‘ክሱ አስቂኝ ነው’ ታዛቢዎች

Ethiopia Zare (ኀሙስ የካቲት 27 ቀን 2000 ዓ.ም. March 6, 2008)፦ ዛሬ በደረሰን ሰበር ዜና መሰረት ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የተከሰሰው የአዲሱን "አውራምባ ታይምስ" ጋዜጣ ማስታወቂያ በአንድ የኢህአዴግ ተመራጭ ማስታወቂያ ላይ ለጥፈሃል በሚል ሲሆን፣ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀርቦ ፍርድ ቤቱ በዋስ እንደለቀቀው ለማወቅ ችለናል። ከሳሹ ምርጫ ቦርድ እንደሆነ ታውቋል።

 

በየትኛውም የአሜሪካም ሆነ የአውሮፓ ሀገራት በመንገድ ላይ የሚለጠፍ ማስታወቂያ በተደራራቢ አዳዲስ ማስታወቂያዎች የሚለጠፉባቸው ከመሆኑም በላይ፣ የልጠፋ ሥራውን በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሠሩት በኮንትራት የሚሠሩ ወጣቶች ማስታወቂያውን በየቦታው እንዲለጥፉ በመነጋገር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤ አንድን ጋዜጠኛ በእንደዚህ አይነት ተራ ክስ ምክንያት ከሥራ ማስተጓጎል አሳዛኝ ከመሆኑም በላይ አጠቃላይ ክሱ አስቂኝ ነው ሲሉ ታዛቢዎች ተችተዋል።

 

አዲስ ቪዲዮ

ዜና እና ፖለቲካ

ኪነ-ጥበብ

ቪዲዮ

መጻሕፍት

ስለእኛ

ይከተሉን!