"ባለ 30 ገጽ ክስ ተዘጋጅቶብኛል" አውራምባ ታይምስ

Ethiopia Zare (ማክሰኞ ሐምሌ 29 ቀን 2000 ዓ.ም. August 05, 2008)፦ ዛሬ ገበያ ላይ የዋለው "አውራምባ ታይምስ" ጋዜጣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን በሚመለከት ምንም አይነት ዘገባ እንዳይዘግብ መከልከሉን በመግለጽ የዶ/ሩን ምስል በትልቁ የኤክስ ምልክት አድርጎ በማውጣት ጋዜጣውን ለአንባቢዎቹ ማቅረቡን ሪፖርተሮቻችን ከአዲስ አበባ ገለጹ።

 

አውራምባ ታይምስ ጋዜጣ በተጨማሪም በፍትህ ሚኒስቴር የተቀነባበረ ባለ ሰላሳ ገጽ ክስ ተዘጋጅቶ እየጠበቀው መሆኑንና ተጨባጭ መረጃዎችም እንደደረሱት ዛሬ ገበያ ላይ በዋለው ዕትሙ ያስነበበ መሆኑን ለማወቅ ችለናል።

 

አውራምባ ታይምስ ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ አስፈላጊ አይደለም ያላቸው ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ስልክ በመደወል እነ ዶ/ር ብርሃኑን በሚመለከት መዘገቡን እንዲያቆም መንገራቸውን ጨምሮ ዘግቧል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ