ሸንቁጥ አየለ

ኅቡእ ጣት (ዘ ሀይድ)
ኅቡእ ጣት (ዘ ሀይድ)፣ የሸንቁጥ አየለ አዲስ መጽሐፍ

ኅቡእ ጣት (ዘ ሀይድ) የተሰኘውን አዲሱ መጽሐፌ፤ በኢትዮጵጵያውያን፣ ኤርትራውያን እና ግብጻውያን፤ ብሎም በተጓዳኝ ያሉ አገራትን ፖለቲካዊ ስነልቦናዊ ጭብጥ፣ የፖለቲካ ኢኮኖሚያዊ ስሌት፣ አገራዊ ራዕይ፤ እንዲሁም አጠቃላይ የፖለቲካ ቀመራዊ ውል ሊፈትሽ ይባትታል።

በኃይል፣ በፍቅር፣ በጥላቻ፣ በጥርጣሬ፣ በጋብቻ፣ በእውነት፣ በወገናዊነት፣ በሸፍጥ፣ በሰብዓዊ የስሜት ጡዘቶች፤ እንዲሁም በሳይንሳዊ የአዕምሮ መቃተቶች ውስጥ የፖለቲካ ቀመራዊ ትርምስምሶች ተያይዘው ይጋመዱበታል።

ምናልባት እርስዎ ሲያነቡት ባለ 206 ገጹን ኅቡእ ጣት መጽሐፍ፤ ወደ ሁለት ሺህ ገጽ አሳድገው ሊተነትኑት ወይም አዲስ መጽሐፍ ቀምረው ሊጽፉበት ሊነሱ ያስቡ ይሆናል።

መጽሐፉን ኦንላይን /online/ ያገኙታል። ባይወዱት ይናደዱበታል። ካልተናደዱበት ግን ይወዱታል። ቢወዱትም ወይም ቢናደዱበትም ግን አንዳ የሃሳብ ብልጭታ በውስጥዎ ማጫሩ አይቀርምና እንዲያነቡት ጋብዤዎታለሁ።

ሸንቁጥ አየለ:- የኅቡእ ጣት (ዘ ሀይድ) መጽሐፍ ደራሲ።

http://www.shenkut.com/GetMyBooks.aspx

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ