Adanech Abebe and Eng. Takele Uma

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ፣ ኢንጂንየር ታከለ ኡማ (ከግራ ወደቀኝ)

አዲስ አበባ ከተማ አዲስ አበቤ ከንቲባ አሁንም አላገኘችም

ኢዛ (ማክሰኞ ነኀሴ ፲፪ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 18, 2020)፦ ከአዲስ አበባ ከተማ ምክልት ከንቲባነታቸው ተነስተው የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኾነው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተሾሙት ኢንጂንየር ታከለ ኡማ ምትክ የከተማዋ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የከተማ ምክትል ከንቲባ ኾነው ተሾሙ።

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የፌዴራሉ መንግሥት ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ኾነው ሲያገለግሉ ከነበሩበት ሥልጣን ዛሬ ማክሰኞ ነኀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ተነስተው በምትካቸው ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ተሹመዋል።

 

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በጠራው አስቸኳይ ስብሰባ፤ በዛሬ ዕለት ሹመታቸውን ያጸደቀላቸው ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከዚህ ቀደም የገቢዎች ሚኒስትር የነበሩ ከመኾናቸውም በላይ የናዝሬት (አዳማ) ከተማ ከንቲባ በመኾን ማገልገላቸው ይታወሳል።

የከተማዋ ምክር ቤት በወ/ሮ አዳነች አቤቤ አማካኝነት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ተቋማት አስተባባሪ ኾነው እንዲሾሙ የቀረቡትን አቶ ዣንጥራር ዓባይን ሹመት አጽድቋል። አቶ ዣንጥራር የተተኩት ወደ ሜቴክ (የብረታ ብረት ኢንጂንየሪንግ ኮርፖሬሽን) ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኾነው በዛሬው ዕለት በተሾሙት በኢንጂንየር እንዳወቅ ምትክ ነው።

ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ከ1983 ዓ.ም. ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩትና የተሾሙ ባለሥልጣናት አንዳቸውም የከተማዋ ነዋሪ ወይንም የትውልድ ሥፍራቸው አዲስ አበባ እንዳልኾነ ይነገራል። ወ/ሮ አዳነች አቤቤም የትውልድ ሥፍራቸው አርሲ መኾኑ ይታወቃል። በመኾኑም አዲስ አበባ በአዲስ አበቤ ሳትመራ እስካሁን ቆይታለች። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ