ቤል ተዋረደ፣ ናባው ተሰባበረ

ዳዊት ፋንታ

በአንድ ወቅት ገጣሚና ደራሲ በዕውቀቱ ስዩም "ይህ አዲስ አበባ አይደለም፣ ይህ የገጠር ቀበሌ ነው" የተሰኘ መጣጥፍ ፅፎ ነበር። እናም በዚያች "ሥርዓት አልበኝነት" በነገሰባት የገጠር ቀበሌ ውስጥ የሂሳብ መምህሩ ከመቅፅበት ተነስተው የስዕል መምህር ሲሆኑ ይታያል። በርግጥም የሕግ የበላይነት ባልሰፈነባት በዚያች የገጠር መንደር የሂሳብ መምህሩ የስዕል መምህር መሆን ሳያንሳቸው ተማሪዎቻቸውን ሲያሰቃዩ ይስተዋላል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

አበበ ጉዑሽን በላ

ያሬድ አይቼህ

“በአለም ማየት የምትፈልገውን ለውጥ ሆነህ ተገኝ።” ማህተማ ጋንዲ

ኢሳት ጃንዋሪ 8፡2013 ላይ እንዲህ የሚል አጭር የቪዲዮ ሰበር ዜና ለጥፎ ነበር፡ “የ FBI መርማሪዎች አበበ ገላውን ለመግደል የታቀደ ሴራ አከሸፉ(።) በሴራው የተሳተፉ የህወሃት ሰላዮች ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።” ‘ሴረኛ’ ከተባሉት ሰዎች አንዱ አቶ ጉዑሽ አበራ ነው።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢኮኖሚ ቴክኖሎጂና የወጣቶች ባህርይ

ከበደ ኃይሌ

ለዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ኢትዮጵያውያን ወላጆች በአሁኑ ጊዜ ኢኮኖሚና ቴክኖሎጂ ባሳደረባቸው ተጸዕኖ ልጆቻቸውን እንደባህላቸው ተቆጣጥሮ ለማሳደግና በኢትዮጵያዊነት ሊያስጠራ የሚያስችል ባህላቸውን ለማውረስ ባለመቻላቸው ልጆቻቸውን እንደባዕድ ሲያዩ እየታዘብን እናልፋለን እንጂ የወላጅነት ሃላፊነታቸውን ሊወጡ ያልቻሉበት ምክንያት ምን እንደሆነ የሚረዱላቸው በ21ኛው ክፍለ-ዘመን ወጣት ልጆች የሚያሳድጉ ብቻ ናቸው ለማለት ያስደፍራል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአሉላ አባ ነጋ ጠላቶች

(አንተነህ መርዕድ)

አሉላ አባ ነጋ ትግራይ ውስጥ በተንቤን አውራጃ መናዌ በምትባል መንደር እንግዳ ቁቤ ከተባሉ ገበሬ ነው የተወለዱት።በወጣትነታቸው በሚያሳዩት  ግንነትየአጼ ዮሃንስን የዚያንጊዜውን ካሳ ምርጫን ትኩረት ስበው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የአበበ ገላው ጉዳይ

ክንፉ አሰፋ

የአቶ መለስ ዜናዊ ዜና እረፍት በተሰማ ማግስት አንድ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵአዊ ከአውሮፓ ለአበበ ገላው ስልክ ይደውልለታል።  ግለሰቡ ደጋግሞ ሲደውል የአበበ የእጅ ስልክ ጠፍቶ ስለነበር ሶስት ተከታታይ የድምጽ መልእክቶችን ትቶ ነበር። “አበበ እባክህን ባስቸኳይ መልሰህ ደውልልኝ።  አንተን በተመለከት ከአገርቤት የመጣ መረጃ አለ።እባክህን መልሰህ በዚህ ቁጥር አስቸኳይ ደውልልኝ።” ይላል መልእክቱ።  ደዋዩ ከልብ እንደተጨነቀ ከድምጹ መረዳት ይቻላል። 

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ሻለቃ ፀአዱና ሟቹ ዶ/ር ልኡል

(ከእየሩሳሌም አርአያ)

ሻለቃ ፀአዱ የህወሓት ታጋይ የነበረች ናት። ከኤርትራና ጣሊያን የዘር ግንድ ያላት ሻለቃ ፀአዱ የቀይ ቆንጆ ናት፤ ገፅታዋን በመመልከት ማንነትዋን በቀላሉ መገመት ይቻላል። የሽማግሌው ስብሃት ነጋ ባለቤት ነበረች። ሽማግሌው ስብሃት ከበረሃ ጀምሮ በአብዛኛው የድርጅቱ አባላት የሚታወቁበት ባህርይ ሴሰኝነታቸው ነው። ከፀአዱ ጋር ከበረሃ የጀመሩት ፆታዊ ግንኙነት እስከ 1990ዓ.ም ድረስ የዘለቀ ሲሆን በ ጊዜያቸው ልጆች አፍርተዋል። በኮንኮርድ ሆቴል ጀርባ ገባ ብሎ በሚገኘው የተንጣለለ ቪላ የሚኖሩት ሽማግሌው ስብሃትና ሻለቃ ፀአዱ ነጋ-ጠባ ሲያነታርካቸው የነበረው አስገራሚ « አጀንዳ» ፈንድቶ የወጣው ከላይ በተጠቀሰው አመት ነበር። በፓርቲው ሕግ፥ “አንድ የማ/ኰሚቴ አባል በትዳሩ ላይ ችግር ሲከሰት ጉዳዩ የሚታየው በድርጅቱ አመራር ነው”፤ ከዚህ ባለፈ ወደ ፍ/ቤት መሔድ አይቻልም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በአረብ ሀገር ክፍል 9

በግሩም ተ/ሀይማኖት

አሰቃቂ ነገር በመስማት በዓልን በእንባ….

በየመን ኢትዮጵያዊያን ላይ የሚደረገው ድብደባ በገመድ እስከማነቅ ከፍቷል

የሰው ልጅ ላይ ሊፍጸም የማይገባው ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የመን ውስጥ ባሉ የተደራጁ አፋኞች ዜጎቻችን ላይ እየተፈጸመ ነው፡፡ ሰኞ ታህሳስ 29 ቀን በዓልን በገመድ ታንቀው ሲደበደቡ ከነበሩ እና ከሞት ተርፈው ሰነዓ ከገቡ ልጆች ጋር አሳለፍኩ፡፡ ሰውነታቸው ላይ በድብደባ ያረፈውን ቁስል እያየን አንገታቸው ላይ ገመዱ የከረከራቸው ምልክት ሰቅጥጦን ከሞት እንዴት እንደተረፉ እያወጉን በእንባ ታጅበን አሳለፍን፡፡ ሙሉውን አስነብበኝ ...

“ዘጠኝ ቁጥር”

ክንፉ አሰፋ

በኪም ጆንግ ዘመነ-መንግስት በችጋር እና በእርዛት ይጎሳቆል የነበረ አንድ የሰሜን ኮረያ ወጣት ብቻውን በአደባባይ ወጥቶ የኪም ጆንግ ኢልን መንግስት ይረግማል። “የምንበላው የለም! የምንለብሰው የለም!… ታርዘናል፤ ደህይተናል! ኪም ጆንግ ከስልጣን ይውረድ!”… ወጣቱ ብቻውን ሲጮህና ሲቃወም የተመለከቱ የኮምኒስቱ ፓርቲ የደህንነት አባላት ወጣቱን አፍነው ወስደው፣ ጨለማ ክፍል ውሰጥ ይወረውሩታል። ለሁለት ቀን ያህል በርሃብ ከቀጡት በህዋላም የጥይት ውርጅብኝ በጆሮው ላይ በማጮህ አስፈራርተው ይለቁታል። በእስር ቤቱ ይተኮስ የነበረው እውነተኛው ሳይሆን የልምምድ ጥይት ነበርና በእስረኛው ላይ የስነ-ልቦና እነጂ የአካል ጉዳት አላደረሰበትም። ሙሉውን አስነብበኝ ...

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ