ቅምሻ ስለአንጋፋው ጋዜጠኛ ፀጋዬ እንደሻው
Ethiopia Zare (እሁድ መስከረም ፬ (4) ቀን ፳፻፩ (2001) ዓ.ም. September 14, 2008)፦ ባለፈው ዓመት ረቡዕ ጳጉሜን 5 ቀን 2000 ዓ.ም. አንጋፋው ጋዜጠኛ ፀጋዬ እንደሻው በ65 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። ጋዜጠኛ ፀጋዬ ለጀርመን ድምፅ ራዲዮ የሀገር ቤት ወኪል እንደነበር አይዘነጋም።
ጋዜጠኛ ፀጋዬን በቅርብ የሚያውቀውና ነዋሪነቱ በኖርዌይ የሆነው ጋዜጠኛ አበራ ለማ አብረው ያሳለፉን ጨምሮ ስለጋዜጠኛ ፀጋዬ የሚያውቀውን በመጠኑ ለኢትዮጵያውያንና ለአድናቂዎቹ ለማካፈል ሦስት ገጽ ጽሑፍ በኢትዮጵያ ዛሬ በኩል አበርክቷል። (ጽሑፉን በፒ.ዲ.ኤፍ. አስነብበኝ)