አበሻው ባንዲራ - ጎንደር ላይ ታየ!!

ተስፋዬ ገብረአብ

ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ / People in Gonder are protesting against Ethiopia's ruling party and land grabs, 31 July 2016.

እነሆ! በቅፅል ስሙ "አምባሻው" ተብሎ የሚታወቀው "የኢትዮጵያ ባንዲራ" ባለፈው ሰንበት ማለትም ሐምሌ እሁድ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. (ኦገስት 31፣ 2016) ቄሶችና ሼኮች በተገኙበት፣ መቶ ሺህ በሚገመት ህዝብ ሸኚነት የቀብር ሥነሥርዓቱ በበጌምድር ጠቅላይ ግዛት ተፈመ ማለት ይቻል ይሆን? "ምነው ተኛ?" በሚል በሐሜት ድቅቅ አድርገን እንደ ክትፎ ስንከትፈው የሰነበትነው የአማራ ህዝብ ተደራጅቶና ተዘጋጅቶ፣ የቴዎድሮስን ከተማ ሲያንቀጠቅጣት ዋለ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የነፍጠኞች ፖለቲካ

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ታሪካዊው የጎንደር ሰልፍ / People in Gonder are protesting against Ethiopia's ruling party and land grabs, 31 July 2016.

ነፍጠኛነት ባህላችን ነው፤ ፖለቲከኛነት አዲስና ባዕድ የትግል ዘዴ ነው፤ ፖለቲከኛነትና ነፍጠኛነት ተቃራኒ ተግባሮችን ያመለክታሉ፤ ተቃራኒ ተግባሮች አብዛኛውን ጊዜ ተቃራኒ ዘዴዎች ያስፈልጋቸዋል። ለምሳሌ መፍጨትና ማቡካት ተቃራኒ ተግባሮች ናቸው፤ መፍጨት ሲበታትን፣ ማቡካት ሰብስቦ ያያይዛል፤ የሚፈጭ ሰው ማቡካት ይችላል፤ እንዲሁም ማቡካት የሚችል ሰው መፍጨት ይችላል። ፈጪ አቡኪ መሆን የሚችለውን ያህል ወይም አቡኪ ፈጪ መሆን የሚችለውን ያህል፤ ነፍጠኛ ፖለቲከኛ ወይም ፖለቲከኛ ነፍጠኛ መሆን ይችላል ወይ? መልሱ ግልጽ ነው፤ አይችልም። የነፍጠኛ ትግል በጠመንጃ ነው፤ የፖለቲከኛው ትግል በቃላት፣ በንግግር ነው። በሌላ አነጋገር የነፍጠኛ በዱላ፣ የፖለቲከኛ ትግሉ በመላ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ህወሓት የተከለውን የጡት ቆረጣውን ሐውልት አፍርሰን እንጣለው

ዓሊ ጓንጉል

“... ሃያዎቹ መጨረሻ ላይ ያለ፣ በፊቱ የተደፋ፣ እጆቹን ወደፊት ዘርግቶ፣ ... ልብሱ በደም እና አቧራ የጨቀየ ኢትዮጵያዊ ... አስከሬን መንገድ ዳር ወድቋል፣ ሰውየው ጫማ፣ ገንዘብ፣ መታወቂያ የለውም። ለአርብ ጸሎት የሚሄዱት ሰዎች በሚያዩት አዝነዋል፣ ግን የገረማቸው አይመስሉም ...” ይህ በትናንትናው ዕለት (august 31/2016) በኒውስዊክ መጽሔት ላይ ከወጣ የዜና ዘገባ የተወሰደ ነው። ርዕሱ “ጦርነትን የሸሹ የመናዊያን እና ድርቅን የሸሹ ኢትዮጵያዊያን ጅቡቲ ላይ ተገናኙ” ነው የሚለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጎንደሮች ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ ድል

አብርሃም በየነ

የጎንደር አመጽ Protest in Gonder July 31, 2016

የጎንደሮች የመለከት ድምፅ ኢትዮጵያ ነች። የእምቢልታው መስተጋቦ ኢትዮጵያዊነት ነው። የጥሩምባው የክተት ጥሪ የአማራው ህዝብ የህልውና ጥያቄ ነው። ስለሆነም አማራ ለህላዌው፣ ኦሮሞ ለመብቱ፣ ጋምቤላ ለመሬቱ፣ አፋር ላንድነቱ በጠላቱ በወያኔ ላይ የተነስ ጥሪውን ተቀብሎ በጋራ እንዲያምጽ ነጋሪቱ ተጎሹሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዓትን የምትከተል ሀገር አይደለችም

ገለታው ዘለቀ

ኢትዮጵያ ሆይ የአስተዳደር ዘየሽ ምን ይመስላል? ተብላ ብትጠየቅ በዓለም ላይ የፌደራል ሥርዓትን ከሚከተሉ ሀገራት አንዷ ነኝ ስሜም የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት ይባላል ትላለች። በርግጥ በዓለም ላይ ካሉ ብዙዎቹ ሀገራት የፌደራል ሥርዓትን አይከተሉም። ብሪታኒያን ፈረንሳይን ጨምሮ በዴሞክራሲ የበለጸጉ አንዳንድ ሀገራት የአሃዳዊ አስተዳደር ዘየን ይከተላሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አስቸኳይ ወቅታዊ መልዕክት!

ነፃነት ዘለቀ (ኢትዮጵያ)

አሁን ያለንበት ወቅት ለወሬና ለፍልስፍና አመቺ አይደለም። በሞቀንና በበረደን ቁጥር ከያለንበት ሸጥና ጎጥ እየተነሣን በብዕርም ይሁን በአንደበት የምንወራከብበት ወይም እንካስላንትያ የምንገጥመት ወቅት ላይ አይደለንም። ጊዜው የጣር መጨረሻ ነው፤ ዘመኑ የነፃነት ትግል ወቅት ነው። ስለሆነም ከሚያናቁረን ይልቅ የሚያስማማንን ንግግርና ሃሳብ የምንወረውርበት ሊሆን ይገባል። ከእልህና ከስድብ ይልቅ መቻቻልና መግባባት የሠፈነበት የመጨረሻ ምዕራፍ ሊሆን ጊዜው ግድ ይለናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጀግና ልጅ ልደቱ በኀዘንና በመከራ ይከበራል (የማለዳ ወግ)

ነቢዩ ሲራክHabtamu Ayalew with his daughter. ሀብታሙ አያሌው ከልጁ ከህፃን ኤማንዳ ሀብታሙ ጋር

* እንኳንም ተወለድሽ ህፃን ኤማንዳ ሀብታሙ

ዛሬ የወጣቱ አባዎራ ሀብታሙ የአብራክ ክፋይ ህጻን ኤማንዳ ሀብታሙ 4ኛው ዓመት የልደት ቀን መሆኑን ስሰማ ከልብ የመነጨ መልካም ምኞቴን ለመግለጽ፣ ብሎም በሕግ ሽፋን በአባቷ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ግፍ በማውገዝ እንደ ዜጋ ማለት የምለውን ማለት ፈለግኩ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምላሽ ለሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ተንሳይ “የሀገራችን ፖለቲካ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች” ጽሁፍ

ለመፍትሔው መፍትሔ የወያኔ/ህወሓትን ዕድሜ ለማራዘም በሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ተንሳይ የመፍትሔ ሃሳቦች

(የሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ተንሳይን ጽሁፉ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)

ነሲቡ ስብሐት፤ ከሰሜን አሜሪካ

ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ተንሳይን

እነሆ 17 ዓመት በበረሃ 25 ዓመት በመንግሥት ሥልጣን የተቆናጠጠው ወያኔ ዛሬ የሥልጣን ዘመኑ ማብቂያው የመጨረሻው መጀመሪያ ላይ ደርሷል። በትግሉ ላይ ነበርን ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ አመራር እርከን ላይ ነበርን የሚሉ የወያኔ ባለሥልጣን፤ የድርጅታቸውን 17 ዓመት የትግል ጉዞ አብረው ፕሮግራም ሲነድፉ፣ ፖሊሲ ሲያወጡ፣ የትግራይ ነፃ አውጪ ብለው በዘር ሲደራጁ፣ የአማራ የበላይነት ሰፍኗል ብለው አማራ ላይ ሲያነጣጥሩ፣ የብሔር/ብሔረሰቦች መብት እስከመገንጠል ብለው የዘር ፖለቲካ ሲያራምዱ፣ ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ተይዛለች ብለው ከሻዕቢያ ጋር ለኤርትራ ነፃነት ሲታገሉና ሲያታግሉ የነበሩ ዋናው የድርጅቱ አመራር ባልደረባ፤ ዛሬ የወያኔ ወንበር እንዳበቃለት ሲገለጥላቸው “ዕድሜውን እንዴት እናራዝመው?” “ትንታኔአቸውን” አስነብበውናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሀገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦች (ሌ/ጄ ፃድቃን ገ/ትንሳኤ)

ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ

ሌተናል ጄኔራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ Photo – General Tsadkan during an interview with HornAffairs. Feb. 2015

መግቢያ

ከሃያ አምስት ዓመት ኢህአዴግ የደርግን መንግሥት በጦርነት አሸንፎ የሀገራችንን ፖለቲካዊ ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ፤ ቀስ በቀስ እያደጉ የመጡ ፖለቲካዊ ችግሮች በግልፅ ጎልተው መታየት ጀምረዋል። አሁን ገዥው ፖርቲና ፖርቲው የሚመራው መንግሥትም የችግሮቹን መኖር አምኖ ለመፍታት እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ መንገር ከጀመረ ሰነባብቷል። ይህ ሁኔታ ለማንኛውም የሀገሩን ደህንነትና ሰላም፤ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ማህበራዊ ብልፅግና፤ ለሚመኝ ሀገር ወዳድ ዜጋ ያሳስባል። ከዚህ አንፃር የተለያዩ አስተያየቶች እየተደመጡ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ