ግንቦት ሃያ ሲመጣ

ዳዊት ከበደ ወየሳ (አትላንታ)

ግንቦት 20 በየአመቱ ሲመጣ፤ በብዙዎች ህሊና ውስጥ የተለያዩ ስሜቶች ይመላለሳሉ - ለሚያስደስተው ደስታ፤ ለሚያዝነውም ሃዘን። ሁሉም በየራሱ መንገድ ግንቦት ሃያን ሊያስታውሰው ይችላል። ግንቦት ሃያን በተለየ መንገድ ከሚያስቡት አንዱ የሆነው፤ የኢህአዴግ ፕሮፓጋንዳ ማሽን ኢቲቪ ይህንን ቀን የሚገርም ውሸት እና ቅጥፈት በማስተላለፍ ያሳልፈዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በየፊናችን እየተማረርን መማራችን ለበጎ ነው

ይነጋል በላቸው

እቲ ናይ ቀደም ሰላም ዘመን ክምለስ፤

ሰላም ኢልና ንዝመር ብሃደ መንፈስ። ...
(ከኤርትራው ተወላጅ ድምጻዊ ርዕሶም ገ/እግዚአብሔር የዘፈን ግጥም የተወሰደ)

ይሄ ኢሣት የሚባል ቴሌቪዥን በትዝታ ባህር እያስዋኘ ጊዜየንም ዕንባየንም እያስጨረሰኝ ነው። በግማሽ ሜትር ርቀት እሱው ጋ - እቲቪው አጠገብ - ከተደቀንኩ የሚያስነሳኝ የለም። ቤቴ ሁሌ በአምባጓሮ እንደታመሰ ነው። ቤተሰብ የሚፈልገውና እኔ የምፈልገው ለየቅል በመሆኑ ትንሹ አምባገነን ሆኛለሁ። ለነገሩ አምባነንነት የሚጀምረው ከቤት ነውና ይቺ ተፅዕኖየ እየተሰማችኝ መጥታለች። ምን ላድርግ?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

እጀ ብልህ መሪና ደጋፊዎቹ

ታክሎ ተሾመ

አገራችን ኢትዮጵያን አስመልክቶ በድርጅት፤ በቡድን፤ በተናጥል የሚደረጉ የመፈክር እንቅስቃሴ መኖራቸው ያለና የሚጠበቅ ነው። በሁሉም ዘንድ የሚደረጉ መፈክሮች የሩቅና የቅርብ ዓላማን የሚያመላክት መሪ ቃል ቢሆንም ፍሬ ቃሉ በሁሉም ዘንድ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም የመፈክሮችን ይዘት ድርጅቶችም ሆነ ደጋፊዎች የሩቁንም ሆነ የቅርቡን ዓላማ ሳያሳኩ መንገድ ላይ ወደ ኋላ መመለስ የሚታይበት አጋጣሚ ብዙ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ብሔራዊ ስሜትን ያልተላበሰ ተቃውሞ

ዐባይ ግድብ Abay damስሜነህ ታምራት (ከስዊድን)

ከጥቂት ሣምንታት በፊት ለዐባይ ግድብ ማስፈጸሚያ የሚውል የገንዘብ ማስገኛ ስብሰባን ለማደናቀፍ በኖርዌይ ሁለት ተቃውሞዎች ተደርገዋል። ለዚህ ጽሑፍ መነሻ የሆነኝ ይህ ሚዛን የጎደለው ተቃውሞ ብቻ ሳይሆን፤ ይልቁንም ተቃዋሚዎቹ ከስዊድን ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ "እኛ የኖርዌይ ጀግኖች ነን!" ሲሉ መደመጣቸው ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሰማያዊ ፓርቲ ጥሪ ከወዲሁ ያስመዘገባቸው ድሎች

ግርማ ካሳ

አገር ውስጥ በሰላም የሚንቀሳቀሰው የሰማያዊ ፓርቲ፣ ግንቦት 17 ቀን 2005 ዓ.ም.፣ በአፍሪካ ሕብረት ጽ/ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አውጇል። ከግንቦት 15 እስከ 17 ባሉት ቀናት ደግሞ፣ ኢትዮጵያውያን ጥቁር አልባሳት በመልበስ፣ አገዛዙ በሚያራምዳቸውን ጎጂ ተግባራት ላይ፣ ያላቸውን ተቃውሞ እንዲገልጹ ጥሪ አስተላልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የሙስናው እስር ምስጢር!

አዲስጉዳይ መጽሔት ቅጽ 7፣ ቁ. 164 Addis Guday ማረ በላዎቹ ርስ-በርስ ተበላሉ!

ሰሎሞን ተሰማ ጂ. 

ለብዙዎች "ሙስና" የሚለው ቃል በ1989 ዓ.ም ወዲህ የተፈጠረ ሃይለ-ቃል ይመስላቸዋል። ነገር ግን አይደለም። ቃሉ ግዕዝ ነው። ትርጉሙም፣ "ጥፋት" ማለት ነው። በአማረኛም የኖረ ሕዝባዊ ግጥም/አባባል አለ፤ እንዲህ የሚል ነው።

"የከንሯ ለዛ፣ የጉንጯ ሙስና፤
"ዐርብ ሮብ ያስክዳል፣ እንኳን ዐሙስንና።" ይላል - አዝማሪም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የኛ ነገር፡ የኔም ነገር፤ አንድ

 ተክለሚካኤል አበበ (ቶሮንቶ ካናዳ)

1.   እስኪ ደግሞ ትንሽ ልረብሽ። ጽሁፍ ተሸፋፍነው የተቀመጡ ሀሳቦችን ካልገለባበጠ፤ ያንቀላፉትንም ካልረበሸ አይመቸኝም።

2.   አንዳንድ ጠንካራ ምሳሌያዊ አባባሎች በአንድ ሀይማኖት ውስጥ ቢነገሩም፤ መልእክታቸውን የሀይማኖት ድንበር አይወስነውም። ጠቀሜታቸውን ሳይንስና ስልጣኔም አይሽረውም። በአሸዋላይና በአለት ላይ ስለሚገነባ ቤት ጽናት ልዩነት ቅዱስ መጽሀፍ የተናገረውን መጥቀስ ይቻላል። ቃልበቃል አላስታውሰውም፤ ግን እምነታችን በጠንካራና በማይናወጽ አለት ላይ የተመሰረተ እንዲሆን፤ በፈተናና በጥርጣሬ፤ እንዲሁም በጽናት እጥረት እንዳይበረዝ ሲያስጠነቀቅ፤ መጽሀፍ ቅዱስበአለት ላይ የታነጸ ቤት በአሸዋ ላይ እንደ ተገነባ ቤት ንፋስና ወጀብ አያናወጠውምአይነት ነገር ይላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ዱላ መመከት ያቃተው አማራ

ይኸነው አንተሁነኝ

ህወሓት ሀገራችንን በገልበቱ መግዛት ከጀመረበት ግንቦት 1983 ዓ/ም ጀምሮ ለቁጥር የሚያታክቱ ለመስማት የሚያስጨንቁ ብዙ ቁም ስቅሎችን ፈጽሟል። የራሱን የህወሓትን ፓርላማ አንቀጽ 39ን በመመርኮዝ ራስን የመቻል ጥያቄ አቅርባችኋል ወይም ልታቀርቡ አስባችኋል በሚል ሰበብ ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ የስቃይ ዘመናትን አሳልፏል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓባይ ወንዝ ዙሪያ ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋል

ፍቅር ለይኩን

በቅርቡ ሙስጠፋ አል ላባድ የተባለ ሊባኖሳዊ ፖለቲከኛና ጸሐፊ Egypt is Battling Ethiopia over the Nile Water በሚል ርዕስ አንድ መጽሐፍ አሳትሞ አውጥቷል። ይህን የአል ላባድን መጽሐፍ "አስ ሳፊር" የተባለ የሊባኖስ ዕለታዊውና ተነባቢ የዐረብኛ ጋዜጣ የመጽሐፉን አጭር ዳሰሳ በፊት ለፊት ገጹ ይዞ ወጥቶ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የ"ኢሕአዴግ ደጋፊዎች" መልካም እንቅስቃሴ

ግርማ ካሳ

በዳያስፖራ ቀንደኛ የኢሕአዴግ ደጋፊና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች አስተባባሪ የሚባሉት፣ የሲቪሊቲ ፓልቶክ ክፍል ዋና አድሚን፣ አቶ ብርሃኑ ዳምጤ (አባ መላ) ከአውራምባ ታይምሱ ዳዊት ከበደ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ አደመጥኩ። አባ መላ ጠንካራ ትችት በኢሕአዴግ ላይ ሰንዝረዋል። ይሄም ብዙዎችን ሳያስገርም አልቀረም። "አባ መላ፣ አራዳ ነው፤ ወያኔ ሊወድቅ ሲል ፍሬቻ አብሮቶ ታጠፈ" ያሉም አሉ። ፡) ፡) እኔ ግን ብዙ አላስገረመኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ