ። አንደ አብዛኛው ኢትዮጵያዊም ኢህአዴግን የምቃወም ሰው ነኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በርግጥ ኢትዮጵያ ላይ ሴራ አለ? (ከኩችዬ)

ኩችዬ (This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. - ጁላይ 30, 2008)

ይህን ጥያቄ የማነሳው ያለ ምክንያት አይደለም። ጥቂት በማልለው የኅብረተሰባችን ክፍልና አልፎ አልፎም ቢሆን በተቃዋሚ ፓርቲዎች አካባቢ ሲንጸባረቅ የማየው የውጭ ፖሊሲ አዝማሚያ ስለሚያሳስበኝ ነው። ክርክሬን አጭርና ደፋር በሆነ ዓረፍተ ነገር ልክፈትና “ታላላቅ መንግሥታት የኢትዮጵያን መጠናከርና አንድነት አይፈልጉም” የሚለው አመለካከት ከዘመናችን የፖለቲካ ጭብጥ ጋር የማይገናዘብ በማስረጃ ያልተደገፈ አጉል ስጋት ነው እላለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወደኋላ የተጓዘው የፕሬስ ሕግ

“ተሻሽሏል” በሚል ሰኔ 24 ቀን 2000 ዓ.ም. (July 1, 2008) በፓርላማው የፀደቀውና አፋኙ የፕሬስ ሕግ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ባሉ ወገኖች ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው መዘገባችን አይዘነጋም። በሀገር ውስጥ በመታተም ላይ ያሉ የግል ፕሬሶች ሕጉን አስመልክቶ ያላቸውን ተቃውሞ በተደጋጋሚ ሲያሱሙ የነበረና አሁንም ድረስ ሕጉ አፋኝ መሆኑን እየገለጹ ቢሆንም፤ ገዥው የኢህአዴግ መንግሥት ግን ጩኸታቸውን ‘ጆሮ ዳባ’ ማለቱ ይታወቃል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...