Ethiopia Zare (ቅዳሜ ግንቦት 23 ቀን 2000 ዓ.ም. May 31, 2008)፦ ትናንት ጠዋት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አራት ፖሊሶች ከቢሯቸው ተወስደው የታሰሩት ሁለት የ”አዲስ ነገር” ጋዜጣ አዘጋጆች ረፋዱ ከሰዓት ላይ በዋስ መለቀቃቸውን ከአዲስ አበባ የደረሰን ሪፖርት አስረዳ።

 

የጋዜጣው ዋና አዘጋጅ አቶ መስፍን ነጋሽ እና ምክትል ዋና አዘጋጁ አቶ ግርማ ተስፋው እያንዳንዳቸው የሁለት ሺህ ብር ዋስ ለፖሊስ እንዲያቀርቡ ተጠይቀው፤ ዋስትናውን በማሟላታቸው ትናንትና ከሰዓት በኋላ ወደ ዘጠኝ ሰዓት ተኩል አካባቢ መፈታታቸው ታውቋል። ዋስትናውን የተጠየቁት ክሱ ወደ ፍርድ ቤት ሲላክ፤ አዘጋጆቹ ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ለማረጋገጥ እንደሆነ ታውቋል።

 

ከሳሻቸው የቅንጅትን ሕጋዊ ሠርቲፊኬት ምርጫ ቦርድ የሰጣቸው አቶ አየለ ጫሚሶ እንደሆኑ በትናንትናው ዕለት መዘገባችን ይታወሳል። (የትናንቱን ሙሉ ዘገባ አስነብበኝ)

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ