Amhara National Regional State Head of Government Office

የአማራ ክልል ምክር ቤት

ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል

ኢዛ (ሰኞ የካቲት ፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓ.ም. February 17, 2020)፦ የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ነገ የካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. አስቸኳይ ጉባዔውን እንደሚያካሒድ ተገልጿል። የተለያዩ ሹሙቶችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመምከር ውሳኔ ያሳልፍበታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ ሹመቶችን ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጉባዔውን አስመልክቶ የተሠራጨው መረጃ ያስረዳል።

ምክር ቤቱ በነገው ዕለት የሚያደርገው አስቸኳይ ጉባዔ አምስተኛ ዙር፣ አምስተኛ የሥራ ዘመን፣ አንደኛ አስቸኳይ ጉባዔው መኾኑ ታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የጨፌ ኦሮሚያ መደበኛ ጉባዔውን በተመሳሳይ በነገው ዕለት ያካሒዳል።

ከጉባዔው አጀንዳዎች መካከል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሥራ አስፈፃሚ አካላትን አፈፃፀም መገምገም አንዱ ተግባሩ እንደኾነ ታውቋል። ከዚህም በተጨማሪ የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችንም በመመልከት ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል። (ኢዛ)

አዲስ ቪዲዮ

ይከተሉን!

ስለእኛ

መጻሕፍት

ቪዲዮ

ኪነ-ጥበብ

ዜና እና ፖለቲካ