የቦምብ ጥቃት በሻሸመኔ

የቦምብ ጥቃት በሻሸመኔ

አንድ የጸጥታ ኃይል ጉዳት ደርሶበት የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ነው

ኢዛ (ሐሙስ ነኀሴ ፲፬ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. August 20, 2020)፦ ዛሬ ሐሙስ ነኀሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ጠዋት በሻሸመኔ ከተማ ቅኝት በሚያደርጉ የጸጥታ ኃይሎች ላይ ቦምብ ወረወረ በተባለ አንድ የኦነግ ሸኔ አባል ላይ እርምጃ መወሰዱን ፖሊስ አስታወቀ።

በሻሸመኔ ቀበሌ 01 አካባቢ በጸጥታ ኃይሎች ላይ ቦምብ ወርውሮ ሊሰወር ነበር የተባለው የኦነግ ሸኔ አባሉ ከድር ቱሌ የሚባል መኾኑ ተጠቅሷል።

ግለሰቡ በወረወረው ቦምብ አንድ የጸጥታ ኃይል ጉዳት ደርሶበት የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ነው። ቦምብ የወረወረው ግለሰብ እርምጃ ከተወሰደበት በኋላ በእጁ ሁለት ሞባይሎች፣ ገንዘብ እና ትጥቅ መያዣ ቀበቶ ይዞ እንደነበር ፖሊስ ገልጿል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ