የአውሮፓ ህብረት የምርጫ 2002 ዓ.ም. ዝርዝር ሪፖርት አቀረበ
Ethiopia Zare (ማክሰኞ ጥቅምት 30 ቀን 2003 ዓ.ም. November 9, 2010)፦ ከአምስት ወራቶች በፊት በኢትዮጵያ የተካሄደውንና በወያኔ/ኢህአዴግ 99.6% አሸናፊነት እንደተጠናቀቀ የተገለጸውን ‘ምርጫ’ 2003 በሚመለከት የአውሮፓ ህብረት ታዛቢ ቡድን ዝርዝር ሪፖርቱን አወጣ። ምርጫው ግልጽና ለሁሉም ተቃዋሚዎች የተመቻቸ የመጫዎቻ ሜዳ ማዘጋጀት ያለመቻል ጉድለት ነበረው ሲልም መግለጫው አብራርቷል።
በ35 ገጽ የተካተተው የህብረቱ ታዛቢዎች ቡድን ሪፖርት ለቡድኑ መሪ ቴርስ በርማንና ለታዛቢዎቹ አባላት ከገዥው መንግስት ኢህአዴግ ቪዛ በመከልከላቸው ምክንያት ባልተለመደ መልኩ ሪፖርቱን ከሀገሪቱ ውጭ በብራሰልስ ለመስጠት እንደተገደዱ የቡድኑ መሪ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።
ህብረቱ በመግለጫው የመንግስት መገናኛዎች የሚዛን መጓደል ታይቷል፤ በምርጫ ሂደቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሀን ስነ ምግባር ደንቡን በሚጻረር መልኩ የመንግስት ሚድያ የኢትዮጵያ ህዝብ በምርጫ ሂደት ሙሉና ሚዛናዊ መረጃ የማግኘት መብቱን ነፍገውታል። በማለትም በተለይ የመገኛኛ ብዙሀኑን አውታር የተቸ ሲሆን የግል ጋዜጦች በገዥው ፓርቲና በአንዳንድ ዋና ዋና ተቃዋሚ ፓርቲዎች የበለጠ ሚዛናዊ ሽፋን አቅርበዋል። ብሏል።
በተለይ ከኖርዌይ፣ ኔዘርላንድና ካናዳ የተውጣጡ ታዛቢዎችን የያዘው ቡድን በተለያዩ ከቅድመ ምርጫ እስከ ድህረ ምርጫ ታዩ ያላቸውን አዎንታዊና አሉታዊ ገጽታዎች የተነተነ ሲሆን መስተካከል ይገባቸዋል ያላቸውንም ነጥቦች አስቀምጧል። (የህብረቱ ታዛቢዎች ያወጡትን መግለጫ ይህንን በመጫን ያንብቡ!)



