የህወሓትን “ሌጋሲ” በጨረፍታ

Meles Zenawi and TPLFተሻለ መንግሥቱ

የወያኔው መንግሥት ያላወረሰን ነገር የለም። ሁለመናችንን እከክ በእከክ አድርጎናል - በቀላሉ በማይድን እከክ አውርሶን ወያኔም እኛም ጣር ላይ እንገኛለን - አሸናፊው ባልለየለት እልህ አስጨራሽ የአውራ ዶሮዎች ጦርነት ተጠምደን።

የመለስና የድርጅቱ የህወሓት ውርስ (ሌጋሲ) በአሥራዎች ቀርቶ በመቶዎች ዓመታትም ተዝቆ የማያልቅ ዕዳ አሸክሞናል። በኢኮኖሚውና በትምህርቱ ረገድ የደረሰብን ኪሣራ ምናልባት በጊዜ ሂደትና ደጋግ ዜጎች የአስተዳደሩን ልጓም ሲይዙ ሊስተካከል ይችላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አገርን የማዳን የመጨረሻ ጥሪ!

ምሕረት ዘገዬ (ከአዲስ አበባ)

TPLF letter

ብዙ የምለው የለም። ከዚህ በታች ያለው በየድረገፆች ተለጥፎ የሚገኘው የሕወሓት አስገዳጅ ደብዳቤ በግልጽ ከሚናገረው እምብዝም የተለዬ ነገር መናገር አይቻልም። ደብዳቤው በራሱ ከበቂ በላይ የሆነ የአገር ዘረፋ መግለጫ ነው። አገር በደብዳቤ እየተዘረፈች ማለቋ ነው። በሕግ ሽፋን የሚደረግ የለዬለት አገርን ራቁት የማስቀረት ዘረፋ እየተካሄደ ነው! ባንክን መዝረፍ፣ ግምጃ ቤትን መዝረፍ፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ የአገርና የሕዝብ ንብረትን መዝረፍ፣ መሬትን መዝረፍ ... ዜጎችን ማሰር፣ ማሰቃየት፣ መግደል፣ ደብዛ ማጥፋት፣ ማስራብ፣ ማጋዝ፣ ማሳደድና ማሰደድ ... መቼም በማይረካ የዘረፋና የግድያ ሱስ ተጠምደው አገርን ማፍረስ የወያኔዎች ልዩ ባሕርይ እንደሆነ ወደ ዕድሜያቸው ጫፍ ደረሱ። እኛም እነሱም ስናሳዝን!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ወያኔ ብቻ ወይስ የውጭ ኃይሎችም ጭምር?

Dr. Fekadu Bekeleፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

መግቢያ

ይህንን ጥያቄ አንድ ስሙን ልጠቅሰው የማልፈልገው ምሁር በኢሜይል ለብዙ ጓደኞቹ በጥያቄ መልክ ሲያስተላልፍ ለእኔም ስላስተላለፈልኝ ይህንን በሚመለከት ቀደም ብዬ በትንተና መልክ ያቀረብኩ ቢሆንም እንደገና ይበልጥ ግልጽ ለማድረግ ይህችን አጭር ትንተና ለመስጠት ቃጣሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

መራራው መረራ

አንተነህ መርዕድ

Prof. Merera Gudina

መረራ ትናንትም ዛሬም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ እንዲሰፍን ተግቶ የታገለና አሁንም የሚታገል የአገር ጀግና ነው። ማሰር፣ ማሰቃየትና መግደል መረራ ጉዲናንና ሌሎችን ኢትዮጵያውያን ዝም የሚያሰኝ፤ አምባገነናዊ አገዛዝንም ባለበት የሚያፀና ቢሆን ኖሮ ደርግ ባልወደቀም ነበር። መረራም ሆነ ሌሎች ኢትዮጵያውያንም ትግላቸውን አላቆሙም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ፍምን እፍ ብትላት ትነዳለች፣ ትፍም ብትልባት ትጠፋለች፣ ሁለቱም ሁሉ ከአንድ አፍ ይወጣሉ” መጽሐፈ ሲራክ ም. ፳፰፣ ቁ. ፲፪

ይገረም አለሙ

ፍም አስፈላጊም አላስፈላጊም የሚሆንበት ወቅትና ምክንያት ይኖራል፣ ይህን ለይቶና ተገንዝቦ እፍንም ትፍንም እንደአግባቡ መጠቀም ውጤታማ ያደርጋል። ይህን ለማድረግ የሚቻለው እንቅስቃሴው ግላዊም ይሁን ድርጅታዊ መነሻውን ያወቀ፣ መሄጃ መንገዱን የለየ፣ መድረሻ ግቡን በግልጽ ያስቀመጠና ለግል ሥልጣንና ጥቅም በማሰብ ሳይሆን አገርንና ህዝብን በማስቀደም ላይ የተመሰረተና በስሜት ሳይሆን በእውነት በግብታዊነት ሳይሆን በእቅድና በስልት የሚከናወን ሲሆን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአቶ አሰፋ ጫቦ የተባ ብዕር - ስለ ነገም ቢናገር

Assefa Chaboይገረም አለሙ

አቶ አሰፋ ጫቦ ከጦቢያ መጽሔት ከህትመት ውጪ መሆን ጋር አብሮ የራቀን ብዕራቸው አልፎ አልፎ በድረ ገጾች ብቅ እያለ እንደናፍቆታችን ባንረካም ከማጣት ይሻል ሆኖን ሰነባብቷል። ሰሞኑን ደግሞ አዘውትረው መከሰት ጀምረዋል እና እሰየው ብለናል። ግና በአብዛኛው የእገሌ ጽሁፍ/ነገር ኮርኩሮኝ እያሉ ብቅ የሚሉ በመሆኑ በቅርቡ ደግሞ ይህን ልጻፍ ብየ አስቤ ሳይሆን ብልጭ ሲልብኝ ወይንም ሲልልኝ ነው የምጽፈው ብለው እቅጩን ስለነገሩን ኮርኳሪ ነገር ከጠፋ ሊጠፉ ነው ብዬ ሰጋሁ። ለነገሩ በኢትዮጵያ ጉዳይ ለተለከፈ ሰው የሚኮረኩረው አይደለም የሚያስቆጣ የሚያስቆጨው ነገር መች ይጠፋና ነው እንደዚህ ማሰቤ ብዬ ራሴን ብታዘበውም ብልጭ ሲል የሚጻፍና ታስቦ የሚጻፍ ልዩነት ስላለው ይህችን መልእክቴን ለመጻፍ ተነሳሳሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የትግሉ ዋና ዓላማ ለሥልጣኔ ወይንስ ሥልጣንን ለመያዝ?

Dr Fekadu Bekeleበሰፊ ምሁራዊ እንቅስቃሴ ያልተደገፈ የፖለቲካ ትግል የሥልጣኔ እንቅፋት ነው!

ፈቃዱ በቀለ (ዶ/ር)

መግቢያ

በአብዛኛዎቹ የሦስተኛው ዓለም ተብለው በሚጠሩ አገሮችና፣ በጠቅላላው የካፒታሊስት አገሮች ተብለው በሚታወቁትና የሳይንስና የቴክኖሎጂ የበላይነትን በተጎናጸፉት አገሮች ያለውን ልዩነት ስንመለከት ልዩነቱ እጅግ ከመስፋቱ የተነሳ እንደዚህ ዐይነቱን የተወሳሰበ ሕብረተሰብ ለመገንባት የብዙ መቶ ዓመታት ሥራ እንደሚያስፈልገን ይታየኛል። በአጠቃላይ ሲታይ የካፒታሊስት አገሮች ይህ ዐይነቱ የዕድገት ደረጃ ላይ ደርሰው ዓለምን መቆጣጠር ሲችሉ እኛን ምን ነካን ብለን የምንጠይቅ ብዙ ላንሆን እንችላለን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአሁኑን ፌዴራል አወቃቀር ግድፈት ለማየት የሐረርን ክልል ብቻ ማየቱ በቂ ነው

Hararግርማ ካሳ

ኅዳር 29 ቀን 2009 የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በሚል በታሪካዊቷ የሐረር ከተማ በዓል ተዘጋጅቶ ነበር። በዝግጅቱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ንግግር አድርገዋል። ይህ ዝግጅት ለአሥራ አንደኛ ጊዜ ሲሆን በሐረር የተከበረው፣ በአሉን የሕዝቦች እኩልነት፣ አብሮ የመኖር የመቻቻል እሴቶችን ለማጎልበት የታሰበ እንደሆነ የገለጹት፣ ጠ/ሚኒስትሩ አሁን ያለውን ሕገ መንግሥት የሕዝቦች የቃል ኪዳን ሰነድ ሲሉም አሞግሰውታል። ቢሆን ደስ ባለን ነበር፤ ግን ሜዳ ላይ ያለው ሁኔታ ካሉት በጣም የተለየ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም (መዝ. 33፡16)

ተሻለ መንግሥቱ

የአየር ጠባይ:- የሰሞኑ ንፋስ ከባድ ነበር። በተለይ ኅዳር 25 እና 26 ሁለቱን ቀናት አዲስ አበባ ብቻ ሣትሆን ብዙ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በኃይለኛ የንፋስ ወጀብ ሲናጡ እንደነበር ከአንዳንድ አካባቢ በተገኙ የሥልክ ልውውጥ መረጃዎች ለመረዳት ተችሏል። ብዙ ደካማ ቤቶች የቆርቆሮ ክዳናቸውን ተነጥቀዋል፤ የወያኔዎች ዜጎችን ከመረጃ ውጪ የማድረግ ዕኩይ ባሕርይ ካስከተለው የዲሾች መነቃቀል ባልተናነሰ ብዙ ዲሾች ተነቃቅለውና አቅጣጫቸውን ስተው ጥቂት የማይባሉ ምሥኪን ዜጎችን ላልታሰበ ወጭ ተዳርገዋል፤ የመብራትና የሥልክ ምሰሦዎች ወድቀው ከኃይል መቋረጥ በተጨማሪ ቀላል የማይባል ጉዳት አድርሰዋል፤ ዛፎች ከሥራቸው ተነቃቅለዋል። ... ንፋሱ በዚህ ብዙም ባልተለመደና ባልተጠበቀም የማፍረስ ተግባሩ ሣይወሰን በተጓዳኝ ባስከተለው የጧትና የማታ ቅዝቃዜው በተለይ ባለጠጋዎችን ብዙ ጆንያ ከሰል እንዲጨርሱ አድርጓቸዋል። ... ሁሉም ነገር ለበጎ ነው ብለን ዝም አልን - ለነገሩ ሌላ ምርጫም አልነበረንም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ