የስየ “ምስጢሮች”
ተስፋዬ ገብረአብ
ስየ አብርሃ የፃፈውን መጽሐፍ አነበብኩት።
የተደጋገመውን ዝባዝንኬ እየዘለልኩ እንደምንም ጨረስኩት። የስየ ወንድሞች የገዟቸው መኪኖች የሻንሲ ቁጥር ምንም ስለማያደርግልኝ እየነጠርኩ አልፌዋለሁ።
ስየ ላይ አልፈረድኩበትም። ሙሉውን አስነብበኝ ...የአንባብያን ድምፅ: 3 / 5
ተስፋዬ ገብረአብ
ስየ አብርሃ የፃፈውን መጽሐፍ አነበብኩት።
የተደጋገመውን ዝባዝንኬ እየዘለልኩ እንደምንም ጨረስኩት። የስየ ወንድሞች የገዟቸው መኪኖች የሻንሲ ቁጥር ምንም ስለማያደርግልኝ እየነጠርኩ አልፌዋለሁ።
ስየ ላይ አልፈረድኩበትም። ሙሉውን አስነብበኝ ...ያገር ልጅ
ስለተስፋዬ ገብረአብ ሸጋ የአማርኛ ቋንቋ ብዕርተኝነት እንዳዲስ እዚህ ላይ አላነሳም። በጣም ብዙ ብዙ ተቺዎችና አስተያየት አንጓቾች በቁጥራቸው መጠን ብለውታል። ደራሲው ተስፋዬና የፕሮፓጋንዳ መጣጥፍ ጣፊው ተስፋዬም የብዕር ውበት ለዛቸው አንድ ነው። ልዩነታቸው ከዘላቂው የፈጠራ ሥነ-ጽሑፍ ሰብዕናና ካላፊው ከረጋፊው የፕሮፓጋንዳ ሰውነት ላይ ብቻ ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...
የአንባብያን ድምፅ: 1 / 5
ገሠሠ እንግዳ
በኢትዮጵያ በህይወቴ ዘመን ሦስቱን ሥርዓቶች ማለት የዓፄ ኃይለሥላሴ፣ የኰለኔል መንግሥቱ ኃይለማሪያም እና የመለስ ዜናዊ መንግሥታት መልካቸው ብቻ ሳይሆን ተግባራቸውንም ጭምር ለማስተዋል ከበቁት ሰዎች ውስጥ አንዱ ነኝ። በተለይም በሀገራችን ለውጥ ለማምጣት “ዳቦ ለተራበ”፣ ”መሬት ላራሹ” የሚል ህያው መፈክር ይዞው “አትነሳም ወይ የግፍ አገዛዝ አይበቃህም ወይ?!” እያሉ በአደባባይ ወጥተው ይጮኹ ከነበሩት ተማሪዎች አንዱ ሁኘ ብዙ ውጣ ውረድ አልፈው እዚህ ከደረሱት ትውልድ አንዱ ነኝ። የወጣቱ አስራት አብርሃምን መጽሐፍ ሳነብ የቀሰቀሰብኝ ትዝታም ያ ያሳለፍኩት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች እንቅስቃሴ የእሳትነት ዘመኔ ነበር። ሙሉውን አስነብበኝ ...
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
እንደ ግምገማ - ኩችዬ This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it.
“መጽሐፍ!” ሲሉት ሰፍ የሚል ከራማ ቢጤ አለብኝ መሰል ስየ አብርሃ ደረሱ የተባለው መድብል እጄ እስኪገባ ቸኩዬ ነበር። ባገራችን የቅርብ ዘመን ታሪክ ላይ አሻራቸውን ካተሙት ጥቂት ስዎች መሀል ናቸውና እኒህ ሰው የሚሉትን ለማወቅ ብተጋ አይፈረድኝም። ጀመርሁ የሚሉት የሁለተኛው ምዕራፍ ጉዟቸው የምንፈልገው ዓይነት መሆኑን የሚያመላክቱ ፍንጮች ያዘለ ሊሆን ስለሚችልም መጽሐፉን ለማንበብ በቂ ምክንያት ያለ መሰለኝ። ላወቀበት በመስመሮቹ መሀል የተሰነጉትን ሁሉ መመርመር ነው። ሙሉውን አስነብበኝ ...
የአንባብያን ድምፅ: 5 / 5
እጅጋየሁ አወቀ
”... ደራሲ ተስፋዬ ራሴን ነፃ አውጥቻለሁ የሚሉትን የቀድሞ የፖለቲካ ድርጅታቸውን በመደገፍ ተቃዋሚውን፤ በተለይም በአሰብ ጉዳይ ላይ ከመለስ የተለየ አቋም የወሰዱትን ቢታገሉ፤ እየሠሩ ያሉት ”ሀገሬ” ለሚሏት ለኢትዮጵያ ወይስ ለእናታ ሀገራቸው ለኤርትራ? ልብ በሉ፣ በአሰብ ላይና የአልጀርሱን ስምምነትና የሔጉን ውሳኔ ውድቅ እናደርጋለን በሚሉት የአንድነት/መድረክ አመራር አባላት ላይ ሰፊ ዘመቻ እያካሄዱ ሲሆን፣ የአሰብን ጉዳይ አታንሱብኝ እያለ የአልጀርሱን ስምምነት ፈርሞ ያፀደቀውንና የሔጉንም ፍ/ቤት ውሳኔ ለተቀበለው ለጠ/ሚ መለስ ቡድን የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ በመስጠት ላይ ናቸው። ታዲያ አቶ ተስፋዬ ማን ናቸው? የኢትዮጵያ ወይስ የኤርትራ ጥቅም አስከባሪ ፕሮፓጋንዲስት? ...” ሙሉውን አስነብበኝ ...