Ethiopia Zare (ኀሙስ መጋቢት 18 ቀን 2000 ዓ.ም. March 27,2008) የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የመስራቾች ፊርማ ለማሰባሰብ በሀገሪቱ በሚገኙ የተለያዩ ክልሎች ሊዘዋወሩ መሆኑን ለፓርቲው ቅርብ የሆኑ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ዛሬ ገለጡ። 

 

ትናንት የመስራቾች ፊርማ ማሰባሰብ የጀመረው የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለማርያምን ወደ ጉራጌ ዞን፣ አቶ ሙሉነህ ኢዩኤልን ደግሞ ወደ ደቡብ ክልል ነገ ወይንም ተነገወዲያ እንደሚልክ ታውቋል። 

 

ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርዋ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሣ ደግሞ በሚቀጥለው ሣምንት ወደ ክልል አንድ (ትግራይ ክልል) እንደሚጓዙ እነዚሁ ምንጮቻችን ገልጠዋል። 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ