ተገፊዎች የባህሪ ለውጥ አምጡ እንጂ!

ገለታው ዘለቀ

ልትታተም ካሰበች አንዲት ልቦለድ ጽሁፍ ላይ አንድ የምናብ ሰው ከተገረመበት ነገር ተነስተን አጭር መልእክት ለማቀበል እንሞክራለን። ይህ የምናብ ሰው ወደ አንድ ሃገር ይሄድና በዚያ በአንድ ሆቴል ውስጥ ተቀምጦ ናሽናል ጂኦግራፊ የተሰኘውን የቴሌቪዥን ፕሮግራም ያያል። በወቅቱ ይተላለፍ የነበረው ፕሮግራም የዱር እንስሶች ኑሮ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወያኔ ህወሓት ያልከበደው ኢትዮጵያዊ ማነው?

ይኸነው አንተሁነኝ

ሌቱ መሽቶ ይነጋል፤ ሳምንታት ወራት ዓመታት በፍጥነት መንጎዳቸውን አላቋረጡም፤ ክረምትና በጋ ይፈራረቃሉ፤ ወቅቶችም ማንም ሳይረብሻቸው ጊዜያቸውን ጠብቀው እያለፉ ነው፤ አፍጣጭ ገላማጭ ያለባቸውም ማዘዣ ጣቢያቸው ከእኛ አይደለምና።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በሆሳዕና "ማክበር" - በቀራንዮ "መስቀል"

ኤፍሬም እሸቴ

ታላቁ የክርስቲያኖች ጾም፣ ዐቢይ ጾም እነሆ የመጨረሻው "ሰሙነ ሕማማት"/ስቅለት ላይ ደረሰ። ለእምነቱ ተከታዮች የአጽዋማት ሁሉ በኩር እና ዋነኛ (ዐቢይ) እንደመሆኑ ከምንም በዓል በላይ በታላቅ መንፈሳዊ ስሜት የሚከበር ነው። የእምነቱ ተከታይ ላልሆነውም ወገን ቢሆን የሚኖረው ባህላዊ አንድምታ ከፍ ያለ መሆኑ ብቻ ሳይሆን ታሪኩን በደረቅ ንባብ ለሚመለከተውም ቢሆን ከዕለት-ተዕለት ሕይወቱ ጋር ሊያስነጻጽረው የሚችለው ብዙ ቁም ነገር እንደሚያገኝበት ጥርጥር የለኝም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ምርጫ የለም እንጂ ምርጫማ ቢኖር ...!

ፍቅር ለይኩን
የዛሬው ጽሑፌን በምርጫ ዙሪያ ካጋጠመኝ ትንሽ ቆየት ካለ ገጠመኜ ልጀምር። በደቡብ አፍሪካዊቷ ቢዝነስ ከተማ ጆሐንስበርግ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በትውልድ ደቡብ አፍሪካዊ የሆኑ ካህን፣ አባትና አገልጋይ የሆኑ በ60ዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙ አንድ አዛውንት አባት አሉ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የጎዳና ተዳዳሪው የወታደራዊ ደህንነትና መረጃ መኮንን ኮሎኔል ካሣሁን ትርፌ

የጎዳና ተዳዳሪው የወታደራዊ ደህንነትና መረጃ መኮንን ኮሎኔል ካሣሁን ትርፌ

ፍቅር ለይኩን

እንደ አለመታደል ሆኖ ከቅርብ የታሪካችን ዘመን እንኳን ብንነሳ ተጠሪነቱ ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ብቻ የሆነ፣ ብሔራዊ ስሜት ያለው፣ ጠንካራ የሆነ ሕዝባዊ መሠረት ያለው የመከላከያ ኃይል ለመፍጠር እየተደረገ የነበረውና አሁንም እያየነው ያለው ሙከራ መንግሥት በተለዋወጠ ቁጥር ሂደቱ እየተገታ ከዚህ ደርሰናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አባይ ለሕዝብ ወይስ አባይ ለኢሕአዴግ?

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም Dr. Tewodros Adhanom

ግርማ ካሳ

ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ጨምሮ በርካታ የኢሕአዴግ ባለስልጣናት፣ በተለያዩ የአሜሪካና የአውሮፓ ከተሞች በመዘዋወር፣ ለአባይ ግንባታ ገንዘብ ለማሰባሰብ ሞክረዋል። ነገር ግን በበርካታ ከተሞች፣ ከዚህ በፊት ከነበረው በተለየ ሁኔታ፣ ጠንካራ ተቃውሞ የደረሰባቸው ሲሆን፣ አንዳንድ ከተሞችም፣ ተቃዋሚዎች ስብሰባውን ሙሉ ለሙሉ እስከመቆጣጠር የደረሱበት ሁኔታም እንደነበረም ታዝበናል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

"መሪ አጣን" እያሉ ማላዘን ይቁም!

መሪነት እና የመሪነት ወለፈንዲዎች

ታደሰ ብሩ

መግቢያ

ማኅበራዊ ለውጥንና እድገትን የሚመለከቱ ዓላማዎች በአንድ ወይም በጥቂት ሰዎች ጥረት የሚሳኩ አይደሉም። እነዚህ ትላልቅ ዓላማዎች እንዲሳኩ የብዙ ሰዎች የተባበረ ጥረት ያስፈልጋል። በርካታ ሰዎችን ለእንዲህ ዓይነቶቹ ግዙፍ ዓላማዎች ማነሳሳትና እና ማስተባበር ነው መሪነት (Leadership) የሚባለው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ከፋውንዴሽኑ ጀርባ ...

ተመስገን ደሳለኝ

(ክፍል ፩)

ያለ ወቅቱ በደረሰ ዝናብ እየራሰች ያለችው አዲስ አበባ ዛሬም ከመለስ መንፈስ ተፅእኖ ነፃ አልወጣችም፤ ጣራና ግድግዳዎቿ እንዲህ በምስሉ እና በድርጅቱ አርማ መዥጎርጎሯን ያስተዋለ አንድ ቀልደኛ የባህር ማዶ ወዳጄ "እኔ ከሀገሬ ከወጣሁ በኋላ የኢህአዴግ ዋና ከተማ ሆነች እንዴ?" ብሎ ፈገግ አሰኝቶኛል። በእርግጥ ይህችን ቀልድ ስንፍቃት የምናገኘው ቁም ነገር፦ ከተማዋ በመለስ ውርስ ድንዛዜ ላይ መሆኗ፣ ...

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዘረፋ ውሎ በእንዳማርያም

ገብረመድህን አርአያ

ስብሃት ነጋ ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ በሚታተመው የአዲስ አድማስ ጋዜጣ ላይ የሰጠውን ቃለ መጠይቅ አነበብኩት። ስብሃት ነጋ “ኢህዴግን የመሰለ ፓርቲ በአፍሪካ የለም” እና ሌላም ብዙ፣ ብዙ ይላል:: ይዘብታል፣ ይፎክራል፣ ይሸመጥጣል፣ ያቀረሻል፣ በህዝብ ሞራል ላይም ያላግጣል። ብዙም አልደነቀኝም። ስብሃትም ሆኑ የዚህ ፋሺስታዊ ስርዓት አንቀሳቃሾች በብዙሃን ደም ላለፉት አርባ አመታት ታጥበዋል፣ ታሪክ አውድመዋል፣ እጅግ ከፍተኛ ዘረፋ ፈጽመዋል፣ አገር ቆርሰው ሸጠዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ