ለሁሉም ጊዜ አለው

ማስተዋል በለጠ

በመላዋ ሀገራችን ለነፃነታችን እየተዋደቁ የሚገኙ ዜጎች ውድ ሕይወታቸውን እየሰው የነፃነት ቀንዲሉን በማብራት ላይ ናቸው። ታሪክ ሲዘክረው የሚኖር ታላቅ መስዋዕትነት እየከፈሉ በመሆናቸው በአልሞ ተኳሽ የወያኔ አጋዚ ጦር አንገታቸው እየታረደና ጭንቅላታቸው እየተገመሰ ሕይወታቸውን የሚያጡ ውድ ወገኖቻችንን ነፍሳቸውን ፈጣሪ ይማርልን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ ያለው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ነውን? (ክፍል ሁለት)

ይገረም አለሙ

በክፍል አንድ ጽሁፌ አንድን ሥርዓት ሕገ መንግሥታዊ ሊያሰኙት የሚበቁ በርካታ ጉዳዮችን ትተን በሕገ መንግሥቱ ላይም የሚነሱ ክርክሮችን አቆይተን ሕገ መንግሥቱ ባለው መልኩ እንኳን የማይከበር አንዳንድ አንቀጾቹም እስከመኖራቸው የማይታወቁ መሆኑ ብቻውን ሥርዓቱን ሕገ መንግሥተዊ ሊያሰኘው እንደማይችል ጠቅሻላሁ። ለዚህ መከራከሪያ ይሆናሉ ያልኳቸውን ጭብጦችም በማንሳት ከሕገ መንግሥቱ አንቀጾች የተወሰኑትን በማስረጃነት ለማቅረብ ነበር የተሰናበትኩት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በኢትዮጵያ ያለው ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ነውን? (ክፍል አንድ)

ይገረም አለሙ

ሕገ መንግሥታዊውን ሥርዓት በኃይል ለማፈረስ የሚል ክስ በሀገራችን ተራና የተለመደ ነገር ከሆነ አመታት ተቆጥረዋል። በስፋት የታወቀው፣ ምን አልባትም የተጀመረው በቅንጅቶች ክስ ይመስለኛል። ለሥልጣን ያሰጋሉ ተብሎ የተገመቱ ዜጎችን በዚህ እየወነጀሉ በመገናኛ ብዙሀን መናገሩንም የጀመሩት አቶ መለስ ናቸው። ለነገሩ ከደደቢት እስከ ምኒልክ ቤተ መንግሥት የተሰራ የተነገረው ሁሉ የአቶ መለስና የአቶ መለስ ብቻ አንደሆነ ተነግሮን የለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ ሆይ ልብ ግዛ! … ህዝብም በእምቢተኝነቱ ይግፋበት!

ያሬድ ኃይለማርያም (ከብራስልስ፣ ቤልጂየም)

ኢትዮጵያ ዛሬ መስቀለኛ መንገድ ላይ ትገኛለች። የወያኔ ግትርነትና መረን የለቀቀ አንባገነናዊነት፣ በሥርዓቱ ተስፋ የቆረጠና የተበሳጨ ሰፊ ህዝብ፣ ለ25 ዓመታት የተጎነጎነ የጎሣ ፖለቲካና ጥላቻ፣ መገለጫ የሌለው ድህነትና ችጋር ሀገሪቱን ሰንገው ይዘዋታል። በአገዛዝ ሥርዓቱ በኩል የሚታየው ህዝብን የመናቅና ከሕግ በላይ የመሆን ዝንባሌ እየከፋ መምጣቱ፤ በሥልጣን ላይ ያሉት ሰዎች አንድም ልባቸው መደፈኑን፤ አለያም ጥልቅ ድንቁርና የተጫጫናቸው መሆኑን ወይም መካር ማጣታቸውን ነው የሚያመላክተው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ለኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጥብቅና

አንዱዓለም ተፈራ - የእስከመቼ አዘጋጅ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን በግሌ አላውቀውም፤ ነገር ግን እስከሚበቃኝ ድረስ አውቀዋለሁ። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ እኔን አያውቀኝም፤ ነገር ግን እኔና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ጠበቆቹ እንዳለን ያውቃል። ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጎንደር ውስጥ አንገረብ እስር ቤት ባሁኗ ሰዓት - ምሽት፣ ረቡዕ ሐምሌ ፳፯ ቀን ፳፻፰ ዓመተ ምህረት - ለጊዜው አለ። እዚያ እንዲቆይ ያደረገው ወገኑ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው፤ በእስር ቤት ያለ ግለሰብ፤ በትክክል ይሁን በድፍረት በመታሰሩ ብቻ፤ ጠበቃ ያስፈልገዋል። እናም ጠበቃው ነኝ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ትግሉን ለህዝባዊ ድል ለማብቃት …

ፊልጶስ

Ethiopians protest (Oromia & Amhara regions) ህዝባዊ ተቃውሞ በኢትዮጵያ (በኦሮሚያና በአማራ ክልል)

አሁን ያለው ህዝባዊ አመጽ በመላው ሀገሪቱ ለመቀጣጥጠል የበቃው የብዙ ወገኖቻችን ሕይወት ቀጥፎ፣ ለእስር፣ ለስደትና ለምድራዊ ስቃይ ዳርጎ ነው።

የ'ስካሁኑ ትግል ለድል ያለበቃው፤ ወያኔ የፈነጨውና ሀገራችንን እስከማፈራረስ ደረጃ የተቃረበበት ዋና ምክንያት፤ ተደራጅተን የጋራ ኃይል ያለመያዛችንና የወያኔን ማንነት ያለመረዳታችን ነው። ወያኔን መነሻውን፣ አሁን ያለበትንና የአጭር ግዜና የረጅም ግዜ መረኀ ግብሩ ካላወቅነው፤ እንዳለፈው የትግል ዓመታት ሁሉ ዛሬም ርስ በርስ መጠላለፍ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ በእሳተገሞራ ጫፍ ላይ ተቀምጣ

Quote of Martin Luther King Jr.ፕ/ር አለማየሁ ገብረማርያም  (ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ)

“በሰላማዊ መንገድ ለውጥ እንዳይመጣ የሚከላከሉ ሁሉ ሞገደኛውን እና የማይቀረውን የአብዮት ማዕበል እንዲያስተናግዱ ይገደዳሉ” ጆን ኤፍ. ኬኔዲ

እንዲፈጸምልህ በምትመኘው ነገር ላይ አስቀድምህ ተጠንቀቅ ምክንያቱም የሚሆነው አይታወቅም የተመኘኸውን ልታገኝ ትችላለህና …

በአሁኑ ጊዜ በሕይወት የሌለው እና የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሓት) ፈላጭ ቆራጭ መሪ የነበረው አምባገነኑ መለስ ዜናዊ አፈር ይቅለለውና የእርሱን አገዛዝ የማይወዱ ተቃዋሚ ኃይሎች ካሉ ወደ ጫካ በመግባት ተዋግተው በማሸነፍ የእርሱ ወሮበላ የአማጺያን ቡድን እ.ኤ.አ በ1991 እንዳደረገው ሁሉ ሥልጣን መያዝ ይችላሉ በማለት ሰላማዊ ዜጎችን ለኃይል በትምከት አመጽ ይገፋፋ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ጠላትን አሳንሶ ማየት፣ የተቃውሞው ጎራ ድክመት

ይገረም አለሙ

ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ / People in Gonder are protesting against Ethiopia's ruling party and land grabs, 31 July 2016.

በዚህ ሳምንት በወጣ በአንድ ድርጅት መግለጫ ውስጥ የተመለከትኳት “ወያኔ የበሰበሰ የሳር ጎጆ ነው” የምትል ቃል ከዓመታት በፊት አንድ ወዳጄ ያጫወተኝን አስታወሰችኝ። ወዳጄ ብሔራዊ ወታደር ሆኖ ያሳለፈ ነው። እንደ ዕድል ሆኖ በሠለጠነበት ማሠልጠኛ ውስጥ ተመርጦ ቀርቶ እዛው ነው የአገልግሎት ግዳጁን የተወጣው - ደዴሳ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የማንነት ፖለቲካ ጠንቆችና የአብሮነት አኗኗሪ መፍትሔ ፍለጋ

Yussuf Yassin. አቶ ዩሱፍ ያሲንዩሱፍ ያሲን (ደን ሐግ)

"It is NOT our differences that divide us. Rather it is our INABILITY to recognize, accept and celebrate those DIFFERENCES." Audre Lorde

ልዩነቶቻችን ውበታችን የሚሆኑት ስናስተናግዳቸው ብቻ ነው፤ አለበለዚያ ያወዛግቡናል ዩሱፍ ያሲን (አርቲክል 2012)

1. የማንነት ጥያቄዎች በየፈርጁና በየመልኩ

እገሌ የሚባል ስብስብ ለመንግሥት ምክር ቤት የማንነት ጥያቄ አቀረበ። እገሌ የሚባለው ደግሞ በዚህ ክልል ሳይሆን በዚኛው ክልል ልካለል አለ። ሌላው እኛ መታወቂያ መለያ አጠራሬ ይህ ነው እንጂ ይህኛው አይደለም። አንደኛው ብሔረሰብ ልዩ ዞን (ኮንሶ) ሌለኛው ክልል (ሲዳማ) ይሰጠኝ የሚል ጥያቄ አቀረበ። ስብስቦች የማንነት ጥያቄያቸው በሕገ መንግሥት መሠረት ለመንግሥት ምክር ቤት አቀረቡ ሲባል እንሰማለን። ይህንን ጥያቄ ያቀረቡ የቅማነት፣ የቁጫ፣ የወልቃይት፣ የዱቤ ብሔረሰብ አባላት ተገደሉ፣ ታሠሩ፣ ተቀጡ፣ ወዘተ ሲባል እንሰማለን። ገሚሱ የማነት ጥያቄ ቀላል መልስ አለው። ገሚሱ ቀላል መልስ የለውም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊነት የብሔር/ብሔረሰብ ጥያቄና ፌዴራሊዝም

ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ

መግቢያ!

አብዮቱ ከፈነዳ ከ1966 ዓ.ም ጀምሮ ህዝባችን ሰላምና እረፍት ማግኘት አልቻለም። አብዮቱ ሲፈነዳ፣ የንጉሳዊ አገዛዝ ሲፈርስ፣ የሱ መሰረት የሆነው የፊዩዳሉ ስርዓት ሲደመሰስ ሰፊው ህዝብ የነፃነት ብርሃንን የማየት ዕድል አጋጥሞት ነበር። እስከተወሰነ ደረጃም ድረስ ነፃነትን በመጎናጸፍ እንደቆመበት የህብረተሰብ ክፍል የየራሱን ማህበራዊ ተቋም መመስረት ችሎ ነበር። ይሁንና ግን ይህ የተጎናጸፈው ድልና የተስፋ ብርሃንን ማየት ከውስጥ ከዚህና ከዚያ ብቅ ባሉ ድርጅቶች፣ ግን ደግሞ ዕውነተኛ ዓላማቸው በማይታወቅ ኃይሎች በመወጠርና ጦርነት ውስጥ እንዲገባ በመገደዱ አገሪቱ እስካሁን ድረስ ጋብ ሊል ያልቻለ ትርምስ ውስጥ እንድትወድቅ ተገደደች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ