Ethiopia Zare (ሐሙስ መስከረም 11 ቀን 2004 ዓ.ም. September 22, 2011)፦ ባለፈው መስከረም 3 ቀን 2004 ዓ.ም. የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር አንዷለም አራጌንና ሌሎች ሦስት የፓርቲውን የምክር ቤት አባላትና እውቁን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላቸው በማለት ኢህአዴግ ያሠራቸው ግለሰቦች ”ከእኔ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም” በማለት ግንቦት ሰባት መግለጫ አወጣ።

 

”የማይቀረውን ውድቀት ለማስቀረት ከንቱ መፍጨርጨር” በሚል ርዕስ ግንቦት ሰባት ንቅናቄ መስከረም 9 ቀን ባወጣው መግለጫ ”... ከግንቦት 7 ጋር አሲረዋል በሚል የሃሰት ክስ መስርቶ የወያኔ ዘረኛ ገዥ ጉጅሌ ወደ ወህኒ እንዲረውራቸው ያስደረገው በጁ መረጃ ኖሮት ሳይሆን በፍርሃትና በከበባ የተወጠረው ጭንቀቱ ነው። ...” ብሏል። መግለጫው በመቀጠልም፣ ”... ዘረኛነት ሰው ለመክሰስና ለማሰር መረጃ አያስፈልገውም። ዘረኛነት እውነትን ለመደፍጠጥ ሃሰትን ለማንገስ ይሉኝታ አያስፈራውም። ዘረኛነት ከአመክኖ ጋር አይገናኝም። በዘረኛነት ለተለከፈ የወያኔ ገዥ ጉጅሌ አእምሮ ስልጡን ክርክርና ውይይት የሚባል ነገር ባእድ ነው። ...” ብሏል።

 

”... ሰሞኑን ወያኔ የተያያዘውን ሰላማዊ ሰዎችን በሽብር ስም የማሸበር፣ ሰላማዊና ህጋዊ የፖለቲካ ተቃዋሚዎችንና ጋዜጠኞችን በሽብር ስም እያፈሰ በየእስር ቤቱ የማጎር ድፍረቱና ጨካኝነቱ የመነጨው ከዘረኛነቱ ነው። በእጃቸው ስንጥር ያልያዙ ሰዎችን አሸባሪዎች በማለት በወታደር ከቦ በህጻናት ልጆቻቸው፣ በወላጆጃቸውና በሚያከብራቸው ወገናቸው ፊት በካቴና አስሮ እየጎተቱ መውሰድ የሚቻለው፣ ታሳሪዎቹንና ልጆቻቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን ሊዋረዱና ሊሰቃዩ የሚገባቸው አይጦች ናቸው ብሎ በማሰብ የሚሰራ እኩይ ስራ ነው። ወያኔ ያለምንም ይሉኝታ አይንኑ በጨው ታጥቦ፣ ፍርድ ቤቶችን የሃሰት ክስ መመስረቻ፣ መገናኛ ብዙሃኑን የሃሰት ወንጀል ማሰራጫ ማድረግ የሚቻለው ጭፍን ዘረኛነት የደፈነው ህሊና ባላቸው እብሪተኛ ገዥዎች የተሞላ ስለሆነ ነው። ...” ሲል ግንቦት 7 በመግለጫው አትቷል። ... ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ