Ethiopia Zare (ኀሙስ መጋቢት 25 ቀን 2000 ዓ.ም. April 3,2008) አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ፈቃድ ለማግኘትና ለማቋቋም በየክልሉ የመስራቾች ፊርማ ለማሰባሰብ ተሰማርተው የነበሩ የፓርቲው መስራቾች ወደ አዲስ አበባ እየተመለሱ መሆኑን ለፓርቲው ቅርበት ያላቸውና የኢትዮጵያ ዛሬ ድረ ገጽ ምንጮች ገለጡ።

በነገው ዕለት ደግሞ ወደ ደቡብ፣ አፋር እና አማራ ክልል የተጓዙት የልዑካን ቡድኖች ወደ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ታውቋል።

 

ፓርቲው ከምርጫ ቦርድ ፈቃድ ለማግኘት የሚያስችለው ከአራት ክልሎች የ1,500 ሰዎች የድጋፍ ፊርማ እንደሚያስፈልገው የፓርቲዎች ምዝገባ ሕግ ይደነግጋል።

 

እንደምንጮቻችን ገለፃ ከሆነ የድጋፍ ፊርማውን አሰባስቦ ከጨረሰ በኋላ ደግሞ የፓርቲውን አመራሮችን ዝርዝር፣ የጠቅላላ ጉባዔ ውሳኔ እና አንድ ፓርቲ ፈቃድ ሲጠይቅ ሊያሟላቸው የሚገቡ ሌሎች ተያያዥ ሰነዶችን አሟልቶ ሲያበቃ ወደ ምርጫ ቦርድ በመቅረብ የፈቃድ ጥያቄውን ያቀርባል።

 

አስፈላጊ የሆኑትን ሰነዶች ለማሟላት ፓርቲው ጥቂት ሣምንታት ሊፈጅበት እንደሚችልና በሚቀጥለው ወር (ሚያዝያ) ውስጥ እነዚህን ሰነዶች አሟልቶ እንደሚጨርስ እነዚሁ የኢትዮጵያ ዛሬ ታማኝ ምንጮት ገልጠዋል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ