አንዳንዴ እናመስግን?

የትነበርክ ታደለ

TV Ads For Alcohol: Do They Increase The Risk For Teenage Drinking Problems?

እናመስግን ይሆን?! ስንቶቻችን በየቤታችን የተንገበገብንበትና በሶሻል ሚዲያ የተንጫጫንበት ቅጥ የለሽና ልክ የለሽ የአልኮል መጠጦች የማስታወቂያ ጋጋታ እንዲገደብ የሚያዝ አዋጅ ሊወጣ ነው እና እናመስግን?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በነገራችን ላይ ‘ውይይቱ’ የት ደረሰ?

ክንፉ አሰፋ

TPLF dialogue

የሙስናውን የመረጃ እጦት ኩምክና ሰምተን ስቀን ሳንጨርስ ሰሞኑን ደግሞ የውይይት ፉገራ አመጡ። ልክ እንደቀበሌ ስብሰባ ተቃዋሚዎችን በአዳራሽ ውስጥ አጉረው ሲያበቁ እነሱ ከመድረክ ሆነው ይቀልዱባቸዋል። የNBC ውን፤ የዴቭድ ሌተርማን 'ሌት ናይት ሾው" (late night show) የሚመስል ነገር በቴሌቭዥን ለቀውብን ነበር። ሁለቱ ባለሥልጣኖች፤ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ እና አቶ አስመላሽ ወልደሥላሴ መድረክ ላይ ጉብ ብለዋል። በአነስተኛና በጥቃቅን የተደራጁ 21 የፓርቲ መሪዎች ደግሞ እንደ ቲያትር ተመልካች አዳራሹ ውስጥ ተሰይመዋል። እነዚያ ከላይ፣ እነዚህ ከታች ተቀምጠዋል። እነዚያ ይናገራሉ፣ እነዚህ ደግሞ ይሰማሉ። ... ሌላ ምን አማራጭ ሊኖራቸው?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከጥልቅ ተሃድሶው ማግስት ዘመቻ ዘ-ፀዓት

ገለታው ዘለቀ

TPLF

ለወትሮው ከገዢው ፓርቲ አካባቢ የተለመደው የተሃድሶ ትርጉም ለየት ያለ ነበር። “ኢህአዴግ” ስብሰባዎችን ያደርግና ሲጨርስ “የተሃድሶ ሰዓት!” ይባልና በዚያን ጊዜ የማእድ አገልግሎትና የተለያዩ መጠጦች የኪነት ትርኢት የሚቀርብበት ሰዓት ተሃድሶ ይባላል። ለአንድ የገዠው ፓርቲ አባል ተሃድሶ ሲባል ቶሎ ወደ ህሊናው የሚመጣው ነገር ድግስ ይመስላል። ከስብሰባ በኋላ ዘና ማለት። ይሁን እንጂ በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጥልቀት በመታደስ ላይ ነን ሲሉ የገለፁ ሲሆን፣ ይህ ተሃድሶ በአዕምሮ መታደስን-መለወጥን የሚያሳይ እንደሆነ ተገልፃልናል። ይሁን ይሏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢኮዋስ Vs ኢጋድ

የትነበርክ ታደለ

 ECOWAS vs IGAD

ተሸናፊው የጋምቢያ ፕሬዚዳንት ያህያ ጃሜይ ከክብር ራሳቸውን አዋርደው አሁን አገር ጥለው ተሰደዋል። ገና የምርጫው ውጤት እንደተገለጸ የገቡትን ቃል አክብረው ውጤቱን በጸጋ እንደተቀበሉ ቢቀጥሉ ኖሮ ለአገራቸውም ለራሳቸውም ክብር ከመሆኑም ባሻገር ለመላው አፍሪካም አንድ የዴሞክራሲ መሰረት ጥለው ባለፉ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቦይ ስብሃት ነጋ የሙስና ወጎች

ክንፉ አሰፋ

Sebhat Nega

በአሜሪካ አገር፤ አንድ ባለሥልጣን በሙስና ሲባልግ እስር ቤት ይገባል። በፊሊፒንስ አገር አንድ ባልሥልጣን የሙስና ወንጀል ቢፈጽም አሜሪካ ይገባል። የኛ አገር ባለግዜ ግን ሙስና ሲሰራ አሜሪካ እየተመላለሰ ይነግዳል። ለግዜው ልዩነቱ የዚህን ያህል ነው። ገለልተኛ የፍትህ አካል ባለበት አገር፤ ሙስና አፍ አውጥቶ አይናገርም፣ እግር አውጥቶም አይራመድም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በማንነት ፖለቲካው ምስቀልቅል የአማራ ብሔረተኛነት ተጽዕኖና ተግዳሮቶቹ

Yusuf Yassinዩሱፍ ያሲን

1. አማራ ከሰኔ (1983) ኮንፊረንስ እስከ ጥቅምት (2009) ስብሰባ
አማራ ወያኔ ኢሕዴአግ በጠራው የአዲስ አበባ 1983ቱ (1991) የሰኔ ኮንፊረንስ አልተወከለም ነበር። በቅርቡ በዋሽንግተኑ የጥቅምት 2009 (2016) በኢትዮጵያ አገራዊ ንቅናቄ (ኢሃን) ስብሰባ ላይም አልተወከለም ተባለ። በሁለቱም ስብሰባዎች አማራ ተገቢ ውክልና አላገኘም ነው አንዱ ቅሬታው። በመጀመሪያው ኮንፊረንስ ውክልና የተነፈገው በብሔረሰቡ ስላልተደራጀ ነው የሚል ምክንያት ነበር በኮንፈረንሱ አዘጋጆች የተሰጠው። ላሁኑ “አለመወከል” የተሰጠው ምክንያትም የአማራ ብሔረተኞችን አላረካም እንዲያውም አስቆጣ እንጂ። እንዲያውም የሚወክለው ሰው ጠፍቶ አማራ ባንድ ሰው ተወክሎ ነበር መባሉን በቅርቡ በሲያትል የተሰበሰቡት የአማራ ድርጅቶች ወኪሎች እንደ ስድብ ነው የቆጠርነው ነበር ያሉት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሁለቱ አርበኞች ሳይጋጩ እንዲኖሩ

ገለታው ዘለቀ

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሕይወት ውስጥ ሁለት ዓይነት የአርበኝነት ስሜቶች ገዝፈው ወጥተዋል። በርግጥ በአንድ አገር ውስጥ የተለያዩ የአርበኝነት ስሜቶች መፈጠራቸው በራሱ የሚያመጣው ችግር የለም። በአንድ ማኅበረሰብ ወይም አገር ውስጥ የአርበኝነት ስሜቶች በተለያየ መንገድ መገለፃቸው የሚያመጣው ችግር የለም ብቻ ሳይሆን ዜጎች የአርበኝነት ስሜት ሲይዛቸው ይህንን ስሜት በነፃነት የሚገልፁበትን መስመር መዘርጋት ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብ ነው። በዚህ በዛሬው ፅሁፍ ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ጎልተው ስለሚታዩት ሁለት የአርበኝነት ስሜቶች እንወያይ። እነዚህ አርበኞች አንደኛ ብሔራዊ አርበኞች ሲሆኑ ሁለተኛ የብሔር አርበኞች ናቸው። ታዲያ እነዚህ አርበኞች ሲጋጩ ይታያል። ለምን ይጋጫሉ? ስለምን ይራራቃሉ? መቼም በአንድ አገር ውስጥ አርበኞች ከተጋጩ በዚያች አገር ውስጥ ሰላምንና ልማትን ማሰብ ወደፊት መራመድን ማሰብ እጅግ ከባድ ነው። አርበኞች እርስ በርስ ከተጠላለፉ መረጋጋት አይኖርም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኮማንድ ፖስት (አዘአኮ)

አንተነህ መርዕድ

በማንኛውም ጊዜና በየትም የዓለም ክፍል የተከሰቱ አምባገነኖች በአንድ ማህፀን ውስጥ እንደተፈጠሩ ፍፁም መንትያዎች (አይደንቲካል ትዊንስ) በገፅታና በባህርይ በጣም ይመሳሰላሉ። አዲስ የተፈጠሩ አምባገነኖች ታሪክ ሆነው ካለፉት ጨካኞች ብዙ ትምህርት ቀስመውና ልቀው ግፍን ያለገደብ በሕዝብ ላይ ይፈፅማሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሀብታሙ አያሌው አሜሪካ መግባት ሳይሆን የሚያስደስተኝ፤ በገዛ አገሩ ላይ መታከም አለመቻሉ ነው የሚያሳዝነኝ

የትነበርክ ታደለ

Habtamu Ayalew

ከሦስት ዓመት በፊት ለአንድ በውጪ ቋንቋ ለሚታተም መጽሔት Seeking Cure Abroad Growing Number of Ethiopians Look for Medical Solutions in Foreign Lands የሚል ጽሁፍ አቅርቤ ነበር።

ይህን ዘገባ በምጽፍበት ወቅት አዲስ አበባ ከተማ በሚገርም ሁኔታ ሞንታርቦ በሚንቀለቀል የድምጽ ብክለት ትታወክ ነበር። ይህ በሚኒባሶችና በአይሱዙዎች የተጫነ ሞንታርቦ የሚያወጣው ድምጽ የሙዚቃ ወይም የቲያትር ማስታወቂያ እንዳይመስላችሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ