ትንሽ ድፍረት፤ ራስን ለማየት

ይገረም አለሙ

Sun Tzu, The Art of War

በማናቸውም እንቅስቃሴ የበላይነትን/አሸናፊትን ለመቀዳጀት መሰረታዊ ቁልፍ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ ራስንና ተፎካካሪን/ጠላትን ማወቅ ግንባር ቀደሞች ናቸው። እነዚህን ሁለቱን በሚገባ ሳያውቅ የሚነሳ ወይንም በሂደት እነዚህን ለማወቅ የማይጥር ግለሰብም ይሁን ቡድን ውጤታማ አይሆንም። ይህ ጉዳይ በተለይ በወታደራዊና ፖለቲካዊ ጉዳይ ሲሆን ውድቀቱ በግለሰብና በቡድን ብቻ የሚገታ አይደለም። ለአገርና ለሕዝብ ይተርፋልና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እንኳን ለገና አደረሰን!

Assefa Chaboአሰፋ ጫቦ (Dallas Texas USA)

የፈረንጅ ገና ዋዜማ ዕለት በሆንኩት ልጀምር። ሁለት ወዳጆቼ፤ አንደኛው ከዚሁ ከቨርጂኒያ፤ ሌላው ከሳሳከችዋን፤ ካናዳ ደውሎ ስለበዓሉ ትንሽ ተነጋገርን። እነሱም የሚሰማቸውን እኔም የሚሰማን ያዝ ለቀቅ አደርገነው። “ዞሮ ዞሮ ከቤት!” እንዲሉ ያው ሁሌም ሚዛኑ የኢትዮጵያ ዓመት በዓላት ናቸው። “ባሻ አሸብር ባሜሪካ” መሆንናችን መሰለኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እናት አቤቱታ

Temesgen Desalegne and his mother

ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የልጄ የተመስገን ደሳለኝን ጤንነትና የጉብኝት ሁኔታን ስለማወቅ

የልጄ ተመስገን ደሳለኝን ጉዳይ ይዤ እናንተው ጋር መመላለስ የግድ ሆኖብኝ ዛሬም ከደጃችሁ መጥቻለሁ። ባሕሌና አስተዳደጌ ያስተማረኝ፤ አንድ ቦታ ለአንድ ጉዳይ መመላለስ ለችግሩ ባለቤትም ሆነ ለመፍትሔ ሰጭው አሰልቺ መሆኑን ነው። እውነት ለመናገር ዛሬም ወደ በራፋችሁ ስመጣ እንደው እነዚህን ሰዎች ሥራ እያስፈታኋቸው ይሆን ከሚል ሃፍረት ጋር ነው። ግን ምን ላድርግ? ጉዳዩ ልጅን የሚያኽል የስጋ ክፋይ ነገር ሆነብኝ። እንድትረዱልኝ የምፈልገው እኔም ተቸግሬ እያስቸገርኳችሁ መሆኑን ነው። በተጨማሪም ጭንቀት እረፍት ስላሳጣኝና ጤናዬንም እየፈተነኝ በመሆኑ የመፍትሔ ያለህ እያልኩ አለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያዊነት ስሌት ለነፃነት ብቻ፤ ቀላል አቀራረብ

አቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

Ethiopia

እንደመግቢያ፤

እኔ ከአባቴ የአምቦ ጉደር ሙቱሉ ኦሮሞነቴ ወደኋላ አስር በሚቆጠሩ ዘሮቼ ከአያቴ ተቆጥሮልኝ ባጠናሁት፤ እና በእናቴ ደግሞ ከኮንሶ-ኦሮሞነት በነገረችኝ የዘር ሐረጓ አዲስ አበባ ተወልጄ ባድግም ኢትዮጵያዊነቴን እንጂ፤ አንዳንድ ትግሬነትን እንዳሸመቁበት፣ ጉጅሌው ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ቋንቋ እያስተማረና ለምድ እያለበሰ ሲያሰለጠናቸው በድብቅ ደም እንዳፈሰሱት ለአገር ሻጭ ጀሌዎች የገዳይ ተመልካች አልነበርኩም፤ አልሆንምም። የዚህ ሁሉ መገለፅ ምክንያቱ የኢትዮጵያዊነትን አሊያም የኦሮሞነትንም ሆነ የኤርትራዊነትን ጭምብል አድርገው ነፃነታችንን የሚወጉትን በአደባባይ ለማጋለጥ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለኦህዴድ እና ለብአዴን አባላት

ከአማራና ኦሮሞ ትብብር ይለምልም ፕሮጀክት (አኦትይፕ)

በአሁኑ ወቅት በአገራችን ኢትዮጵያ በተለይም በአማራና በኦሮሚይ ክልሎች ላይ በህወሓት ትእዛዝ እየደረሰ ያለውን የዜጎች ስቃይና እንግልት እያያቹት ነው። በሁለቱም ክልሎቹ የተነሳውን ፀረ-ህወሓት ተቃውሞ በሚገባ የተረዳችሁት መሆን አለበት። የተቃውሞዎቹ መሠረታዊ ጥያቄ የብአዲንና የኦህዲድ የአስተዳደር በደል ሳይሆን፤ የተቃውሞዎቹ መሠረታዊ ጥያቄ የህወሓት የባላይነት ይወገድና ኦህዲድና ብአዲን የህወሓት አገልጋዮች ወይም ሎሌዎች መሆናቸው ያብቃ ነው። ወገን እየሞተና እየተሰቃይ ያለው ለእናንተም ነፃነት እያለ ነው። ህወሓት ነገሩን ለማድበስበስና ለማደናገር ተቃውሞዎቹ በክልሎቹ ባልሥልጣናት የአስተዳደርና የአመራር ብቅት ማነስ የተቀሰቀሱ ናቸው በማለት የሕዝቡን ተቃውሞ ወደክልሎቹ አመራሮች በመወርወር፤ የክልሎቹን አመራር በማተራምስ፤ በየክልሎቹ አመራር መሀከል ቅራኔዎችን በማባባስና በማናቆር፤ አዳዲስ የህወሓት ታዛዥ አባላትን በየድርጅቶቹ በመሰግሰግ የበላይነቱን ለመቀጠል እየጣረ ይገኛል። ይህ የህወሓት መሠሪ ተግባር የነበረ ነው፤ ለወደፊቱም የሚቀጥል ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ኢትዮጵያን አፈራርሰን ኦሮሚያን እንገነጥላለን”

በበታችነት ሕመም የተጠቁ አሳዛኝ ፍጡሮች ባዶ ጩኸት!

ሸግዬ ነብሮ (ኢጆሌ ባሌ)

“አገር አጥፊው አረም በሀገሬ ሲስፋፋ፣
ሁሉም ተዳከመ የሚያርመው ጠፋ፣
የጊዜ ጉዳይ ነው እኔ አለቆርጥም ተስፋ፣
ሀገሬ ነው የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣
ጥቃቱ ይሰማው ሲቆረስ አካሉ።”
ከሊቀ ማዕመራን አበባው ይግዛው “ወይ ሀገሬ” ከሚለው ግጥም የተወሰደ።

የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሥጋ ለመቀራመት በተነሱበት ወቅት በተለያዩ አገሮች እገራቸውን ያስገቡት በኃይማኖት አስተማሪነት ሰም የቄስ ካባ አልብሰው የመረጃ (ሰላይ) ሰዎቻቸውን በመላክ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው፣ የሜቴክ ጉድ ዓይኑን አፍጥጦ ጥርሱን አግጥጦ መጣ

እሸቱ ሆማ ቀኖ

METEC

ጉደኛው ኢሕአዴግ በስኳር ፋብሪካዎች ላይ ያለውን አቋም መሰረታዊ በሆነ መልኩ መቀየሩን የዛሬው የፋና ዜና ገልጿል። የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ መጓተት ያስከተለውን ምስቅልቅል ሜቴክም ሆነ ኢሕአዴግ ሊደብቁት ከማይችሉበት ደረጃ ደርሷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ያልተላከ ደብዳቤ

አሰፋ ጫቦ

Abadula and Hailemariam

“የከሸፈ ደብዳቤ !”ልለው ፈልጌ ተውኩት። ሳይቀባበል አይከሽፍምና ነው!”ከራስ ጋር መነጋገርና ት ዝ ብ ት!” ብዬ ጽፌ የነበረውን አይታችኋል ብዬ እገምታለሁ። እዚያ ላይ በነሐሴ ወር 2008 አንድ “ለመነሻ” የሚሆን ረቂቅ (Prliminary Draft) አዘጋጅቼ ለዚህ ይመጥናሉ ለምላቸው አስራጭቼ ነበር። ሊኖርን ከሚችሉት አማራጮች አንዱ አድርጌ ነበር ያየሁት። ከዚያ “ቄሱም ዝም! መጽሐፉም ዝም!” ሆነብኝ። እንድታውቁት ያክል እንዳለ አሁን ይኸውና አውጣሁት!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

”በኦሮሚያ ያሉ ዞኖች ከፈለጉ ከኦሮሚያ የመውጣት መብት አላቸው” አቶ ቃሲም የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር ቃል አቀባይ

ግርማ ካሳ

Kassim Abbaa Nashaa

ኦቦ ቃሲም ሁሴን አባናሻ፣ ኦቦ ነጋ ጃላ በሊቀመንበርነት፣ ጀነራል ኃይሉ ጎንፋ በምክትል ሊቀመንበርነት የሚመሩት የተባበሩት የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ ናቸው። ላስ ቬጋስ የሚገኘው የሕሊና ራዲዮ ላይ ቀርበው ነበር። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ