አዲስ የተመረጡ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት ዝርዝር

Ethiopia Zare (ሰኞ ጥር 26 ቀን 2000 ዓ.ም. February, 4,2008)፦ ስድሳ አባላትን ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረው የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ፓርቲ አመራሮቹ ከተፈቱ በኋላ ይፋ በሆነው አለመግባባት የላዕላይ ምክር ቤቱ አባላት በስድስት የተለያዩ አሰላለፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ በአብዛኛው በተቀዳሚ ም/ሊቀመንበሯ የሚመራውን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አሰላለፍ የሚደግፉ መሆኑ ተገለጸ።

 

ከእነ ብርቱካን ሚደቅሳ ጋር ያሉ የላእላይ ምክር ቤት አባላት(23)

1. ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው                -          መኢአድ የነበሩ

2. አቶ አክሉ ግርግሬ                       -                  ››

3. አቶ አስቻለው ከተማ                    -                 ››

4. አቶ ዘለቀ ዓለሙ                           -                 ››

5. ዶ/ር ኃይሉ አርአያ ኢዴአፓ      -   መድኀን የነበሩ

6. አቶ ክፍሌ ጥግነህ                         -                ››

7. ዶ/ር ሚኪያስ አባይነህ                 -                ››

8. አቶ ታምራት ታረቀኝ                 -                ››

9. አቶ አንዱዓለም አራጌ                 -                ››

10. ወ/ሮ ላቀች ደገፋ                        -                ››

11. አቶ ሙሉጌታ ወንድምአገኘ      -                ››

12. ወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ               -    ቀስተደመና የነበሩ

13. ዶ/ር በፍቃዱ ደግፌ                    -               ››

14. ዶ/ር ሽመልስ ተ/ፃዲቅ                -               ››

15. ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማሪያም              -               ››

16. አቶ ዲባባ አመንሲሳ                  -               ››

17. አቶ የኔነህ ሙላት                       -               ››

18. ዶ/ር አብዱ መንገሻ                    -               ››

19. አቶ ኢላላ ተዘራ                         -      ኢዴሊ የነበሩ

20. አቶ ስለሺ ጠና                            -               ››

21. አቶ ሙሉነህ ኢዩኤል                 -               ››

22. አቶ መሐመድ ዓሊ                      -      መኢአድ የነበሩ፤

 

ከእነ ብርቱካን ሚደቅሳ ጋር እንደሆኑ የሚታሰቡ ግን በውጭ ሀገር የሚገኙ(3)

1. ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ         -   ቀስተ ደመና የነበሩ

2. አቶ አየለ አንጎሎ       - ኢዴሊ የነበሩ

3. አቶ ደበበ እሸቱ          -  ቀስተደመና የነበሩ

4. አቶ መስፍን አማን    -  መኢአድ የነበሩ

 

ከእነ ብርቱካን ሚደቅሳ ጋር እንደሆኑ የሚታሰቡ ግን ስብሰባ መገኘት ያቋረጡ(1)

1. አቶ ብሩክ ከበደ መኢአድ የነበሩ

 

ከእነ ኢ/ር ኃይሉ ሻውል ጋር ያሉ የላዕላይ ምክር ቤት አባላት (9)

1. ኢ/ር ኃይሉ ሻውል                        -    መኢአድ የነበሩ

2. አቶ አባይነህ ብርሃኑ                    -                ››

3. ሻ/ቃ ጌታቸው መንግሥቴ             -                ››

4. ወ/ሮ መሶበወርቅ ቅጣው             -                ››

5. ዶ/ር ታዲዎስ ቦጋለ                    -                ››

6. አቶ አሰፋ ሀ/ወልድ                      -                ››

7. አቶ ወንደሰን ተሾመ                   -     ኢዴአፓ መድህን የነበሩ

8. አቶ ገ/ፃዲቅ ኃ/ሥላሴ                  -     መኢአድ የነበሩ

9. አቶ ማሙሸት አማረ               -   መኢአድ የነበሩ

 

ከእነ ኢ/ር ኃይሉ ሻውል ጋር እንደሆኑ የሚታሰቡ ግን በውጭ ሀገር የሚገኙ(1)

1. ወ/ሮ ንግስት ገ/ሕይወት   -  ቀስተደመና የነበሩ

 

አቋማቸውን በግልጽ ያላሳወቁ (9)

1. ዶ/ር ደምበል ባልቻ                 -   መኢአድ የነበሩ

2. አቶ መሐመድ ዓሊ                 -              ››

3. አቶ ገ/ክርስቶስ ኃ/ሥላሴ        -              ››

4. አቶ እንዳለ ገ/ሕይወት           -  ኢዴአፓ መድህን የነበሩ

5. አቶ ኪዳነ ማርያም                 -  ቀስተደመና የነበሩ

6. ዶ/ር አለማየሁ አረዳ              - ኢዴሊ የነበሩ

7. ወ/ሮ ለኔ ሲል አሰፋው

8. አቶ ሚዛኑ እንዳሻው

9. ዶ/ር ሳሙኤል ከበደ

 

ኢዴአፓ መድህን ተብለው የቀጠሉ (5)

1. አቶ ልደቱ አያሌው

2. አቶ ሙሼ ሰሙ

3. አቶ አብዱራህማን አሕመድ

4. አቶ መስፍን አያሌው

5. አቶ ጎሹ አውደው

 

በውጪ ሀገር ከስድስት ወር በላይ የኖሩ (7)

1. ዶ/ር አድማሱ ገበየው

2. ዶ/ር ሙሉዓለም ታረቀኝ

3. አቶ ቸኮል ጌታሁን

4. አቶ ዳንኤል አሰፋ

5. ሻ/ቃ አድማሱ መላኩ

6. ዶ/ር በዛብህ ደምሴ

7. ወ/ት ለይላ ሲርጋጋ

 

በዘለቄታው ከፓርቲው የፖለቲካ ሥራ ራሳቸውን ያገለሉ (4)

1. ወ/ሮ ይደነቁ ምትኩ

2. ወ/ሮ ኩሪ ደበሌ

3. አቶ ቴዎድሮስ ግስላ

4. ወ/ት ሰላማዊት መንክር

 

በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው ሥራ አስፈጻሚ ባለፈው አርብ ተሰብስቦ የወሰነው ኢዴአፓ መድህን ተብለው በቀጠሉ አምስት ሰዎች፣ በውጪ ሀገር ከስድስት ወር በላይ በኖሩ ሰባት ሰዎች እና በዘለቄታው ከፓርቲው የፖለቲካ ሥራ ራሳቸውን ባገለሉ አራት ሰዎች በአጠቃላይ በ16 ሰዎች ምትክ ነው።

 

ሥራ አስፈጻሚው ውይይት ሲጀምር ከእነ አቶ ተመስገን ቡድን ጋር በመሆን ሲሆን ለተተኩት የላዕላይ ምክር ቤት አባላት 12 ሰዎችን አቅርቧል። እነ ብርቱካን በበኩላቸው አራት ሰዎችን አቅርበው በአጠቃላይ 16 ሰዎች የላዕላይ ምክር ቤቱን ተቀላቅለዋል።

 

እነ ብርቱካን ቡድን ተመርጠው ፓርቲውን የተቀላቀሉት

1. ፕሮፌሠር መስፍን ወ/ማርያም

2. አቶ አስራት ጣሴ

3. ወ/ሮ ሸዋዬ ኪሮስ

4. አቶ ፈጠነ

 

ከእነ ተመስገን በኩል የተመረጡትን በሚመለከት ከስድስት ሰዎች ውጭ የተሟላ መረጃ አልተገኘም። ታማኝ የሆኑ ምንጮች እንደጠቆሙት ግን

1. አቶ ተመስገን ዘውዴ

2. አቶ ብሩ ቢርመጂ

3. አቶ እንዳልካቸው ሞላ

4. አቶ በቀለ ወ/ሚካኤል

5. አቶ ክብረት ኃይሉ

6. አቶ አለማየሁ ናቸው።

 

አጠቃላይ የሆነው ስም ዝርዝራቸው በዚህ ሣምንት ይፋ እንደሚሆን ታውቋል።

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!