“በስመ ተቃዋሚ ተቃቅፎ መሳሳም” - ለትልቁ ዓላማ?

(ሶሊያና ሽመልስ /Soli S Gebremichael - Zone 9)

ከጥቂት ጊዜያት በፌት አንድ የመጽሐፍ ዳሰሳ ዝግጅት ላይ ተገኝቼ ነበር። መጽሐፉ “ፌኒክሷ ዛሬም፣ ሞታም ታንቀላፋለች” ሲሆን ጸሐፊዋ የቀድሞው የሕወሓት አባልና አመራር የአቶ ገብሩ አስራት ባለቤት ወ/ሮ ውብማር ናቸው። በዳሰሳው ወቅት በትግል ጊዜ ለምን መጽሐፉ ላይ የተጠቀሱትን ችግሮች እንዳልፈቱ ሲጠየቁ ወይዘሮዋ እንዲህ ብለው መልሰው ነበር።

“ደርግን የሚያህል ጠላት ከፊት ለፊታችን እያለ እንዴት እርስ በርስ በመጣላት ጊዜ እናባክናለን? ነጻ ስንወጣ የሕወሓት ፖሊሲና ፕሮግራም ሁሉንም ነገር ይፈታዋል።” ብለን ተውነው ይላሉ።

በኋላ ላይ ደግሞ ሕወሓትን ስለመለወጥ ሲጠየቁ ‹‹ሕወሓት ከዚህ በኋላ የሚለወጥ ድርጅት አይደለም አርጅቷል። 40 ዓመት በኋላ የድርጅት ባሕሪይ አይቀየርም›› ሲሉ ይከራከራሉ።

የትኛው ጠላት? የትኛው ትልቁ ዓላማ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ ወያኔ እና የሚዘረፈው ሰራዊት

መሳይ መኮንን

ዛሬ ለኢሳት የደረሰው ጥብቅ መረጃ 11ዓመታትን ወደ ኋላ በትዝታ ወሰደኝ። ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከዋናው ጸሀፊ ቢሮ አፈትልኮ የወጣው መረጃ እንደሚያጋልጠው ለሰላም አስከባሪ 11 ሺህ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሚከፈለው ደምወዝ ከ90 በመቶ በላይ የህወሀት ካዝና ውስጥ የሚገባ ነው። በወር 13 ሚሊዮን ዶላር(500 ሚሊዮን ብር ገደማ) የወታደሩን ገንዘብ ህወሀቶች ይቀራመቱታል። ይህን ጉዳይ የመንግስታቱ ድርጅት የሚያውቀው ይመስለኛል። ለዚህም እኔ የተሳተፍኩበትን የሰላም አስከባሪ ዘመቻ አጋጣሚ በአስረጂነት ማሳየት እችላለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአዲሱ ህወሓት መንግሥት መጥፎ አጋጣሚ

ኤርሚያስ ለገሠ (ክፍል-1)

1 - ደስታ እና ሀዘን

ሰሞኑን ፍቺ በፍቺ ሆነናል። የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን ከፊል አካል ተፈታ። ደስ አለን። የተፈቱት ካልተፈቱት ያላቸው ልዩነት ለብዙዎች ግራ ቢያጋባም!…ዛሬ ደግሞ እነ ሀብታሙ አያሌው ተፈተዋል። ይህም በግለሰብ ደረጃ ደስ የሚል ዜና ነው። ቢያንስ በቅርብ የማውቀው ሀብታሙ (” ሀብትሽ!”) ክፋ ደጉን የማታውቀው ልጁ እጁ ላይ ስታንቀላፋ፣ ወደ አልጋዋ ወስዶ ሲያስተኛት፣ ከእንቅልፏ ስትነቃ አቅፎ ሊያነሳት በመቻሉ ደስ ይለኛል። እንኳን ለዚህ አበቃህም ማለት እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኦባማ የአፍሪካን ገዢዎች እያዋዛ ደቆሳቸው!

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም

ኦባማ በአፍሪካ ኅብረት ያደረገው ንግግር ብዙ ጥያቄዎችን መልሷል፤ የኦባማ ጉብኝት ያስከተለው ጫጫታ ሁሉ መልስ አገኘ፤ የሰው ልጆች በመሀከላቸው ምንም ዓይነት የአድልዎ ልዩነት ሳይደረግባቸው በሰውነታቸው ብቻ በተፈጥሮ ያገኙትን ክብራቸውንና መገሣቸውን አስከብረው መኖር እንዳለባቸው በአጽንኦት ተናገረ፤

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዝዋይ እስር ቤት

ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም

ሐምሌ 16/2007 ዓ.ም. ለአሥር ወራት በእስር ላይ የቆየውን ጋዜጠኛ፣ ተመስገን ደሳለኝን (ከኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ዝምድና የለውም፤) ለመጠየቅ ወደዝዋይ ወህኔ ቤት ሄጄ ነበር፤ የወሕኒ ቤቱ ባለቤቶች ማረሚያ ቤት ይሉታል፤ ማረሚያ ቤት ማለት ሀሳቡን በነጻነት የሚገልጽና በሀሳቡም ከወያኔ ጋር በሎሌነት ለመተዳደር የማያመች ሲሆን የቀናውን በጉልበት የሚያጎብጡበት ማለታቸው ነው፤ ማረም ማለት ቀጥታውን ማጉበጥ ነው፤ እንዴት እንደሚያጎብጡት ላሳያችሁ፤--

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በበጋው ወር ፍራንክፈርት ትጣራለች

ዮሃንስ ደሳለኝ (ፍራንክፈርት - ጀርመን)

መቼም ማንም ልብ እንደሚለው ሞቃታማው የሐምሌ ወር ገና ብቅ ሲል ነው ጀርመናውያን በበጋ አለባበስ ደምቀው የሚታዮት።

የዘንድሮው በጋ (sommer, auf Deutsch) ወር ገና ሰኔ አጋማሽ ለይ ነበር ወበቁን የጀመረው ፣ ቀኑ እየጨመረ ወደ ዋናው በጋ ሲገባ ነዋሪውም የአለባበስ ሁኔታውን ከዕለቱ አየር ሁኔታ ጋር እየቃኘ ስያስኬደው አጀብ ያሰኛል ፣ አንዳንዶቹማ ከወገብ በታች ለመከለል ሲባል ብቻ ከሚጠለቅ አልባሳት ውጭ የላይኛውን የሰውነት ክፍል ማራቆት የለመዱትና የግድ የሆነ ድርጊት ነው፣ አሊያ ግለቱ እንኩዋን በልብስ በእርቃንም አቅል ያስታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የነጻነት ትግል መጀመሪያው የቀና ልቦና ባለቤትነት ነው

Magdalaወለላዬ ከስዊድን

አፄ ቴዎድሮስ ያሠሩትን መድፍ (ሴባስቶፖል) ወደ ተራራው አናት ለማውጣት እየተጣደፉ ነው። እሳቸው ጭምር በጉልበት እያገዙ ሲገፋ ውለው ረፋዱ ላይ ከሰፈር ደርሰው ሲመለሱ አንዱ መድፉን ከሚገፉት ተለይቶ ወደ ሰፈር ሲወርድ መንገድ ያገኙትና ቆም ብለው ወዴት ነው ሥራ ትተህ የምትሄድ? ብለው ይጠይቁታል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እናት ኢትዮጵያ አደይ ኤርትራ

ከአንተነህ መርዕድ (ሚያዝያ 2007)
መሳይ መኮንንና ፋሲል የኔዓለም ወደ ኤርትራ ያደረጉት ጉዞ የብዙ ኢትዮጵያውያንን እንዲሁም የኤርትራውያን ወንድምና እህቶች ቀልብ መሳቡ እሙን ነው። በተለይም የፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቃለ መጠይቅ በብዙ መልኩ አስደምሞናል። እድላችን የተቆራኘነውና መነጋገሩና መብሰልሰሉ የሚገባ በመሆኑ ያለፍንበትን ሁሉ በትዝታ እንድፈትሽና አሁን የደረስንበትን እንዳይ ምክንያት ሆኖኛል። ነገሮችን ውስብስብና አጠቃላይ ከሆነ መልኩ ይልቅ ተጨባጭ ከሆኑ የግል ገጠመኞች ዙርያ ማውጋቱ የበለጠ ጉልህ ያደርገዋልና አንባቢዎቼም የራሳችሁ ገጠመኝ ዙርያ እየተሽከረከራችሁ የእኔን እንድትካፈሉ እጋብዛለሁ። በዚህ መልኩ ከምን ተነስተን የት እንዳለን ይታየናል። ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኢህአዴግ ዕድሜ ስንት ነው?

ዮሃንሰ ደሳለኝ (ጋዜጠኛ)

ወዲህ የሁለት ክርስቲያን ወዲህ ደግሞ የሁለት ወገን ደም እንዳይፈስ ቅዱሳን አባቶቻችን በፀሎትና በሽምግልና የተጉበት ጉዳይ ፍሬ አፍርቶ ከዛግዌ ሥርዎመንግሥት ወደ ሰለሞናዊ ሥርዎመንግሥት በሰላም ተሸጋገረች።ያለ ጠብታ ደም ይህ ከሆነ ስምንት መቶ ዓመታት ተቆጠረ። ከዚያ ወዲህ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ህዝብ እንደናፈቀው ገዥዎች እንደተሳለቁበት እነሆ ወያኔ ደራሲው አዘጋጁና ተዋናዩ የሆነበት "ምርጫ" ከፊታችን ቆሟል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የመሪዎች እንባ

ወለላዬ

PM Hailemariam Desalegn. ጠ/ሚ ኃይለማርያም ደሳለኝ

ከስም ልጀምር፣ የዛሬ ወጣቶች በተለይ ዘፋኞች ስማቸው በመጠኑ ተቆርጦ ወይም አንሶ ሲጠሩ እየሰማን ነው፤ ቴዎድሮስ - ቴዲ ብዙ ባያስከፋም ተያይዘው የቀጠሉት ዘፋኞች ግን እስከ አባታቸው ስለሚያሳንሱት ኢትጵያዊ ስም መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ የሆነብኝ ጊዜ አለ። እስቲ አሁን ጃህ ሉድ አጥሮ ነው ወይስ ተቆርጦ ቻቺ፣ ጃኪ፣ ጂጂ፣ አቢ፣ ኢሚ፣ ዮሲ፣ ጃኪ-ጎሲ፣ ሚሊ፣ ሚኪ፣ ዮኒ፣ ... ልተዋቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ