Ethiopia Zare (እሁድ ግንቦት 17 ቀን 2000 ዓ.ም. May 25, 2008)፦ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ግንቦት 23 ቀን 2000 ዓ.ም. ሊያደርገው የነበረውን ጠቅላላ ጉባዔ ለሰኔ 7 ቀን 2000 ዓ.ም. ማዛወሩን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ የኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጹ።

 

እሁድ ግንቦት 10 ቀን የላዕላይ ምክር ቤቱ ባደረገው ስብሰባ ጠቅላላ ጉባዔው ግንቦት 23 ቀን 2000 ዓ.ም. እንዲጠራ መወሰኑን መዘገባችን አይዘነጋም። እንደ ኢትዮጵያ ዛሬ ምንጮች ገለጻ ከሆነ ጉባዔው ሊራዘም የቻለው ጠቅላላ ጉባዔው ሊካሄድበት ታቅዶ ከነበረው የሆቴል አዳራሽ ጋር በተያያዘ ችግር ምክንያት ነው።

 

እስካሁን ድረስ ከምርጫ ቦርድ ሕጋዊ ፈቃድ ለማግኘት ማመልከቻ ያላስገባውና በወ/ት ብርቱካን የሚመራው የቀድሞው የቅንጅት ፓርቲ፣ የአሁኑ የ”አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ” በሚያደርገው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ የድርጅቱን አመራሮች እንደሚመርጥ መዘገባችን አይዘነጋም።

 

ጠቅላላ ጉባዔው ተካሂዶ ካበቃ በኋላ ፓርቲው ሕጋዊ ፈቃድ ይሰጠው ዘንድ ለምርጫ ቦርድ ማመልከቻውን ያስገባል ተብሎ እንደሚጠበቅ መዘገባችን ይታወሳል።

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ