ባልደራስ

ለ”ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ” የተሠጠው ለሦስት ወራት የሚያገለግለው ጊዜያዊ እውቅናና የምዝገባ ሰርቲፊኬት

ሦስት ፓርቲዎችም በተመሳሳይ ተመዝግበዋል

ኢዛ (ረቡዕ ጥር ፲፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. January 22, 2020)፦ በጋዜጠኛና አክቲቪስት እስክንድር ነጋ የሚመራው “ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ” ፓርቲና ሦስት ሌሎች ፓርቲዎች ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ (ሰርቲፊኬት) እና ጊዜያዊ እውቅና እንደተሠጣቸው ተገለጸ።

ከቦርዱ የተገኘው መረጃ ከባልደራስ ሌላ ጊዜያዊ እውቅናና ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ የተሠጣቸው ሦስቱ ፓርቲዎች “አንድ ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ”፣ “የአማራ ግዮናዊ ንቅናቄ” እና “እናት ፓርቲ” ናቸው። እንዲህ ዐይነቱ ፈቃድ የሚቆየው ለሦስት ወራት ብቻ ነው።

ባልደራስ ለእውነተኛ ፓርቲ የተሠጠው ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ በክልላዊ የፖለቲካ ፓርቲነት ሲሆን፤ የተቀሩት ሦስቱ ደግሞ የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲነት መኾኑ ታውቋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!