Reported by Matias Ketema

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ግንቦት 5 ቀን 2000 ዓ.ም. May 13, 2008)፦ በአቶ ኦባንግ ሜቶ የአኝዋክ ጀስቲስ ካውንስል መሪ አነሳሽነት የፊታችን ኀሙስ ተነገወዲያ ሜይ 15 ቀን 2008 እ.ኤ.አ. (ግንቦት 7 ቀን 2000 ዓ.ም.) በመላው ዓለም የሚደረገው ሰልፍ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልምም እንደሚደረግ አስተባባሪው ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ዛሬ ገለጸ።

 

በስዊድን የሚደረገውን ሰልፍ በማስተባበር የሚመራው የቅንጅት (የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ) ድጋፍ ማኅበር ሲሆን፣ ዓላማው የዛሬ ሦስት ዓመት በተመሳሳይ ዕለት ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓ.ም. በኢትዮጵያ በተደረገው ምርጫ ”ድምፃችን አይነጠቅም!” በማለት ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲ እና ለአንድነት የተሰዉትን ሰማዕታት ለመዘከር፣ እንዲሁም ለለውጥ የተደረገውን የዲሞክራሲ ንቅናቄንም ለማስታወስ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

 

በዕለቱ በስቶክሆልም በሚደረገው ሰልፍ፤ የሰልፉ ታዳሚዎች በሰገልስ ቶርየት (ፕላታን) በ14፡00 ሰዓት ተገናኝቶ በ15፡00 ሰዓት ወደ ሚንት ቶርየት ያመራል። በቦታውም የስዊድን የልዩ ልዩ ፓርቲዎች አባላት እንደሚገኙ ከአስተባባሪው ኮሚቴ ለመረዳት ችለናል።

 

የድጋፍ ማኅበሩ ሰብሳቢ ስለሰልፉ ዓላማ፣ ስለዲሞክራሲያዊ ትግሉ እና ኢትዮጵያ ባሁን ጊዜ ስላለችበት ሁኔታ ንግግር እንደሚያደርጉ ለማወቅ ችለናል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ