የኦህዴዱ መሪ ወርቅነህ ገበየሁ ትግሬ ነው፤ ምስጢሩ እነሆ ...

ክንፉ አሰፋ

Workneh Gebeyehu. ወርቅነህ ገበየሁ

ከምርጫው ጥቂት አስቀድሞ የወርቅነህ ገበየሁ አያት ስም ገብረኪዳን ነበር። የቀድሞ ወዳጄ ወርቅነህ የአያቱን ስም ከገብረኪዳን ወደ ኩምሳ ለመቀየር የወሰደበት ግዜ እና ምክንያቱ አላስደነቀኝም። ይህንን የዘር ፖለቲካ ጨዋታ ጠንቅቆ የሚያውቀው ዶ/ር መረራ ጉዲናም የተቃዋሚ እጩ ተመራጭ ነበር። ጉዳዩን ጠንቅቆ ያውቀዋል። በአዲስ አባባ ዩኒቨርሲቲ ፖለቲካ ሣይንስ ፋካልቲ ስንማር ሁለታችንንም በአንድ ክፍል አስተምሮናል። የወርቅነህ ትክክለኛ አያት ስም ያለበት ሰነድም በእጁ አለ። ግን ጉዳዩን አላጋለጠውም። ምናልባት የሙያው ስነ-ምግባር ይህንን ለማድረግ አይፈቅድ ይሆናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከውልደቱ የተበላሸ በዕድገቱ ያልተቃና፤ እንዴት ይታረቃል አሁን በስተርጅና

TPLF. ህወሓት/ወያኔይገረም አለሙ
ከውልደቱ የተበላሸ በዕድገቱ ያልተቃና፤
እንዴት ይታረቃል አሁን በስተርጅና፤

“ይታረቃል” የሚለው ቃል ሁለት ፍቺ አለው፤ በአጭሩ አንዱ እርቅ ሲሆን፣ ሁለተኛው የጎበጠን ማቅናት፣ መስመር የሳተን ማስተካከል ወዘተ ነው። ይህ ጽሁፍ የሚያተኩረው በሁለተኛው ትርጉሙ ላይ ነው። ወያኔ ሊለወጥም ሊስተካከልም ሊታረቅም የሚችል አለመሆኑን ለማሳየት።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ተራራም ይሰረቃል? የራስ ዳሽኑ ፖለቲካ

ክንፉ አሰፋ

Ras Dashin mountain. ራስ ዳሸን ተራራ

ራስ ዳሸን ተራራ ከትግራይ "ክልል" ካርታ የመውጣቱ አሲዮ ቤሌማ በብሔራዊ ቴሌቪዥን ሲነገር፤ "ደፍረውናል! ንቀውናል! ብታምኑም ባታምኑም በቁም ሞተናል!" የሚለው የኮሎኔል መንግሥቱ ንግግር በጆሮዬ ላይ አቃጨለ። ድፍረቱ እና ንቀቱ እንዳለ ሆኖ፣ በቁም የሞቱት ግን እኛ ሳንሆን እነሱ መሆናቸውን የሚያበስር የዜና እወጃ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ “የፌደራል ሥርዓት” ችግሮችና አማራጭ መፍትሔዎች

ገለታው ዘለቀ

Federalism in Ethiopia. የኢትዮጵያ “የፌደራል ሥርዓት” ችግሮችና አማራጭ መፍትሔዎች

እንደ መግቢያ

ከዚህ በፊት “ኢትዮጵያ የፌደራል ሥርዓትን የምትከተል ሀገር አይደለችም” ብዬ ፅፌ ነበር። ዛሬም ትንሽ አዳብሬ በዚሁ ላይ ትንታኔ መስጠት አምሮኛል። ይህ ጽሁፍ ደግሞ እንዲነሳልኝ የፈለኩበት ምክንያት በቅርቡ የህወሓት አንጋፋ ታጋዮች የሆኑት አቶ ስዩም መስፍንና አቶ አባይ ፀሃየ በቅርቡ በኢትዮጵያ “ወቅታዊ” ጉዳይ ላይ የተሰኘ መግለጫ ሰጥተው ነበር። የነዚህን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ንግግር ያዳመጠ ሁሉ የየራሱን ምልከታ ያስቀምጣል። እጅግ ብዙ ሰው ግን አዲስ ነገር የማይገኝበት ወቅታዊ የማይባል ያደርገዋል። ሀገሪቱን ህዝባዊ ተቃውሞ በሚንጥበት በዚህ ሰአት ቢያንስ ስለብሔራዊ መግባባት ስለ ብሔራዊ እርቅ ስለ ይቅርታ ማውራት ተገቢ ነበር። የፖለቲካ መሪ ምንም እንኳን የያዘው አቅጣጫ ለራሱ አዋጭ ቢመስለውም ነገር ግን ህዝብ ካልተቀበለው ራሱን ይመረምራል። ይህ ግን በኛ ሀገር ፖለቲካ አለመታየቱ ያሳዝናል። ሥልጣን ለሚወዱ ባለሥልጣናትም የሥልጣን ዕድሜ የሚጨምረው ይቅርታና መታረም መለወጥ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የእናቶች ለቅሶ ያብቃ!

አንተነህ መርዕድ

Ethiopian mother crying

አንድ እናት ስታለቅስ ሳይ ኢትዮጵያ እንደምታለቅስ ይሰማኛል። በአለፉት አርባ ዓመታት ኢትዮጵያ ወልዳ ያሳደገቻቸው፣ ለነገ ተስፋ ይሆኑኛል ያለቻቸው ወጣት ልጆቿ በአምባገነን ገዥዎቿ ሲቀጠፉ ማቅ ለብሳ አልቅሳለች። እጆቿን ዘርግታና ተንበርክካ አንብታለች። የአምላኳ መልስ ዘገዬ እንጂ መምጣቱ አልቀረም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጠ/ሚ ኃይለማርያም የዘመቻ ትዕዛዝና የአምባገነኖች መመሳሰል

አክሊሉ ወንድአፈራው

PM Hailemariam Desalegn. ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ

የዛሬ አራት ዓመት የህወሓትና የኢህአዴግ የበላይ አዛዥና ናዛዥ አቶ መለስ ዜናዊ ሲያርፉ በቦታቸው የተተኩት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ፤ በትጥቅ ትግል ከተሳተፉት የህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች የተለየ ተመክሮ ያላቸው በመሆናቸው፤ ምናልባት የሀገሪቱን የፖቲካ አቅጣጫ ቀስበቀስ ከፍጹም ፈላጭ ቆራጭነትና ያአፍሪካ ቀንደኛ አፋኝ መንግሥታት ተራ አውጥተው ወደ የህዝብን መብት የማክበር አቅጣጫ ሊያመሩ ይችላሉ የሚል አስተሳሰብ በሰፊው ይሰማ ነበር። “ኢየሱስ ክርስቶስን የተቀበልኩ ክርስቲያን ነኝ” ብለው መናገራቸው ደግሞ፣ ከኃይማኖተቢሱ መለስ ዜናዊ የተሻለ ሰብዓዊ ርህራሄና ፈሪሃ እግዚአብሔር ያሳዩናል ብሎ የጠበቀው ብዙ ሰው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢትዮጵያ ምጥ

ያዬ አበበ

የሦስተኛው ምጥ አዋላጅ ኢህአዴግ ይሳካለት ይሆን?

ኢትዮጵያ ምጥ ላይ ነች። ከዚህ በፊትም ሁለቴ አርግዛ አዋላጆቿ የሚያደርጉትን ስላላወቁ፤ እናት ብዙ ደም ፈሷት ከሞት አፋፍ ድናለች። የሦስተኛው ምጥ አዋላጅ ኢህአዴግ ይሳካለት ይሆን?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የወልቃይት ጥያቄ ሕገ መንግሥታዊነት

ይገረም አለሙ

Map of "Great Republic of Tigray". "የታላቅዋ ትግራይ ካርታ"

የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ መነሳት የጀመረበት ጊዜ ጠያቂዎቹ እንደሚሉት ከወያኔ የሥልጣን ዕድሜ በላይ ነው። ስሙን ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ብሎ፤ ዓላማውን ትግራይን ነጻ ማውጣት አደርጎ የተነሳው ቡድን በለስ ቀንቶት ትግራይን መቆጣጠር ሲችል ቢያንስ በሁለት ምክንያቶች ወደ ቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል መስፋፋትን ነው የመረጠው። አንደኛው ምክንያት ማሸነፍ ከተቻለ በትግራይ ሳይወሰኑ ማዕከላዊ ሥልጣን ለመያዝ፤ ሁለተኛው ደግሞ “ነጻ ሊያወጧት የታገሉላትን” ትግራይ ግዛት ለም መሬቶቸን በማጠቃለል ማስፋት ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወልቃይት፣ ያሬድ ጥበቡና ጄኔራል ጻድቃን

Yared Tibebu. ያሬድ ጥበቡበፍቃዱ ደረጀ

- ጻድቃን እንደ እኛ ሊያስብ ይችላል፣
- ሕጋዊ ማዕቀፎችን እንጠቀም፣
- አዲስ አበባ አድጋለች መጎብኘት ባልችልም፣
- የመለስ ጥሩ ስራ ህወሓትን ከሌሎች ድርጅቶች እኩል አድርጎት መሄዱ ነው

ያሬድ ጥበቡ ኢህዴን የተባለውን ብአዴን ከመሰረቱ ግለሰቦች አንዱ ነበር። ሲታገል ሲታገል ቆየና ከዕለታት አንድ ቀን የዓመት እረፍት ተሰጠው፤ ይህንን የእረፍት ጊዜውን በዋና እንደሚያሰልፍ ቀድሞ የተረዳው ወዲ ዜናዊ፤ ተከዜ ላይ ለምን አንዋኝም ሲል ግብዣ አቀረበለት። ሳያቅማማ ተቀበለው። የመለስ ዜናዊ ጦር እየወጋው ቢሆንም ያሬድ አንዳች ነገር ሳይሰማው ወደ ተከዜ ወንዝ ተጓዘ። እንደደረሱም ጨዋታ ፈረሰ፣ ዳቦ ተቆረሰ። ከዛሬ ጀምሮ የኢህዴን አመራር አይደለህም፤ ሁለት ምርጫዎች አቀረበለት … ብርሀኑ ነጋ የሄደበትን መንገድ መርጦም፤ በፓርት ሱዳን አድርጎ ዲሲ መኖር ከጀመረ 30 ዓመት ሊሞላው የጳጉሜን መጥባት እየተጠባበቀ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በአማራው ክልል ያለው መለስተኛ ጦርነት ሳይባባስ መፍትሔ ይፈለግ

ግርማ ካሳ

- በሰሜን ጎንደር ዞን 145 ወታደሮች ተገድለዋል
- ከአዘዞ ካምፕብቻ 143 ወታደሮች ካምፑን ጥለው እስከነ ትጥቃችው ጠፍተዋል

ህወሓት ለሰላም በሮቹን በሙሉ ስለዘጋ፣ በሰላም የሚታገሉ፣ እንደ አንድነት ያሉ ፓርቲዎችን አግዶ፣ እንደ አንዱዋለም አራጌ፣ ናትናኤል መኮንን ኦልባና ለሌሳ … ያሉ ሰላማዊ የፖለቲካ መሪዎችን አስሮ፣ ምርጫ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ፣ ዜጎች ወደ ማይፈለጉት መስመር ፊታቸውን እንዲያዞሩ ገፋፍቷቸዋል። የሰላም በር ሲዘጋ የአመጽ በር ተከፍቷል። በአሁኑ ወቅት ምንም መሸፋፈን አያስፈለግም፤ በተለይም በአማራው ክልል በአሁኑ ጊዜ መለስተኛ ጦርነት ነው ያለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ