6ኛውን በአውሮጳ የኢትዮጵያውን የስፖርት ውድድር ዛሬ ጠዋት ተጀመረ

Ethiopia Zare (ዓርብ ሐምሌ 25 ቀን 2000 ዓ.ም. August 01, 2008)፦ በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም የሚካሄደው በአውሮጳ የስድስተኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ ጠዋት አምስት ሰዓት (11 AM) የእግር ኳስ ጨዋታው በክብር እንግዶቹ በመንግሥቱ ወርቁ እና በሉቺያኖ ቫሳሎ ተመርቆ ተጀምሯል። (በፎቶግራፉ ላይ ንግግር የሚያደርገው መንግሥቱ ወርቁ ሲሆን፣ በስተግራው ደግሞ ያለው ሉቺያኖ ነው)
በእግር ኳሱ ይሳተፋሉ ተብለው የተጠበቁት ከአስራ አንድ የአውሮጳ ሀገሮች የመጡ ሃያ ቡድኖች ናቸው። ከስዊድን 3 ቡድኖች፣ ከእንግሊዝ 3 ቡድኖች፣ ከጀርመን 4 ቡድኖች፣ ከሆላንድ 2 ቡድኖች እና ከጣሊያን 2 ቡድኖች የሚመጡ ሲሆን፤ ስዊዘርላንድ፣ ቤልጅየም፣ ፈረንሣይ፣ ኖርዌይ እና ፊንላንድ አንድ አንድ የእግር ኳስ ቡድን ይዘው ቀርበዋል። የጀርመኑ አምስተኛ ቡድን ”ሙኒክ” ግን በውድድሩ ሳይሳተፍ ቀርቷል።
ሙሉውን የውድድሩን ውጤት በሥፍራው የሚገኙት የኢትዮጵያ ዛሬ ዘጋቢዎች አሟልተው በተቻለ ፍጥነት ለማቅረብ ይሞክራሉ።



