ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና አውራምባ ታይምስ

ግርማ ካሳ

ከዶ/ር ብርሃኑ ጋር አንድ ወቅት፣ የቅንጅት አመራር አባል የነበሩ ጊዜ በጣም ወዳጆች ነበርን። ላለፉት አምስት አመታት ግን ተራራቅን። አለመስማማት በመካከላችን ተፈጠረ። እርሳቸው አንድ መንገድ ያዙ። የጦርነት መንገድ! ከማይመቹን ቡድኖች ጋር ማበር ጀመሩ። በተለያዩ ጊዜያት የሚመሩት ድርጅት የሚያራምዳቸውን ፖሊሲዎችን መንቀፍ ጀመርን። የፖለቲካ ልዩነት ባህል ብዙ ያልገባቸው የርሳቸው ደጋፊዎች ተነሱብን። "ግንቦት ሰባትን ለምን ትናገራላችሁ?" በሚል ወያኔ ተባልን።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኃይል መቋረጥ እያስከተለ ያለው ቀውስ

ተሻለ መንግሥቱ

ይህን ጦማር የምጽፈው፣ እንደልዩ ዕድል ወይም አጋጣሚ ሆኖ ከንፍሮ ውስጥ ጥሬ እንደሚገኝ ሁሉ በወያኔ መንደር ውስጥ ስለሀገራቸው የሚጨነቁ በጣት የሚቆጠሩ ባለሥልጣናትና የሥራ ኃላፊዎች ቢኖሩ "ሕዝቦቻቸው" በምን ዓይነት ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ተረድተው ችግሩን ለመቅረፍ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ለመማጸን ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ስለኢሳት ለኢትዮጵያውያን የተላከ መልዕክት

ዳግማዊ ጉዱ ካሣ

ኢትዮጵያ ሀገራችን የለየላት የዜጎቿ እሥር ቤት ከሆነች በጥቂቱ 22 ዓመታት አለፉ። ከ22 ዓመታት በፊት የነበረው ሥርዓተ መንግሥቷ አሳሪና ገዳይ ቢሆንም እንደሥርዓትና የገዢዎቹም ማንነት እንደሀገራዊ ስብዕና ሥርዓተ መንግሥቱ በኢትዮጵያዊ ወገናዊነቱ የማይታማ፣ የመንግሥት አገልጋዮችም በሀገር ወዳድነታቸው ጥያቄ ውስጥ የማይገቡ ከደነዝነታቸውና ድንቁርናን መሠረት ካደረገው ዕብሪታቸው በስተቀር ሌላ ጠላት የሌላቸው ገልቱ ሥርዓትና ጨካኝ ኢትዮጵያውያን ባለሥልጣናት እንደነበሩን የምናስታውሰው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምክር ቤቱ በቀኝ ክንፍ ሲያጠቃ ዋለ

ግርማ ሠይፉ ማሩ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሦስተኛ ዓመት ሁለተኛው ዓመት አጋማሽ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ መለስ ዜናዊ በሞት መለየት መንስዔ ከገባበት የሀዘን ድባብ ተላቆ ከወትሮ በተሻለ መነቃቃት እየታየበት እንደሆነ ይታመናል። ይህ እውነት ቢሆንም አንዳንዶች ምንም አዲስ ነገር የለም ይላሉ (የአዲስ አድማስን "ፓርላማው ጥርስ አወጣ" ዘገባን ልብ ይሉዋል።) አዲስ ነገር መኖሩ ግን እየታየ ያለ አውነት ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ይድረስ ለኔልሰን "ሮሊህላህላ" ማንዴላ!

(ቴዲ - ከአትላንታ)

ነፍስ ውጪ ነፍስ ግቢ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉሰማሁ። ታዲያ እስከዛሬ ስንቀራፈፍ ልነግርዎት ያሰብኩትን ሳልነግርዎ ነገር ቢበላሽ ጸጸት እንዳይሰማኝ ስል፣ በህይወት እያሉ ይቺን ጦማር ልልክልዎ ወደድኩ። ሆስፒታልዎ ውስጥ፣ አልጋዎ አጠገብ ደርሳ ያዩዋታል ብዬም ተስፋ አደርጋለሁ። ካልሆነም በመንፈስዎ ስሜቴ ይድረስዎ!

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዓባይና የአሜሪካ ጨዋታ

(/መስፍን/ማርያም)

በአሥራ ዘጠነኛው ምዕተ-ዓመት አስተሳሰብ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሰው ዓላማ ለአውሮፓ ቄሣራውያን ዋና ግባቸው ሆኖ እስከ ሃያኛው ምዕተ-ዓመት ዘልቆአል፤ አሀን ፈጽሞ በተለየ ዘመን አሜሪካ ይህንን አስተሳሰብ ይዞ የተነሣ ይመስላል። ኢትዮጵያን የተቆጣጠረ ዓባይን ይቆጣጠራል፤ ዓባይን የተቆጣጠረ ግብጽን ይቆጣጠራል፤ ግብጽን የተቆጣጠረ ኃይል ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር ይቆጣጠራል፤ ቀይ ባሕርን ከመግቢያና መውጫው ጋር የተቆጣጠረ ኃይል ዓለምን ይቆጣጠራል

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. እና ኢትዮጵያ

ገብረመድህን አርአያ (ከአውስትራሊያ)

ወደ ግንቦት 20ቀን, 1983 ዓ.ም. ከመግባታችን በፊት ትንሽ ወደ ኋላ መለስ በማለት የደርግ ስርዓትን በትንሹ እንቃኘው።

ደርግ
የካቲት ወር 1966 ዓ.ም. የዘውድ አገዛዙን ስርዓት በመቃወም በአርሶ አደሩ፣ በተማሪው፣ በአስተማሪው፣ በመንግስት ሰራተኛው፣ በወዛደሩ፣ በነጋዴው እና በመለዮ ለባሹ ወዘተ፣ ወዘተ የተቀጣጠለው ህዝባዊ አመጽ ጊዜ ሳይወስድበት በ6 ወራት ውስጥ የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ግቡን መታ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኛ ነገር፡ የአባይ ችግር፡ የአያልሰው ምክር

ተክለሚካኤል አበበ

ክፍል 4 (ክፍል ሁለትና ሶስት ይመጣሉ)

1. ብዜ ግዜ የአቶ አያልሰው ደሴ ጽሁፎች ረዣዥሞች ስለሆኑ፤ እንዲሁም ክፍል ስለሚበዛቸው (1፣ 2፣ 3፣ 4፣ ...)፤ ርእሳቸውን ብቻ እያየሁ አልፋቸው ነበር። በዚህ በአባይ ጉዳይ ግን የጻፉት አነበብኩት። ጽሁፉ በርስ በርስ ቅራኔ የሚንተከተክና በኢህአዴግ የአባይ ግድብ ማጭበርበሪያ ዘመቻ ዙሪያ ያለውን ተቃውሞ በቅጡ ያልዳሰሰ፣ ይልቅስ ሌሎችን ተቺዎች በሚከስበት ደዌ ክፉኛ የታመመ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በተጨማሪም ጽሁፉ የአካባቢውን ፖለቲካ በቅጡ የቃኘ ቢሆንም፤ የደረሰባቸው ድምዳሜዎች ግን የተሳሳቱ ናቸው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዛሬ ደግሞ…(ሊያነቡት የሚገባ)

/መስፍን/ማርያም

ጦርነት እንኳን ገና በልቶ ላልጠገበ ሕዝብና ለጥጋበኞቹም አይመችም፤ የተራበ ሕዝብ በጠገቡ መሪዎች ሲነዳ ግን ጦርነት ለአጉል ጀብደኛነት ዝና የሚጠቅም መስሎ ይታያቸዋል፤ ከኤርትራ ጋር ጦርነት ለመግጠም በሚያሰፈስፉበት ጊዜ በርቱ እያሉ የሚያቅራሩሞ ልተውነበር፤ ዛሬ አቀራሪዎቹም ሆኑ ጀብደኖቹ በኤርትራ ጦርነትያ ለቀባሪ ስለቀሩት ሰዎች፣ ጠዋሪ ስላጡ እናቶችና አባቶች፣ አሳዳጊ ስለሌላቸው ልጆችና አካለ-ጎደሎ ለሆኑት የሚያስብላቸው አለወይ? የአቡነ ጴጥሮስ ሐውልት መነሣትና በኢጣልያ የግራዚያኒ ሐውልት እንዳይሠራ የተጠራውን ሰላማዊ ሰልፍ ከልክሎ ለሰልፍ የወጡትን አስሮ ያሳደረ አገዛዝ ለአገራቸው ለሞቱት ኢትዮጵያውያን የሚሰጠውን ዋጋ በመጠኑም ቢሆን ያሳያል፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን አገራቸውን ሲወዱ ራሳቸው በልጽገው ለልጆቻቸው ብልጽግና እንዲያወርሱ ሕይወታቸውን ቢጠብቁ ለአገራቸውም ክብር ይሆናሉ፡፡

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ