Dr. Debretsion Gebremichael

የሕወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል

“ዘመቻውን አስቁሙልን፤ ካልኾነ ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር መኾንዋን ወስኑ” ዶ/ር ደብረጽዮን

ኢዛ (ረቡዕ የካቲት ፲፩ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 19, 2020)፦ የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሕወሓት 45ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል ዛሬ የካቲት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. በመቀሌ ስታዲየም ተከብሯል። ዶ/ር ደብረጽዮን፤ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን በእነርሱ ላይ ይካሔዳል ያሉትን ዘመቻ አስቁሙልን ወይም ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር እንድትኾን ወስኑ አሉ።

ከበዓሉ ዋዜማ ጀምሮ በክልሉ ከተሞች በተለያዩ ዝግጅቶች ሲከበር የነበረ ሲሆን፣ ዛሬ የማጠቃለያ በዓሉ መከበሩ ታውቋል።

ሕወሓት በዓሉን በማስከበር ሰሞኑን አውጥቶ በነበረ መግለጫ፤ በአሁኑ ወቅት አገር እያስተዳደረ ያለውን መንግሥት አብዝቶ የኮነኑትና “ኢትዮጵያ አደጋ ላይ ነች” የሚል መልእክት ማስተላለፉን መዘገባችን አይዘነጋም።

ዛሬ በመቀሌው በዓል ላይ ንግግር ያደረጉት የሕወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፤ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ንግግር አድርገዋል።

ከዛሬው የዶክተሩ ደብረጽዮን ንግግር፤ የብዙዎች ትኩረት የሠጡት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የኃላፊነት ጊዜያቸው መጠናቀቁን ጠቅሰው፤ በትግራይ ላይ በመሪዎች ደረጃ የጥላቻና የፀረ ሕዝብ ንግግሮችን በይፋ እንዲኮንኑ መጠየቃቸው ነው።

አያይዘውም “ይህ ካልኾነ ትግራይ ራስዋን የቻለች አገር መኾንዋን ወስኑ” ስለማለታቸውም ቢቢሲ የአማርኛው ክፍል ዘግቧል።

ዶክተር ደብረጽዮን በኢትዮ-ኤርትራ ጉዳይም በንግግራቸው ያካተቱ ሲሆን፣ በኤርትራና በትግራይ ሕዝብ መካከል ያለውን ግንኙነት በማስታወስ ሰፊ ንግግር አድርገዋል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ